የማንቸስተር ደርቢ፡ ማንቸስተር ዩናይትድ ወይስ ማንቸስተር ሲቲ? የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ ግምቶች

ማንቸስተር ዩናይትድ ከማንቸስተር ሲቲ

በ22ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ቅዳሜ ሰባት፣ እሑድ ሁለት እንዲሁም ቀሪው አንድ ጨዋታ ሰኞ ይከናወናሉ።

ቅዳሜ የሊጉ ጨዋታዎች የሚጀመሩት በጉጉት በሚጠበቀው የማንቸስተር ደርቢ ይሆናል።

ማንቸስተር ዩናይትድ ጊዜያዊ አሰልጣኝ አድርጎ በሾመው ማይክል ካሪክ እየተመራ በሜዳው ማንቸስተር ሲቲን ያስተናግዳል።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ይህንን ጨምሮ የሳምንቱን የሊጉን ጨዋታዎች ግምት እንደሚከተለው አስቀምጧል።

ቅዳሜ

ማንቸስተር ዩናይትድ ከማንቸስተር ሲቲ

ይህንን ጨዋታ ማን እንደሚያሸንፍ መገመት ብችልም የጎሉን ብዛት ነው ማወቅ የማልችለው።

ዩናይትድ በተለመደው አዙሪት ውስጥ ገብቷል።

ካሪክ ምን ዓይነት አሰላለፍ እንደሚመርጥ የሚታይ ቢሆንም የጨዋታው ውጤት ላይ ያን ያህል ተጽዕኖ ይፈጥራል ብዬ አላስብም።

ኧርሊን ሃላንድ ለበርካታ ጨዋታዎች ጎል ባያስቆጥርም ዩናይትድ ላይ ማስቆጠር ለምዷል።

ዩናይትድ ጎል ማስቆጠር ቢችልም ሦስት ነትቡ የማንቸስተር ሲቲ ነው።

ግምት፡ 1 - 3

ቼልሲ ከብሬንትፎርድ

የሊያም ሮስኒየር ቼልሲ ከቀድሞው አሰልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ቡድን ጋር ተመሳሳይ አጨዋወት ያለው ይመስላል።

ሁለቱ ቡድኖች በመጀመሪያው ዙር ሁለት አቻ ተለያይተው ነጥብ ተጋርተዋል።

ብሬንትፎርድ በጥሩ አቋም ላይ የሚገኝ እና ጨዋታውን ቢያሸንፍ ከቼልሲ በላይ መቀመጥ ቢችልም ግምቴ ወደ ሰማያዊዎቹ ያደላል።

ቼልሲ በርካታ ተጫዋቾችን በጉዳት እና በቅጣት ባያሳልፍም ለዚህ ጨዋታ የሚመለሱ ተጫዋቾችም አሉ።

ግምት፡ 2 - 1

ሊድስ ከፉልሃም

ሊድስ በመጀመሪያው ዙር ባለቀ ሰዓት በራሱ ላይ በተቆጠረ ጎል ቢሸነፍም አሁን ቡድኑ በብዙ መልኩ ተቀይሯል።

ፉልሃምም አንዳንድ ተጫዋቸኦችን በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ሲያጣ ይቸገራል ቢባልም ጥሩ መሻሻል አሳይቷል።

በሜዳው ሊድስ ያሽንፋል ብዬ ለመገመት ባስብም ፉልሃም ከሜዳው ውጭ ጎሎችን ማስቆጠር ይችልበታል።

ግምት፡ 1 - 1

ሊቨርፑል ከበርንሌይ

ሊቨርፑል ከበርንሌይ

በርንሌይ ካለፉት 5 ጨዋታዎች ሦስቱን አቻ ቢለያዩም በ12 ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻሉም።

