በኢትዮጵያ እንደተከሰተው ማርበርግ አስጊ የሆኑት ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች

ለመቀጠል ወደታች ይውረዱ

በሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰው መሠራጨት

ባለፉት ሦስት ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ የሚከሰቱ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ወረርሽኞ በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል። እነዚህ በሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ናቸው። የበሽታዎቹ መስፋፋት፣ በአህጉሪቱ ባለው ደካማ የጤና ሥርዓት እንዲሁም የማኅበራዊ እና ምጣኔ ሀብታዊ ተግዳሮቶች ምክንያት አፍሪካ ወደፊት ለሚከሰቱ ወረርሽኞች በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ትሆናለች ሲሉ የጤና ባለሙያዎች ያስጠነቅቃሉ።

የበሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰው መሠራጨት

አስካሁን ከእንስሳት ተነስቶ ወደ ሰው በመተላለፍ በስፋት የተከሰተው ወረርሽኝ ኤምፖክስ ሲሆን፣ በ32 የአፍሪካ አገራት ተሠራጭቷል፣ ከጥር 2022 አስከ መስከረም 2025 ድረስ ባለው ጊዜ 55 ሺህ ሰዎች በበሽታው መያዛቸውን የዓለም ጤና ድርጅት አመልክቷል። የአፍሪካ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል መረጃ እንደገለጸው ሁለት ሺህ የሚደርሱ ሰዎች በበሽታው ሕይወታቸውን አጥተዋል።

የበሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰው መሠራጨት

በበርካታ የአፍሪካ አገራት በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መጨመሩን ተከትሎ፣ በነሐሴ 2024 የዓለም ጤና ድርጅት ኤምፖክስን በዓለም አቀፍ ደረጃ አሳሳቢ የሕዝብ ጤና አደጋ ነው በማለት አውጇል። ይህ ውሳኔም በሁለት ዓመታት ውስጥ በኤምፖክስ ላይ የተላለፈ ሁለተኛው አዋጅ ነው።

የበሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰው መሠራጨት

የበሽታው ክስተት በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱን ተከትሎ የኤምፖክስ ወረርሽኝ በአፍሪካ ውስጥ አስጊ አይደለም ብሎ ድርጅቱ ቢያሳውቅም፤ በጋና፣ በላይቤሪያ እና በኡጋንዳ በሽታው በመስፋፋቱ ምክንያት በርካታ አገራት በተጠንቀቅ ላይ ይገኛሉ።

በዚህ ዓመት ከመስከረም አስከ ኅዳር ድረስ ባለው ጊዜ ውስጥ ዲሞክራቲክ ኮንጎ በሃምሳ ዓመታት ውስጥ ካጋጠሟት የኢቦላ ወረርሽኞች 16ኛውን ስትፋለም ቆይታለች። ኡጋንዳ ደግሞ ባለፈው ዓመት ሚያዝያ ላይ ካበቃው እና ለሦስት ወራት ከቆየው የኢቦላ ወረርሽኝ በኋላ በተጠንቀቅ ላይ ትገኛለች። ወረርሽኙ በኡጋንዳ ውስጥ ባለፉት 25 ዓመታት ለስምንተኛ ጊዜ ያጋጠመ ነው።

የምዕራብ አፍሪካዋ ሴኔጋል የሪፍት ቫሊ ትኩሳት የተባለ ወረርሽኝ እና እየጨመረ የሚሄድ የኤምፖክስ ወረርሽኝ አጋጥሟት፣ በሽታው መከሰቱ ከታወቀ በኋላ በሁለት ሳምንት ውስጥ 11 ሰዎች መሞታቸው ተዘግቧል።

ሩዋንዳ እና ታንዛኒያ በ2024 ያጋጠማቸውን የማርበርግ ወረርሽኝ ለመቆጣጠር ያደረጉት ጥረት ተሳክቶ በሽታው መጥፋቱን ሲያሳውቁ፣ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በግዛቷ ውስጥ ማርበርግ መከሰቱን አረጋግጣለች።

