በሩስያ ጦር በተከበበው ብረት ፋብሪካ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩ ሲቪል ሰዎች መውጣታቸው ተገለጸ

በፋብሪካው ተሸሽገው የነበሩ ግለሰቦች ሲወጡ

የፎቶው ባለመብት, EPA

በዩክሬን ማሪዮፖል ከተማ በሩሲያ ጦር በተከበበው የአዞቭስታል ብረት ፍብሪካ ውስጥ ተሸሽገው የነበሩ አዛውንቶች፣ ሴቶችና ህጻናት ፍብሪካውን ለቀው መውጣታቸውን ሩሲያና ዩክሬን አስታውቀዋል።

እነዚህን ሰዎች ከፋብሪካው በሰላም የወጡት ከሳምት በፊት የተባበሩት መንግስታት ድርጅት እና ዓለምአቀፉ የቀይ መስቀል ማህበር በጥምረት ባከናወኑት ተልዕኮ ሳይሆን እንዳልቀረ ተገምቷል።

ፋብሪካው በማሪዮፖል ከተማ በሩሲያ ቁጥጥር ስር ያልገባ ብቸኛው አከባቢ ሲሆን የዩክሬን ሃይሎች እጅ ለመሰጥት አሻፈረኝ ብለዋል።

ሩሲያ ፍብሪካውን ለሳምንታት የከበበበችው ሲሆን አዞቭ ተብሎ በሚጠራው ባታሊዮን አባላት እጅ እንዲሰጡ እያሳሰበች ትገኛለች።

ሲቪል ሰዎቹ ከየትኛው አከባቢ እንደወጡ ግልጽ ባይሆንም የዩክሬን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ኢርያና ቬርሴቺኮ የሰብአዊነት ዘመቻው ተጠናቋል ብለዋል።

ከዚህ በፊት በነበረው ልምድ ከተለያዩ አከባቢዎች የወጡ ሰዎች በዩክሬን ቁጥጥር ስር ወደሚገኝ ከተማ ለመውሰድ ቀናትን ይፈጃል።

የዩክሬኑ ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ከፋብሪካው 300 ሲቪል ሰዎች ከፋብሪካው በሰላም መውጣታቸውን ሲገልጹ የሩሲያ መከላከያ ሚኒስቴር ግን የወጡት ሰዎች 51 ናቸው ብሏል።

ዜሌንስኪ ከማሪዮፖል ወታደሮችን ለማስወጣት የዲፕሎማሲ ጥረቱ እንደቀጣለም ተናግረዋል።

የማሪዮፖል ሙሉ በሙሉ በቁጥጥሯ ስር መግባት ለሩሲያ እጅግ ወሳኝ ነው። ምክንያቱም አንድ ከአመታት በፊት የጠቀለለችው የክሪሚኒያ ግዛት እና ከዶምቦስ ጋር በየብስ ስለሚገናኝ ነው።

ሁለት የጥቁር ባህርን ዳርቻ 80 በመቶ መቆጣጠር ስለሚያስችላት ነው።

ይህንን ወሳኝ ድል ለማስመዝገብ በሩሲያ ከባድ ጦር መስሪያዎች 'እንዳልነበረች' እየሆነች ያለችው ማሪዮፖል 90 በመቶው የከተማው ክፍል ከጥቅም ውጪ ሆኗል።