BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
በመቀለ ከተማ ሁለት የተለያዩ ቦታዎች የድሮን ጥቃት መፈጸሙ ተነገረ
በትግራይ ክልል ዋና ከተማ መቀለ ውስጥ የድሮን ጥቃት መፈጸሙን እና በሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን የክልሉ ባለሥልጣናት አስታወቁ። ጥቃቱ ስለመፈጸሙ የክልሉ ኮሚዩኒኬሽን ቢሮ መግለጫ ያወጣ ሲሆን፣ የክልሉ ከፍተኛ ባለሥልጣንም ለኤኤፍፒ ዜና ወኪል አረጋግጠዋል። የክልሉ ምክትል ፕሬዝዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ አማኑኤል አሰፋ ለፈረንሳይ ዜና ወኪል ኤኤፍፒ እንደተናገሩት በመቀለ ከተማ ውስጥ ዛሬ ጠዋት የድሮን ጥቃት ተፈጽሟል።
ኢትዮጵያውያንን የሚመለከቱ አራት የፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢሚግሬሽን ውሳኔዎች
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሁለት ዓመት ሊሞላው ወራት በቀረው የሁለተኛው የሥልጣን ዘመናቸው፣ ስደተኞች እና ጥገኝነት ጠያቂዎችን ዒላማ ያደረጉ ትዕዛዞችን አሳልፈዋል። በተለያየ መንገድ ኢትዮጵያውያን ላይ ጫና ሊያሳድሩ የሚችሉ የትራምፕ አስተዳደር አራት ውሳኔዎችን እንመልከት።
የግብፅ የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ግንባታ ላይ ተገኝቷል የተባለው ጉድለት እና ያስነሳው ውዝግብ
የግብፅ መንግሥት፣ በአገሪቱ የሚገነባው 'ኤል ዳባ' የኒውክሌር ኃይል ማመንጫ ማብላያዎች (ሪአክተር) ላይ "ጉድለት" እንደተገኘ በመግለፅ ግንባታውን የሚያከናውነው የሩሲያው ኩባንያ ላይ አቅርቦታል የተባለው ወቀሳ ውዝግብ አስነስቷል። “የኒውክሌር ደኅንነት አሠራር" ላይ ጥሰት ስለመፈጸሙ የወጣውን ዘገባ ተከትሎ ምላሽ የሰጡት የግብፅ ባለሥልጣናት፣ ጉዳዩን አስተባብለዋል።
ቀጥታ, የአሜሪካው ግዙፍ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ 'ጆርጅ ዋሽንግተን' መካከለኛው ምሥራቅ ደረሰ
አብርሃም ሊንከንን እንደሚተካ የሚጠበቀው ዩኤስኤስ ጆርጅ ዋሽንግተን የተሰኘው ግዙፍ አውሮፕላን ተሸካሚ መርከብ ረቡዕ ዕለት መካከለኛው ምሥራቅ መድረሱን የአሜሪካ ጦር ማዕከላዊ ዕዝ (ሴንቲኮም) አስታወቀ። ሴንቲኮም በማኅበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ “ጆርጅ ዋሽንግተን እና ሌሎች ጥቃት ፈጻሚ መርከቦች ትናንት ወደ ሴንቲኮም ማዘዣ ከደረሱ በኋላ በመካከለኛው ምሥራቅ በተያዘለትጊዜ ውስጥ እንቅስቃሴውን ጀምሯል” ሲል አስታውቋል።
የአሜሪካ ፍርድ ቤት የትራምፕ አስተዳደር ለ5000 ኢትዮጵያውያን ተሰጥቶ የነበረውን ጊዜያዊ ከለላ እንዲያነሳ ፈቀደ
የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር፤ የጥገኝነት መብት የሌላቸው ከ5000 በላይ ኢትዮጵያውያን ከአሜሪካ እንዳይባረሩ ያደረገውን ሕጋዊ ከለላ እንዲያቋርጥ ፍርድ ቤት ፈቀደ። የቦስተን ዲስትሪክት ፍርድ ቤት ዳኛ ብሪያን መርፊ ያስተላለፉት ይህ ውሳኔ በአሜሪካ ሕጋዊ የመኖርና የመሥራት መብት ተሰጥቷቸው የነበሩ በርካታ ሰዎችን ለስደት መባረር ስጋት የሚያጋልጥ ነው።
በድሬዳዋ ከተማ ጉዳይ ላይ በሀገራዊ ምክክሩ ከምን ስምምነት ላይ ተደረሰ?