እነዚህ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉት በሽታዎች በመጠን፣ በድግግሞሽ እና በሚያደርሱት ጉዳት በወረርሽኝነት ከዚህ ቀደም ከሚታወቁበት እና በተደጋጋሚ ከሚከሰቱበት አካባቢ ውጪ በአዳዲስ ቦታዎች እየተስፋፉ መሆናቸው የጤና ባለሙያዎች የሚሰጡትን ማስጠንቀቂያ የሚያረጋግጥ ነው። የተባበሩት መንግሥታት የአካባቢ ፕሮግራም እንደሚለው እንዲህ ያለው ሁኔታ ከአውሮፓውያኑ 1940 ጀምሮ በተደጋጋሚ እየተከሰተ ነው።

የዓለም ጤና ድርጅት እንደሚለው በየዓመቱ

1000000000

ሰዎች ከእንስሳ በሚተላለፉ በሽታዎች ተይዘው ሚሊዮኖች ይሞታሉ።

1,000,000,000

የዓለም ጤና ድርጅት ትንተና እንደሚያሳየው በአፍሪካ ባለፉት አስር ዓመታት ከእንስሳት የሚተላለፉ በሽታዎች ወረርሽኝ በ63% ከፍ ብሎ አህጉሪቱን ክፉኛ የተጠቃች አድርጓታል።

ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ባለንበት ክፍለ ዘመን በአፍሪካ ውስጥ ከተከሰቱ የተላላፊ በሽታ ወረርሽኞች አንድ ሦስተኛውን ይይዛሉ።

የበሽታዎቹ ክስተት መጨመር ያሳሰበው የአፍሪካ ሲዲሲ ባለፈው ሐምሌ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ወረርሽኞችን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የአራት ዓመት ዕቅድ ሥራ ላይ አውሏል።

የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ጂን ካሲያ ማስረጃዎች ላይ በመመሥረት አፍሪካ ወደ ሌላ ወረርሽኝ ለመግባት ተቃርባለች ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

ዶ/ር ጂን ካሲያ፣ የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተርዶ/ር ጂን ካሲያ፣ የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተርጌቲ ኢሜጅስ


ይህንን ዓመት ጨምሮ ባለፉት ዓመታት ኢቦላ፣ ማርበርግ፣ ኤምፖክስ እና ሌሎች የተለያዩ ዓይነት የወረርሽኝ ክስተቶች በከፍተኛ ደረጃ ጨምረዋል።

ዶ/ር ጂን ካሲያ፣ የአፍሪካ ሲዲሲ ዋና ዳይሬክተር

ባለፉት ሁለት ዓመታት በአፍሪካ ውስጥ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ወረርሽኝ በ41% መጨመሩን ዋና ዳይሬክተሩ ይናገራሉ።

alt="መፈለጊያዎን

መፈለጊያዎን ያሻሽሉ

ዋነኞቹ አምስት ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች እንዴት በመላው ዓለም ተስፋፉ?

የበሽታው ክስተቶች

0

<100

<200

<300

<500

<999

1000+

ምንጭ፡የዓለም ጤና ድርጅት፣ የአሜሪካ ሲዲሲ፣ የአፍሪካ ሲዲሲ እና የአገራት ጤና ሚኒስቴሮች

በሽታዎች ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉት እንዴት ነው?

ሰዎች ከተህዋሲያኑ ጋር በሚኖራቸው ቀጥተኛ ንክኪ፣ በምግብ፣ በውሃ፣ በአየር ወይም በተበከሉ አካባቢዎች ምክንያት በሽታዎቹ ይተላለፋሉ።

ከእንስሳት የሚነሱ የወረርሽኞች ክስተት ሁኔታ በከፍተኛ ሁኔታ የተለያየ ነው።

ለምሳሌ ኤምፖክስ፣ ዓለም አቀፍ ወረርሽኝ ሆኖ ከመከሰቱ በፊት ለአስርት ዓመታት በተለያዩ ጊዜያት አልፎ አልፎ ሲያጋጥም ቆይቷል። በንጽጽር ኮቪድ-19 ደግሞ በድንገት ተከስቶ በዓለም ዙሪያ በፍጥነት ተዛምቷል።

የእብድ ውሻ በሽታ፣ ቻጋስ፣ ላሳ ፊቨር እና ሳልሞኔሎሲስን የመሳሰሉ ሌሎች በሽታዎች ደግሞ በተደጋጋሚ በመከሰት በየዓመቱ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎችን በተወሰኑ አካባቢዎች ይገድላሉ።