ሊቨርፑል በበኩሉ ምን አይነት አቋም ይዞ እንደሚቀርብ ለመገመት አስቸጋሪ ነው።

የበርንሌዩ አለቃ ስኮት ፓርከር በ2022 በርንመዝን ይዘው 9 ልምን በሊቨርፑል በተሸነፉ ማግስት ከሥራ ተሰናብተዋል።

ፓርከር ተመሳሳይ ጎል ባያስተናግዱም ማሸነፍ እስከሚችሉ ድረስ ግን ጫና ይኖርባቸዋል።

ግምት፡ 2 -0

ሰንደርላንድ ከክሪስታል ፓላስ

ክሪስታል ፓላስ ባለፉት ዘጠኝ ጨዋታዎች ሦስት ነትብ ማሳካት አልቻለም።

ሰንደርላንድም ቢሆን ባለፉት አምስት ጨዋታዎች ማሸነፍ ባይችልም በእንቅስቃሴ ደረጃ ጥሩ ነበር።

ቡድኑ በሜዳው ሲጫወት ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑን ደጋግሞ አስመስከሯል።

ግምት፡ 1 - 0

ቶተንሃም ከዌስት ሃም

የሁለቱም ቡድኖች አሰልጣኞች ጫና ውስጥ ሆነው ይገናኛሉ።

ቶተንሃም በሜዳው ካደረጋቸው አስር ጨዋታዎች ሁለቱን ብቻ ነው ማሸነፍ የቻለው።

ሁለቱም ቡድኖች በደካማ አቋም ላይ ቢገኙም ይህ ጨዋታ ለኑኖ እስፒሪቶ ሳንቶ የበለጠ ከባድ ይሆናል።

ግምት፡ 1 - 0

ኖቲንግሃም ፎረስት ከአርሰናል

ኖቲንግሃም ፎረስት ከአርሰናል

ፎረስት በአራት የሊግ ጨዋታዎች ደረሰባቸውን ሽንፈት ዌስትሃምን በማሸነፍ ቀልብሰዋል።

ቡድኑ ከዚህ ጨዋታ ምንም ነጠብ ማሳካት አይችልም።

ሚኬል አርቴታ ይህንን ጨዋታ እንዴት እንደሚያሸንፍ ያውቃል። በጠባብ ውጤትም የበላይነቱን ይይዛል።

ግምት፡ 0 - 1

እሑድ

ዎልቭስ ከኒውካስል ዩናይትድ

ይህ ለመገመት የሚያስቸግር መርሐ ግብር ነው።

ዎልቭስ ያለፉትን ጥቂት ጨዋታዎች ሳይሸነፉ ለመጓዝ ከመቻላቻውም በላይ በኤፍኤ ካፕ ሽሪውቤሪን ማሸነፍ ችለዋል።

ኒውካስል ያለፉትን ሦስት ጨዋታዎች በማሸነፍ ደረጃውን ማሻሻል ችሏል።

በሻምፒዮንስ ሊግ እና በጉዳት ምክንያት ተጫዋቾችን ማፈራረቅ ስለሚጠይቅ ቡድኑ ውጤታማነቱን ማስቀጠል ላይ ሊከብደው ይችላል።

ግምት፡ 1 - 1

አስቶን ቪላ ከኤቨርተን

ቪላ ባለፉት 15 ጨዋታዎችን አንድ ሽንፈት ብቻ ነው ያስተናገደው።

ቡድኑ በራስ መተማመኑ ከማደጉም በላይ በርካታ ጎሎችን በማስቆተር ላይ ይገኛል።

ኤቨርተን ጃክ ግሪሊሽን ከቅጣት መልስ በማግኘቱ ይበልጥ ተጠቃሚ ይሆናል።

ዴቪድ ሞዬስ ለቪላ ቀላል ተጋጣሚ ባይሆኑም ባለሜዳው እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 2 - 1

ሰኞ

ብራይተን ከበርንመዝ

በርንመዝ ድንቅ አቋም ላይ የሚገኘውን አንቶኒዮ ሴሜኖን በማጣቱ ተጎጂ ቢሆንም ጥሩ የማጥቃት ባህሪ ያላቸው ተጫዋቾችን ይዟል።

ብራይተንም በማጥቃቱ በኩል ጥሩ ቢሆንም በመከላከል ረገድ ክፍተት አለበት።

በመሆኑም ጥሩ እንቅስቃሴ እና ጎሎች የሚታዩበት ጨዋታ እንደሚሆን እጠብቃለሁ።

ግምት፡ 2- 2