በሀገራዊው ምክክር ላይ የድሬዳዋ ከተማ በፌዴራል ከተሞች ጉዳይ ስር ምክክር ከተደረገባቸው ሁለት ከተሞች አንዱ ነው። ከኦሮሚያ እና ከሶማሌ ክልሎች በተወከሉ የምክክሩ አባላት መካከል ከፍተኛ የይገባኛል ክርክር እንደተደረገባት በምክክሩ ላይ የተሳተፉ ታማኝ ምንጭ ለቢቢሲ ተናግረዋል። ይሁን እንጂ የአዲስ አበባ ከተማ ጉዳይ ሰፊ መነጋገሪያ መሆኑ፣ የድሬዳዋ ጉዳይ ብዙም ትኩረት እንዳያገኝ አድርጎታል። ለመሆኑ በድሬዳዋ ላይ ምን ዓይነት ስምምነት ተደረሰ?
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
ቪዲዮ, “ጦርነት ከተጀመረ መንግሥታት ይለወጣሉ፤ ድንበሮች ይቀየራሉ”
ቢቢሲ በኢትዮጵያ እና በቀጣናዊ ወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በኬንያ የኢትዮጵያ አምባሳደር ባጫ ደበሌ ጋር ቃለ መጠይቅ አድርጓል። የኢትዮጵያ አሁናዊ ሁኔታ፣ ከህወሓት ጋር ያለው ውዝግብ፣ የባሕር በር ጥያቄ እና የቀጠናዊ የጦርነት ስጋቶች በቃለ መጠይቁ ተዳሰዋል። በተለይም በአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጦርነት ከተጀመረ ውጤቱ መሠረታዊ ለውጥን የሚያስከትል ሊሆን እንደሚችል ተናግረዋል።
ቪዲዮ, ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ስለኤአይ ጥቅም እና ጉዳት ምን ይላሉ?
ዓለማችንን በማይታመን ፍጥነት እየለወጠ ያለውን ሰው ሠራሽ አስተውሎት (ኤአይ) በአግባቡ መገንዘብ ምርጫ ሳይሆን ግዴታ እየሆነ የመጣ ይመስላል። ስለ ሰው ሠራሽ አስተውሎት የተዛቡ ምልከታዎች ምንድን ናቸው? ለወደፊቱ የኤአይ ዓለም እንዴት እራሳችንን ማዘጋጀት እንችላለን? የሚሉና ተያያዥ ጥያቄዎችን በተመለከተ ኢትዮጵያዊው የማይክሮሶፍት ባለሙያ ዶ/ር ግርማው አበበ ታደሰ ምላሽ ሰጥቷል።
ቪዲዮ, ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ስለምርጫ፤ ስለፕሪቶሪያ፤ ስለአርሲ. . . ምን አሉ?
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰናባቹ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ላቀረቡላቸው ጥያቄዎች በሰጡት ምላሽ የተለያዩ ወቅታዊ ጉዳዮችን አንስተዋል። ቢቢሲ ከጠቅላይ ሚኒስትሩ ንግግር ውስጥ አምስት ዋና ዋና ጉዳዮችን መርጦ አውጥቷል።
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
አነጋጋሪ ጉዳይ
የአዲስ አበባን ጉዳይ ቅርቃር ውስጥ ያስገባው "ከበላይ የመጣ" ሃሳብ እና የምክክር ኮሚሽኑ ምላሽ
አንድ ወር ባስቆጠረው አገራዊ ምክክር ስምንት አጀንዳዎች ላይ ሲመክሩ የቆዩት ከአራት ሺህ በላይ ተሳታፊዎች ወደ መቋጫው እየተቃረቡ ነው። በዚህ ሂደት የአዲስ አበባ ጉዳይ ከሌሎች አጀንዳዎች በበለጠ አነጋጋሪ እና ስምምነት ላይ ለመድረስ አዳጋች ሆኖ ታይቷል። በአዲስ አበባ የምክክር አጀንዳ ላይ የተከሰተው ምንድን ነው? ያላግባቡት ጉዳዮችስ የትኞቹ ናቸው?
አብን የሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ "መዋቅራዊ ጥሰቶች" እና "አንድ ወገን ብቻውን የሚወስንበት እንቅስቃሴ" ታይቷል ሲል ከሰሰ
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን)፣ በሀገራዊ ምክክር ሂደት ላይ "ከተራ የአሠራር ግድፈት" የዘለሉ "ተደጋጋሚ እና የተደራጁ ጥፋቶች ተፈጽመዋል" ሲል ከሰሰ። "ገዢው አካል መዋቅራዊ ጥሰቶችን" እንደፈጸመ በማንሳት የከሰሰው አብን፣ በአዲስ አበባ ጉዳይ ላይ "የከተማዋ ነዋሪዎች ድምፅ እና ፍላጎት በአግባቡ ሳይወከል" መታለፉን ገልጿል። በሂደቱ ላይ የተፈጸሙት "ተደጋጋሚ እና የተደራጁ ጥፋቶች" የሀገራዊ ምክክሩን "ተዓማኒነት፣ አካታችነት፣ ገለልተኝነት እና ፍትሐዊነት ጥያቄ ውስጥ የሚስገቡ" እንደሆኑም ገልጿል።
ከአማራ ክልል ቀውስ ጋር በተገናኘ በሽብር ለተከሰሱት የቀረበው የይቅርታ ሰነድ ምን አካቷል? ተከሳሾቹስ ምን ምላሽ ሰጡ?