ኤችአይቪ መጀመሪያ ላይ ከእንስሳት የተነሳ ቫይረስ ሲሆን፣ ኋላ ላይ ግን ሰውን ብቻ ወደሚያጠቃ የቫይረስ ዝርያ ተለውጧል።

ሪፍት ቫሊ ፊቨር ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፍ ሲሆን፣ ነገር ግን ከአንድ ሰው ወደ ሌላ ሰው አይተላለፍም። ማርበርግ ግን ከእንስሳት ወደ ሰው ከተላለፈ በኋላ ከሰው ወደ ሰው ይዛመታል።

ለምሳሌ የሩዋንዳ የጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሳቢን ንሳንዚማና እንዳሉት በአገሪቱ በ2024 ለተከሰተው የማርበርግ ወረርሽኝ መነሻ የሆነው ግለሰብ ለቫይረሱ የተጋለጠው የሌሊት ወፎች ከሚኖሩበት ዋሻ ነው።

ለምን በሽታዎቹ በተደጋጋሚ ይከሰታሉ?

ከእንስሳት ወደ ሰው ለሚተላለፉት በሽታዎች ክስተት መጨመር በርካታ ተያያዥ ምክንያቶች እንዳሉ የአፍሪካ ሲዲሲ ይገልጻል። ከእነዚህም መካከል የአየር ንበረት ለውጥ፣ የዱር እንስሳት መኖሪያዎች ላይ የሚደርሰው ውድመት፣ የአካባቢ መጎሳቆል፣ የከተሞች መስፋፋት፣ ፈጣን የሕዝብ ቁጥር ዕድገት፣ ለእንስሳት ተዋጽኦዎች ያለው ፍላጎት መጨመር፣ ዓለም አቀፋዊ ትስስር እና የተወሰኑ ባህላዊ ድርጊቶች ይጠቀሳሉ።

ሰዎች ወደ ዱር እንስሳት መኖሪያዎች መግባት እና የዱር እንስሳት ንግድ መጨመሩ ከእንስሳት ወደ ሰው ለሚተላለፉ በሽታዎች ያለን ተጋላጭነት ጨምሮታል የሚሉት በአሜሪካው ቴክሳስ ዩኒቨርስቲ ሳውዝዌስተርን ሜዲካል ሴንተር የተላላፊ በሽታዎች ተመራማሪ ዶ/ር ክሩቲካ ኩፓሊ እና በኬንያ የአሜሪካ በሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል የበሽታዎች ቅኝት ክፍል ኃላፊ ዶ/ር ፔኒናህ ሙንዩዋ ናቸው።

ዶ/ር ክሩቲካ ኩፓሊ፣ ከሳውዝዌስተርን ሜዲካል ሴንተርዶ/ር ክሩቲካ ኩፓሊ፣ ከሳውዝዌስተርን ሜዲካል ሴንተርሳውዝዌስተርን ሜዲካል ሴንተር


አብዛኞቹ በቫይረስ የሚተላለፉ ተህዋሲያን ከትንፋሽ በሚወጡ ብናኞች፣ ከሰውነት በሚወጡ ፈሳሾች ወይም በትንኞች አማካኝነት በፍጥነት ይዛመታሉ።

ዶ/ር ክሩቲካ ኩፓሊ፣ ከሳውዝዌስተርን ሜዲካል ሴንተር

የተጠናከረ የሕክምና ቅኝት ሥርዓት ወረርሽኞችን በተሻለ ሁኔታ ለመለየት እና ለማሳወቅ እንደሚያስችል ባለሙያዎች ይናገራሉ።

ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ስጋት ያለባቸው አካባቢዎች የትኞቹ ናቸው?

ዲሞክራቲክ ኮንጎ በአሁኑ ወቅት ከኢቦላ ጋር እየታገለች ሲሆን፣ እስካሁን ባለው የኤምፖክስ ወረርሽኝ ከፍተኛውን የሞት መጠን አስመዝግባለች። ብራዚል ደግሞ በከፍተኛ ሁኔታ ከእንስሳት ወደ ሰው በሚተላለፉ በሽታዎች ተጠቅታለች።

ዲሞክራቲክ ኮንጎ የእብድ ውሻ በሽታን እና ስሊፒንግ ሲክነስን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ይገኙባታል።

