የዓለም መንግሥታት የደን ምንጣሮን ለማስቀረት ተስማሙ

እንስሳትና ዛፎች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

አንድ መቶ የሚሆኑ የዓለም አገራት በ2030 የደን ምንጣሮን ለማቆም ታሪካዊ የሚባል ስምምነት ሊያደርጉ ቃል ገቡ፡፡

ይህ ስምምነት ላይ የደረሱት እየተካሄደ ባለው የግላስኮ የዓለም አየር ንብረት ለውጥ ስብሰባ ነው፡፡

በዚህ ስምምነት አንዷ ፈራሚ ብራዚል መሆኗ እንደ መልካም ዜና ተወስዷል፡፡

ብራዚል በሰፊ የአማዞን የደን ምንጣሮ ምክንያት ለዓለም አየር ንብረት ለውጥ ትልቅ ስጋት ሆና ቆየታለች፡፡

የደን መደምሰስ በአየር ንብረት ለውጥ ላይ ትልቅ ሚና እንዳለው ይታመናል፡፡

ይህም የሚሆነው ዛፎች በተመናመኑ ቁጥር በአየር ንብረቱ የሚገኘው ካርቦንዳይኦክሳይድን የሚወስድ ተክል ስለሚቀንስ የአየር ንብረት መዋዠቅን ስለሚያስከትል ነው፡፡

በግላስጎ ለሁለት ሳምንታት የቆየው የአየር ንብረት ለውጥ የዓለም ሙቀት መጨመርን ለማስቀረት እንደ ወሳኝ እርምጃ የተወሰደና የተሞገሰ ሆኗል፡፡

የዛፎችን ምንጣሮ እናቆማለን የሚለውን ስምምነት ለመፈረም ቃል የገቡ አገራት ብራዚልን ጨምሮ ሩሲያ፣ ካናዳ፣ ኢንዶኔዥያ ይገኙበታል፡፡

እነዚህ አገራት የዓለምን 85 ከመቶ የደን ሽፋን የሚሸፍኑ ናቸው፡፡

የዩኬው ጠቅላይ ሚኒስትር ቦሪስ ጆንሰን ስምምነቱ የዓለምን የደን ሽፋን ወደነበረበት ለመመለስ ‹ማለፊያ ስምምነት› ብለውታል፡፡

በአሁን ሰዓት በየደቂቃው ስፋቱ 27 የእግር ኳስ ሜዳ የሚሆን የደን ሽፋን ምንጣሮ በዓለም ደረጃ ይደረጋል ተብሎ ይታመናል፡፡

ሳይንቲስቶች እንደሚያምኑት የደን መመናመን ለዓለም የአየር ንብረት መዋዠቅ ሁነተኛ ምክንያት ነው፡፡