በአማራ ክልል ከተከሰተው ቀውስ ጋር በተያያዘ በሽብር ለተከሰሱት ከሦስት መቶ በላይ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች እና ሌሎች ግለሰቦች በይቅርታ እንዲለቀቁ ሂደት ላይ ይገኛሉ። ለሽብር ተከሳሾች የቀረበው የይቅርታ ሰነድ በክልሉ ለተፈፀሙ ግድያዎች እና ጉዳቶች ተከሳሾቹ ኃላፊነት እንዲወስዱ የሚጠይቅ መሆኑን ቢቢሲ የተመለከተው ሰነድ ያሳያል።
በመተከል ዞን ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ተናገሩ
በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል፣ መተከል ዞን በታጣቂዎች በተፈፀመ ጥቃት በርካታ ሰዎች መገደላቸውን እና መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ለቢቢሲ ተናገሩ። ጥቃቱ የተፈፀመው ማክሰኞ ነሐሴ 6/ 2018 ዓ. ም. ጠዋት 12 ሰዓት ላይ በዞኑ ዋና ከተማ ግልገል በለስ በሚገኙ ቤተ ክርስቲያናት እና መናኸሪያ ላይ መሆኑን ነዋሪዎች ተናግረዋል።
በተስፋ ማጣት እና በሞት መሀል፡ የአማራ ክልል ሦስት የጦርነት ዓመታት
በአማራ ክልል ላለፉት ሦስት ዓመታት በፋኖ ኃይሎች እና በመንግሥት መካከል የሚካሄደው ግጭት የበርካቶችን ሕይወት ቀጥፏል፤ ከፍተኛ ሰብኣዊ እና ምጣኔ ሃብታዊ ውድመትም አድርሷል። ቢቢሲ አማርኛ ያነጋገራቸው የክልሉ ነዋሪዎች ከፍርድ ውጭ ግድያዎችን ጨምሮ ንጹኃን እስር እና እንግልትን እያስተናገዱ መሆኑን ይናገራሉ። የትጥቅ ግጭቶችን የሚመዘግበው አክሌድ ከጥር እስከ ሐምሌ 2018 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜውስት ብቻ ከስምንት ሚሊዮን በላይ ሰዎች 'ለግጭት' ተጋልጠዋል ብሏል። ቢቢሲ በግጭቱ በቀጥታ የተጎዱ ነዋሪዎችን እንዲሁም ባለሙያዎችን አነጋግሮ ቀጣዩን ዘገባ አሰናድቷል።
እስከ ግማሽ ሚሊዮን ብር የሚወጣባቸው ግዙፍ የሽምግልና አበባዎች፡ የአበባ አብዮት ወይስ የባህል ለውጥ?
ከጋብቻ በፊት የሚደረገው የሽምግልና ሥነ ሥርዓት ከፍተኛ ድግስ እና ገንዘብ የሚፈስበት እየሆነ መጥቷል። ከሚዘጋጀው ድል ያለ ድግስ ባሻገር በመቶ ሺዎች ብር የሚያስወጡ ቄንጠኛ ግዙፍ የአበባ ‘እቅፎች’ ደግሞ የሽምግልናው ሥርዓት አካል ሆነዋል። በተለይ የሚቀርበው የአበባ ስጦታ መነጋገሪያ ሆኗል። የሽምግልና ሥነ ሥርዓት የሰርግን ቦታ እየተካ ነው? ግዙፉ የአበባ ስጦታስ ከየት የመጣ ልማድ ነው?
