የአእምሮ ምጥቀት (IQ) ምንድን ነው?

ሰሞኑን በማህበራዊ መገናኛ ብዙኀን ላይ የኢትዮጵያውያንን የአእምሮ ምጥቀት መለኪያ (Intelligence Quotient) የሚያሳይ መረጃ ወጥቷል በሚል በርካቶች ሲቀባበሉት ነበር።
በርካቶች በወቅቱ ሲወያዩበት የነበረው ኢትዮጵያውያን በአስተሳሰብ ችሎታ ማነስ ከበርካታ የዓለማችን አገሮች ሁሉ ዝቅ ብለው መገኘታቸውን ነበር።
ይህ መረጃ የኢትዮጵያውያን የአእምሮ ምጥቀት ተመዝኖ 63 መሆኑን ያሳያል።
የኢትዮጵያውያን የማሰብ እና ነገሮችን የመረዳት የአዕምሮ አቅም (አይ ኪው) 163ኛ ደረጃ ላይ ያደረገው ይሄ መረጃ በርካታ አመታትን እንዳስቆጠረም ሀሰተኛ ዜናዎችን በሚከታተሉና ይፋ በሚያደርጉ ገጾች ቢገለፅም አነጋጋሪነቱና አወዛጋቢነቱ ቀጥሏል።
ለመሆኑ በርግጥ የአእምሮ ምጥቀት ምንድን ነው?
የአእምሮ ምጥቀትዎ ምን ያህል ነው? 120? 91? ደግሞስ ምን ማለት ነው? የአንድን ሰው የአእምሮ ምጥቀት መፈተሽ እና መናገር ይቻላል?
ፈተናውንስ የሚያስቀምጠው ማን ነው? ውጤቱስ የሚያመጣው ለውጥ ምንድን ነው?
በዚህ ጽሑፍ የአእምሮ ምጥቀት የምንለው IQ የሚለውን በአቻነት ወክሎ ቆሞ ነው።
አንድ ማህበረሰብ ወይም እንደ አገር በአምዕምሮ ምጡቅ ነው ሲባል ምን ማለት ነው? የምጥቀት መለኪያም መስፈርቶችም ዘመናትን ቢሻገሩም አወዛጋቢነታቸው እንደቀጠለ ነው።
የእነዚህን መስፈርቶችም ሆነ የማህበረሰቡን ሳይንስ ጥናቶች የሚያካሂዱት ምዕራባውያን ከመሆናቸው ጋር ተያይዞ የአፍሪካ፣ የእስያ ባህልና ማንነት ያላገናዘበ ነው በሚልም ይተቻል። ምዕራባውያንን ያማከለ ከመሆኑ አንፃር በአንዳንድ አገራት ምጡቅ የሚባሉ እሳቤዎችንም አላካተተም ይባላል።
ለመጀመሪያ ጊዜ ስለዚህ ጉዳይ የተሰማው ከአልፍሬድ ቢኔት ነው። ፈረንሳዊው አልፍሬድ በመንግሥት ፈተና እንዲያዘጋጅ ታዝዞ ነበር።
ትእዛዙ ተማሪዎች በትምህርታቸው ላይ ድጋፍ ይፈልጉ እንደሆን ለማወቅ ያለመ ነው። በኋላ ላይ አይ ኪው (Intelligence Quotient) ተብሎ ተጠራ።
መጀመሪያ ላይ የሆነ ችሎታን ለመመዘን የተዘጋጁ ፈተናዎች ነበሩ። ስለዚህ ቢኔት የመጀመሪያው የአእምሮ ምጥቀት (IQ) ምዘና መስራች ሲሆን ዛሬ ወዳለን የአይኪው ግንዛቤም አምርቷል።
በዚህ ዘመን የአእምሮ ምጥቀት ስንል አንድ ግለሰብ ያለው አጠቃላይ የአእምሮ ምጥቀት ተመዝኖ ከ 1 እስከ 100 ድረስ ተሰፍሮ ሲለካ ማለታችን ነው።
ከፈረንሳዊው ቢኔት በመቀጠል ደግሞ አትላንቲክን አቋርጦ በአሜሪካዊው የሥነልቦና ምሁር ሃሳቡ ጎልብቶ አይ ኪው ማለት ተፈጥሯዊ ነው፤ አብሮን ይወለዳል እንጂ የምንለውጠው ነገር የለም ወደሚል እሳቤ አደገ።
ይኸው ምሁር የተለያዩ ኅብረተሰብ ቡድኖች፥ ብሔሮች ብሔረሰቦች የተለያየ የአእምሮ ምጥቀት አላቸው ሲል አስረዳ።
እኤአ በ1995 ወደ አሜሪካ ለመምጣት ሙከራ የሚያደርጉ ስደተኞች የአእምሮ ምጥቀት ፈተና ይሰጣቸው ነበር።
በሮም ግዛት ዙሪያ ተሰባስበው የነበሩት እነዚህ አይሁዳውያን በአእምሮ ምጥቀት ፈተናው ዝቅተኛ ውጤት ያስመዘግቡ ስለነበር የአሜሪካን መሬት እንዳይረግጡ ተደርገው ቆይተዋል።
ከስዊድን፣ ኖርዌይ፣ ዴንማርክ፣ፊንላንድ እና አይስላንድ የሚመጡ ዜጎች ደግሞ ይህንን ፈተና ከፍተኛ ውጤት ስለሚያስመዘግቡ ወደ አሜሪካ እንዲገቡ ይደረግ ነበር።
ይህ ቀድሞ በአሜሪካ ይደረግ የነበረው የአእምሮ ምጥቀት ፈተና ውድቅ ተደርጓል።