በተመሳሳይ ብራዚልም ቢጫ ወባ፣ ቺኩንጉኒያ፣ ዴንጊ ፊቨር እና ዚካ ቫይረስ በተደጋጋሚ ይከሰቱባታል።

በሁለቱ አገራት እና በሌሎች በኮንጎ ተፋሰስ፣ በደቡብ አሜሪካ እና በደቡብ ምሥራቅ እስያ በሚገኙ አገራት ውስጥም ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ይከሰታሉ።

alt="መፈለጊያዎን

መፈለጊያዎን ያሻሽሉ

የአምስቱ ዋነኛ ከእንስሳ ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ክስተት እና ሞት አጠቃላይ ድምር

የበሽታው ክስተቶች

0

<100

<200

<300

<500

<999

1000+

ምንጭ፡የዓለም ጤና ድርጅት፣ የአሜሪካ ሲዲሲ፣ የአፍሪካ ሲዲሲ እና የአገራት ጤና ሚኒስቴሮች

የዱር እንስሳት ሥጋ መመገብ ከእንስሳት ወደ ሰው ለሚተላለፉ በሽታዎች ያለን ተጋላጭነትን ከፍ ያደርገዋል፣ ይላሉ ዶ/ር ሙንዩዋ።

በማዕከላዊ አፍሪካ ብቻ
አንድ ቢሊዮን ኪሎ ግራም
የሚመዝን የዱር እንስሳት ሥጋ በየዓመቱ ይበላል።

ዲሞክራቲክ ኮንጎ እና ብራዚል ባሏቸው ኮንጎ እና አማዞን በሚባሉት ግዙፍ ጥቅጥቅ ደኖች ምክንያት በርካታ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎች ይከሰቱባቸዋል።

ዶ/ር ኩፓሊ እንደሚሉት እነዚህ ደኖች በሽታዎችን ተሸክመው የሚያስተላልፉ የትናንሽ እንሰሳት እና ትንኞች መኖሪያ ናቸው።

ዶ/ሯ ጨምረውም በዲሞክራቲክ ኮንጎ ያለው የድህነት ሁኔታ፣ ውስን የጤና አገልግሎት እና በግጭት የተነሳ ሰዎች ተጨናንቀው በመኖራቸው በሽታዎቹ በቀላሉ በፍጥነት የመዛመት ዕድል ስለሚኖራቸው ውጤቱ የከፋ ይሆናል ይላሉ።

ከእንስሳት ወደ ሰው ለሚተላለፉ ለአብዛኞቹ በሽታዎች ቫይረሶች ለምን ምክንያት ይሆናሉ?

ቫይረሶች ባላቸው በፍጥነት የመዛመት ባህሪ ምክንያት ለከፍተኛ ወረርሽኝ መከሰት አመቺ ናቸው። በዚህም ሳቢያ አንድ ጊዜ ከእንስሳት ወደ ሰው ከተላለፉ በኋላ በፍጥነት በመስፋፋት ከጤና አገልግሎት አቅም በላይ ይሆናሉ።

ቫይረሶች አዳዲስ ተቀባዮቻቸውን ለመላመድ እና የተፈጥሮ በሽታን የመከላከያ ሥርዓት ለመውረር ባህሪያቸውን በፍጥነት ይቀያይራሉ። ክላድ 1ቢ የተባለው የኤምፖክስ ዝርያን የመሳሰሉ ልውጥ ቫይረሶች በከፍተኛ ሁኔታ ተላለፊ እና አደገኛ እንደሚሆኑ ዶ/ር ኩፓሊ ይናገራሉ።

በሽታ አምጪ ተህዋሲያኑ በዱር እንስሳት ውስጥ ስለሚቆዩ እና ምልክቶችን ስለማያሳዩ በቫይረስ ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ ወረርሽኞችን አመጣጥን ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው።

ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን የሚሸከሙ እንስሳት የትኞቹ ናቸው?

በሽታዎችን ወደ ሰው የሚያስተላለፉ እንስሳት በሁለት ምድብ ይከፈላሉ።

ተሸካሚ ወይም ማከማቻ የሚባሉት ለበሽታ መነሻ የሚሆኑ ተህዋሲያንን በውስጣቸው የሚይዙ እንሰሳት ናቸው። በራሪ ነፍሳት ደግሞ ተህዋሲያኑን ወደ ሰዎች እና ወደ ሌሎች ያሸጋግራሉ።

የተህዋሲያኑ ተሸካሚ የሆኑት የሌሊት ወፍ፣ ግመል፣ ዶሮ፣ አይጥ እና ወፎች በሽታን በማስፋፋት በኩል ፈታኝ ሁኔታን ይፈጥራሉ በማለት ዶ/ር ሙንዩዋ ይናገራሉ።