"አዲስ አበባ እንደ እንግዳ ካልሆነ ከዚህ በኋላ ለመኖር የምመጣ አይመስለኝም"
የሥዕል እና የቅርጻ ቅርጽ ባለሙያ የሆነው ዮናስ መኳንንት፤ ተወልዶ ያደገባትን፣ የእንጀራ ገመዱ የነበረችውን አዲስ አበባን ጥሎ ገጠር ከገባ ከጥቂት ወራት በኋላ ሁለት ዓመት ይሞላዋል። "እኔ እዚህ ከመጣሁ ትልቅ እረፍት ነው የሚሰማኝ። በጣም ሰላማዊ ቦታ ነው፤ ምንም ዓይነት የመኪና ድምጽ የለም፣ የምትሰማው የእንስሳት ድምጽ ብቻ ነው" ይላል።
በዘውዱ ሃፍቱ ግድያ የዕድሜ ልክ እስር የተፈረደባቸው ግለሰቦች እንዴት በነጻ እንዲሰናበቱ ተወሰነ?
ከሦስት ዓመት በፊት በትግራይ ክልል መቀለ ከተማ በአሰቃቂ ሁኔታ በተገደለችው ዘውዱ ሃፍቱ ግድያ ተጠርጥረው የዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተላልፎባቸው የነበሩት ሁለት ፍርደኞች በነጻ እንዲሰናበቱ ተወስኗል። ውሳኔው በሰብአዊ መብት ተሟጋቾች ዘንድ ከፍተኛ ነቀፌታ ገጥሞታል። በማኅበራዊ ሚዲያ ላይም ቁጣቸውን ገልጸዋል።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የአሜሪካንን ባሕር ኃይል እየፈተኑ ያሉት የኢራን ትናንሽ ጀልባዎች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ባሕር ኃይል እንዳወደሙ ቢናገሩም፣ ኢራን ትናንሽ ፈጣን ጀልባዎችን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦችን እንቅስቃሴን መግታት ችላለች። ስለእነዚህ ውጤታማ የኢራን ፈጣን ወታደራዊ ጀልባዎች ምን እናውያለን?
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!
ከየፈርጁ
"አዳም አንድ ደራሲ የሚያስፈልጉት ሁሉም ግብዓቶች ተሟልተው ያሉት ፀሐፊ ነው"
የአዳም ረታ አዲሱ 'መዝሙረ ሄላም' የተሰኘው የረዥም ልብ ወለድ መጽሐፍ 1,008 ገጾች ሲኖሩት በአምስት ክፍሎች የተከፈለ ነው። ይህ የአዳም አዲስ መጽሐፍ ከዚህ ቀደም የሚጠቀማቸው እንደ ሕፅናዊነት ያሉ ሥነ ጽሑፋዊ ቴክኒኮችን የያዘ መሆኑን በመጽሐፉ አርትኦት ላይ የተሳተፈው ቢኒያም አቡራ ለቢቢሲ ተናግሯል። የመጽሐፉ መቼት ከዚህ ቀደም እንደነበሩ የደራሲው ሥራዎች ከ1950ዎቹ ማለቂያ እስከ 70ዎቹ መጨረሻ ያሉ ናቸው። መጽሐፉ መጠሪያ የሆነችው ሄላም ከዋና ገጸባሕሪያቱ አንዷ ስትሆን በሁሉም ክፍል ውስጥ ትገኛለች። ለሕፅናዊነት አጻጻፉ ኹነኛ ማስተሳሰሪያ በመሆን ታገለግላለች። ቢቢሲ ከአርታኢው ቢኒያም ጋር ያደረገውን ቆይታ እነሆ. . .
ሙዚቃ በሱቅ፣ በወጥ ቤት፣ በወፍጮ ቤት፣ በጋራዥ. . . የሚያጫውቱት ዲጄዎች
ዲጄ ሲባል መጀመሪያ የሚመጣልን ምሥል ምናልባትም የዳንስ ወለል ላይ ወዝ ወዝ የሚሉ ሰዎች እና ብልጭ ድርግም የሚል መብራት ይሆናል። እነዚህ ዲጄዎች ግን ማንኛውንም ቦታ ለሙዚቃቸው መዳረሻ ማድረግ የሚችሉ ናቸው። ጋራዥ፣ ቴአትር ቤት፣ ፀጉር ቤት፣ መጻሕፍት መደብር፣ ልብስ ሰፊ ቤት፣ ግንባታው ያልተጠናቀቀ 40/60፣ ሸክላ ሠሪ ቤት፣ ወፍጮ ቤት፣ ውይይት ታክሲ. . . የማይገቡበት የለም።
አጃኢብ!
የተመለሱ ጥያቄዎች
ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል። የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው። አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ሁለቱም ወጣቶች ከራሳቸው ህመም ተነስተው ሕክምና ለማጥናት መወሰናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።



































































