የፎቶው ባለመብት, new-iq-test.com
በሮም ግዛት ዙሪያ የተሰባሰቡት አይሁዶች በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት አካባቢ የአእምሮ ምጥቀታቸው አማካኝ ነጥብ ዝቅተኛ ነበር። ነገር ግን በሁለተኛው ዓለም ጦርነት ወቅት ከአማካኝ ነጥብ ከፍተኛ ሆኖ ተገኝቷል።
ለዚህ ደግሞ ምክንያት የተሻለ መማር፣ የተመጣጠነ ምግብ መመገብ እንዲሁም ቤተሰቦቻቸውም በተሻለ ፊደል ቆጥረው መገኘታቸው ነው።
ይህ ማለት የአእምሮ ምጥቀትን ሊለውጡ የሚችሉ ምክንያቶች አሉ ማለት ነው። የተለያዩ ቡድኖች የተለያየ የአእምሮ ምጥቀት ውጤት አላቸው ማለት ምዘናው የሚለካው የማይጨበጥ የማይዳሰስ ምጡቅነትን ማለትም ነው።
ምን ማለት ነው? የአንድ ሰው የማይጨበጥ አመክኗዊነትን በአግባቡ መረዳትና ተግባራዊ ማድረግ መቻል ማለት ነው።
ይህንን ደግሞ በልጅነት እድሜ ውስጥ የሚገጥሙ ነገሮች ይወስኑታል።
አመክኗዊ ክርክር ከማይታጣበት ማህበረሰብ የመጣ ግለሰብ፣ እንዲያነብ ከሚበረታታ፣ ውይይትን ከሚያበረታታ ማህበረሰብ የተገኘ ግለሰብ በአመዛኙ ከፍተኛ የአእምሮ ምጥቀት ይኖረዋል።
ለበርካታ ዓመታት የአእምሮ ምጥቀት ምዘና የሚውለው ለፖለቲካ አላማ ነበር። ፖለቲከኞች፣ ጾተኛም ሆኑ ዘረኛ ሃሳባቸውን ደግፎ እንዲያቆምላቸው ይጠቀሙበታል።
ደግሞ የምጥቀት ምዘናው 'ሳይንሳዊ" መሆን በበርካታ መንግሥታት ያለአግባብ ጥቅም ላይ እንዲውል በሩን ሰፋ አድርጎ ከፍቶታል።
በ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ላይ ደግሞ ከሌሎች በተለየ የሴቶች አእምሮ ምጥቀት ምዘና ዝቅ ብሎ ታይቷል።
የአእምሮ ምጥቀት ምዘናዎች፣ እንቆቅልሾችን መጨረስ፣ ተግባራትን ማከናወን ናቸው። አንድ ሰው እነዚህን እንቆቅልሾችም ሆኑ ተግባራት ለማከናወን የሚፈጅበት ጊዜ አልያም አለመቻሉ ተመዝኖ ነጥቡ ይሰጣል።
ከዚህ በፊት እንዲህ አይነት ተግባራትን ለማከናወን ተጋልጦ ካልነበራቸው፣ ከዚህ በፊት ተግባሩን ካከናወነ ጋር እኩል ሊወዳደሩ አይችሉም።
የአእምሮ ምጥቀት ፈተና አንደኛው የተሳሳተ ግንዛቤ ሰዎች ከብልህነት ጋር በአቻነት መውሰዳቸው ነው። ነገር ግን የአእምሮ ምጥቀት ምዘናው የማይዳሰስ አመክንዮን የሚመዝን ሲሆን የተለያዩ ዓይነት ብልህነቶችም አሉ።
ለምሳሌ የማስታወስ ችሎታ፣ ሊለካ የማይችለው ጥበብም የሚገኙት በብልህነት ስር ነው። ለምሳሌ እነዚህ ነገሮች ባይለኩም እንኳ የሒሳብ፣ ሳይንስ፣ ኮምፒውተር ሳይንስ እውቀት ላይ ያገለግላሉ። እነዚህ ደግሞ የአእምሮ ምጥቀት ለመለካትም ያገለግላሉ።
የአእምሮ ምጥቀትን ከብልህነት ጋር በአቻነት አድርጎ መውሰድ በበርካቶች ዘንድ ይታያል።
የአእምሮ ምጥቀት ፈተናውን ቀድሞ መለማመድ ከተቻለ በተለያየ ምክንያት ሊለያይ ይችላል።
ስለዚህ የአእምሮ ምጥቀትን መለማመድ ከተቻለ በየጊዜው ሊሻሻል እና ከፍ ሊል የሚችል ጉዳይ ነው ማለት ነው።
ብልህነት መልከ ብዙ ነው። መልከ ብዙ የሆነ ነገር ደግሞ በአንድ ቁጥር ብቻ የሚሰፈር አይደለም። ብልህነትን ለመለካት ዝርያን የሚጠቅሱ አካላት በሺዎች የሚቆጠሩ ጂኖች መኖራቸውን ማስተዋል ይገባቸዋል።
ስለዚህ ብልህነት በነጠላ ቁጥር ከሚመዘነው የአእምሮ ምጥቀት ምዘና በእጅጉ የተለየና የተወሳሰበ ነገር መሆኑን ማስታወስ ያስፈልጋል።















