የእንግሊዙ ኤምአይ5 ሰላይ የኃላፊነት ቦታውን የሴት ጓደኛውን ለማሸበር ተጠቅሞበታል ተባለ

ሜንጫ የያዘ ግለሰብ

የእንግሊዙ ኤምአይ5 ሰላይ የስራውን ባህርይና ኃላፊነቱን የሴት ጓደኛውን ለማሸበር እንደተጠቀመበት ቢቢሲ ባካሄደው ምርመራ አረጋግጧል።

ሰላዩ በፖሊስ እየተመረመረ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት የስለላ ተግባሩን ለመቀጠል ወደ ውጭ አገር ተሰማርቷል።

ቢቢሲ ሰላዩ በርካታ ስሞችን በመጠቀም ለኤምአይ5ና ሲኤአይኤስ ለበርካታ ዓመታት መስራቱንም አረጋግጧል።

ቢቢሲ ያገኘው ቪዲዮ ግለሰቡ የሴት ጓደኛውን ለመግደል ሲያስፈራራ እንዲሁም በሜንጫም ጥቃት ሲያደርስባት ይታያል።

ሰላዩ የውጭ ሃገር ዜጋ መሆኑ የታወቀ ሲሆን ግለሰቡ ለሴቶች ከፍተኛ ስጋት መሆኑን የሚያሳይ ማስረጃ ቢኖርም የእንግሊዝ መንግሥት ቢቢሲን ፍርድ ቤት ወስዶ ስሙ በይፋ እንዳይታተም አድርጓል።

መረጃዎች እንደሚያሳዩት ግለሰቡ የቀኝ ጽንፈኛ አክራሪ እና በርካታ የጭካኔ ተግባራትን በማከናወን የቀደመ ታሪክ ያለው ነው።

ሰላዩ ታዳጊ ሴቶች ላይ ጾታዊ ጥቃት ለማድረስና ለመግደል ዛቻ ይፈፅም እንደነበር የቢቢሲ ምርመራ አረጋግጧል።

ቢቢሲ ከዚህ ቀደም ባልገጠመው የፍርድ ቤት ሙግት ሴቶች የግለሰቡን ማንነት የማወቅ መብት እንዳላቸው እና ተጠቂዎችንም ከጉዳት መከላከል ያስችላልም በሚል ስሙ ይፋ እንዲሆን ተከራክሮ ነበር።

ነገር ግን መንግሥት ይህንን የምርመራ ዘገባ ቢቢሲ እንዳያትም ያደረገውን ሙከራ የታቀወመ ሲሆን በዚህም ተሳክቶለታል።

የብሪታንያ ዜጋ የሆነችው ቤት (ትክክለኛ ስሟ አይደለም) ሰላዩ ጋር የተዋወቁት በበይነ መረብ የፍቅር ጓደኛ መፈለጊያው ቲንደር ላይ ነው።

ጥንዶቹ በእንግሊዝ አብረው መኖር ጀመሩ፥።

የመጀመሪያ የፍቅራቸው ወቅት ግለሰቡ "አስደሳች" ነበር ትላለች። በርካታ የሚያመሳስሏቸው ጉዳዮችም ነበሩ።

ነገር ግን በጊዜ ሂደት ፆተኛ፣ ጭፍንና ጭካኔና ዓመፅን እንደሚወድ ተረዳች።

ጾታዊ ጥቃቶች ከመፈፀም በተጨማሪ አካላዊ ጥቃቶችን ይፈፅምባት እንደነበርና ያስገድዳትም ነበር ትላለች።

መሳሪያ ይሰበስብ እንደነበርና አሸባሪዎች የሚፈጽሙትን ግድያም በግድ እንድትመለከት ያደርጋት ነበር።

ግለሰቡ መጀመሪያ ላይ እውነተኛ ስሙን ከእርስዋ ደብቆ እንደነበር ትናገራለች።

ከእንግሊዝ የደህንነት መስሪያ ቤት ጋር ያለውን የኃላፊነት ቦታ ለማሸበር ተጠቅሞበታል ትላለች።

"ሙሉ በሙሉ ተቆጣጥሮኝ ነበር። የአሁኑ ማንነቴ ጥላ ነበርኩ" ትላለች።

አካላዊ ጥቃቱ እየበረታ ሲመጣ የቤትም የአዕምሮ ጤናዋ እየተባባሰ መጣ።

Bottom line for Get in touch request