ዶ/ር ፔኒናህ ሙንዩዋ፣ የአሜሪካ ሲዲዲ ቅርንጫፍ በኬንያ ዶ/ር ፔኒናህ ሙንዩዋ፣ የአሜሪካ ሲዲዲ ቅርንጫፍ በኬንያ ቢቢሲ/ፒተር ንጆሮጌ


የሌሊት ወፎች በሁሉም ቦታ የሚገኙ ሲሆን በቅርቡ የተገኙትን ኢቦላ ቫይረስ እና ማርበርግ ቫይረስን ጨምሮ የተለያየ ዝርያ ያላቸው በርካታ ቫይረሶችን ይሸከማሉ።

ዶ/ር ፔኒናህ ሙንዩዋ፣ የአሜሪካ ሲዲዲ ቅርንጫፍ በኬንያ

ዶክተሯ ጨምረውም በዓለም ላይ ከሚገኙ ግመሎች ውስጥ ሁለት ሦስተኛው በአፍሪካ ውስጥ ስለሚገኙ፤ የኮሮናቫይረስ ዓይነቶች ዋነኛ መከማቻ የሆኑት ግመሎች በአፍሪካ አደጋን ደቅነዋል።

የተህዋሲያን ተሸካሚዎች እና አስተላላፊዎች የሆኑት አይጦች እና ወፎች በተለያዩ አካባቢዎች ስለሚኖሩ በሽታዎችን ለመቆጣጠር አስቸጋሪ ያደርጉታል።

የምዕራብ አፍሪካ አገራት በሆኑት ሴራ ሊዮን እና ላይቤሪያ ውስጥ በዓመት ወደ ሆስፒታል ከሚገቡ ስድስት ሰዎች መካከል አንዱን የሚያጠቃውን የላሳ ፊቨር በሽታ ተህዋሲን አይጦች ይሸከማሉ ወደ ሰዎችም ያስተላልፋሉ።

በሽታን ወደ ሰው በማስተላለፍ ለሳይንቲስቶች አሳሳቢ የሆኑት እንስሳት የትኞቹ ናቸው?

በ2024 የዓለም ጤና ድርጅት ሪፖርት በዓለም ዙሪያ የበሽታ ወረርሽኞችን ሊያስከትሉ የሚችሉ 30 የሚሆኑ ተህዋሲያንን ለይቶ ነበረ። አብዛኞቹ ከእንስሳት የሚነሱ መሆናቸውንም አመልክቷል።

እነዚህም ኤምፖክስ፣ ዴንጊ ቫይረስ፣ ኢንፍሉዌንዛ ኤ ቫይረስ፣ ኤምፖክስ ቫይረስ እና ዓለም አቀፉን ኮቪድ-19 የቀሰቀሰውን ቫይረስ ጨምሮ ሳርቤኮቫይረስ የሚባሉት የኮሮናቫይረስ ዓይነቶች ናቸው።

ከእንስሳት የሚነሱ በሽታዎችን መስፋፋት ለመቀነስ መፍትሄው ምንድን ነው?

ዶ/ር ሙንዩዋ እና ዶ/ር ኩፓሊ ሩዋንዳ የማርበርግ ቫይረስ ወረርሽኝን የተቆጣጠረችበትን ውጤታማ መንገድ እንደ ምሳሌ በማንሳት፣ ቀጣይ ወረርሽኞችን ቀድሞ ለመለየት እና ለመቆጣጠር ምላሽ የሚሰጥበትን ጥረት ማሻሻል እና ማቀናጀት ወሳኝ መሆኑን ይናገራሉ።

"ሩዋንዳ የወረርሽኝ ቅኝት እና ምርመራ እንዲሁም ውስን የሕክምና ሙከራ በፍጥነት በማካሄድ በሽታውን የመቆጣጠር ሥራን አከናውናለች" ብለዋል ዶ/ር ኩፓሊ።

ባለሙያዎች እንደሚሉት ተከታታይነት ያለው የምርመራ መሳሪያዎች፣ የክትባቶች፣ የመድኃኒት እና የሕክምና አቅርቦት በአፍሪካ ውስጥ የሚያጋጥሙትን ከእንስሳት ወደ ሰው የሚተላለፉ በሽታዎችን ለመቆጣጠር ወሳኝ ናቸው።