ስደት፡ የአውሮፓ ሃገራትና የስደተኞች ቀውስ

ስደት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የዛሬ አምስት ዓመት ከአንድ ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ድንበር አቋርጠው ወደ አውሮፓ ገቡ።

አብዛኛዎቹ የተሻለ ሕይወት በማሰብ በአገራቸው ያለውን ጦርነትና ግጭት በመሸሽ ነው ወደ አውሮፓ የመጡት። በመንገዳቸውም እራሳቸውን ለአደጋ አጋልጠው ነው የሚጓዙት።

ነገር ግን የስደተኞቹ በድንገት መፍለስ በአውሮፓ ከፍተኛ ምስቅልቅል ፈጠረ። የሰብአዊም ፖለቲካዊም ምስቅልቅል። አንዳንድ አገራት ስደተኞቹን ለመቀበል እጃቸውን ሲዘረጉ ሌሎች ደግሞ ስደተኞቹን ለማስቀረት ድንበራቸው ላይ አጥር መገንባት ጀመሩ።

እንደ አህጉር ግን አውሮፓ የስደተⶉቹን ሁኔታ መቆጣጠር አቅቷት ተንገዳግዳ ነበር። የስደተⶉቹ በብዛት ወደ አውሮፓ መግባት ጫና አሁንም ድረስ አለ።

ላራ ታሃን ሶሪያ ውስጥ ሒሳብ አስተማሪ ነበረች። '' ከ2011 ጦርነት በፊት የነበረኝ ሕይወት በጣም ጥሩ ነበር። አሌፖ ውስጥ በሒሳብ አስተማሪነት በማገኘው ገቢ ሁለት ልጆቼን አስተዳደር ነበር። ነገር ግን ድንገት ጦርነቱ ተጀመረ'' ስትል እንዴት ለመሰደድ እንደተገደደች ታስረዳለች።

''ልክ ጦርነቱ ሲጀምር አገሬ ውስጥ ምንም ተስፋ እንደሌለኝ ተረዳሁ። በከተማው ውስጥ መኪናዬን ሳሽከረክር በየመንገዱ የሞቱ ሰዎችን ሬሳ እምለከት ነበር። ስለዚህ በወቅቱ የነበረኝ ቀላል አማራጭ ወደ ቱርክ መሄድ ነበር።''

በሶሪያ የተቀሰቀሰው የእርስ በርስ ጦርነት ቱርክን በስደተኞች ጉዳይ በዓለም አይን ውስጥ እንድትገባ አደረጋት። ከግሪክና ቡልጋሪያ ጋር በድንበር መዋሰኗ ደግሞ ወደ አውሮፓ መግባት ለሚፈልጉ ስደተኞች በጣም ተመራጭና ቀላል አማራጭ አድርጓታል።

በአውሮፓውያኑ 2015 ላይ ጦርነቱን በመሸሽ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ ሶሪያውያን ስደተኞች ወደ ቱርክ ገብተዋል።

ነገር ግን ጣልያን ውስጥ ደግሞ የስደተⶉች ጉዳይ ለዓመታት ችግር ሆኖ የቆየ ነገር ነበር። ለሰሜን አፍሪካ ቅርብ መሆኗ የሜዲተራኒያን ባህርን ለማቋረጥ ድፍረቱ ያላቸውና እስከሞት ሊያደርስ የሚችለውን የባህር ጉዞ የማያስጨንቃቸው አቅጣጫቸውን ወደ ጣልያን አድርገው ነበር።

በዚያን ዓመት ላይ በባልካን በምትገኘው ሰርቢያ ዋና ዋና ጎዳናዎች ላይ ከመካከለኛው ምስራቅ የመጡ ስደተኞችን መመልከት የተለመደ ነበር።

ላራ ሁለት እህቶቿ ጀርመን ውስጥ ነው የሚኖሩት። ወደ ቱርክ ከመጣች በኋላ ደግሞ የልጆቿ የወደፊት እጣ ፈንታ ቱርክ እንዳልሆነች ተረዳሁ ትላለች። ለዚህም ነው የተሻለ ሕይወት ፍለጋ ወደ ጀርመን ለመሄድ የወሰነችው።

በወቅቱ ጀርመን ከጦርነት የሚሸሹ ስዎችን በመቀበልና በማስተናገድ ለስደተኞች ጥሩ አገር እንደሆነች ይነገርላት ነበር። በሺዎች የሚቆጠሩ ስደተⶉች መስከረም ወር 2015 ላይ መጉረፍ ሲጀምሩ የአገሬው ዜጋ በባቡር ጣቢያ በመገኘትና ስጦታ በማዘጋጀት እንኳን ደህና መጣችሁ ብለዋቸዋል። በጣም አስገራሚ ሁኔታ ነበር።

ላራ ልክ የጀርመኗ ዋና ከተማ ሙኒክ ስትደርስ እጅግ ከባድ ዝናብ እየዘነበ ነበር። '' ለእኔ እንደዛ ኤእነት ዝናብ መመልከት በጣም አስገራሚ ነበር። በበጋ ወቅት ዝናብ ኤእቼ አላውቅም። በሌላ በኩል ስለስደተኞች ጥሩ አመለካከት ያላቸው ብዙ ሰዎችን ተዋውቄያለው'' ትላለች።

በተመሳሳይ በስዊድን የነበረው ሁኔታም ለስደተኞቹ ምቹ ነበር። አገሪቱ ለስደተኞች ምቹ ከሚባሉት መካከል ነበረች በወቅቱ። ስደተኞቹ ወደ ስዊድን ሲገቡ አንዳንድ ሰዎች እንኳን በደህና መጣችሁ ብለው ተቀብለዋቸዋል።

ሳማር ጃቢር ጆርዳን ውስጥ የኤንጂነሪንግ ምሩቅ ነው። የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እያሉ ልክ እንደ ጀርመን ሁሉ ስዊድንም ስደተኞችን ተቀብላ በአግባቡ እንደምታስተናግድ እሰሙ ነበር።

''ሕይወቴ አደጋ ላይ ስለነበረ ጆርዳንን ለቅቄ ወጣሁ። እህቴ ስዊድን ውስጥ ትኖር ስለነበር ከእሷ ጋር እንደምንገናኝ በማሰብ ነበር የወጣሁት። ልክ ስዊድን ስደርስ ከረጅም ዓመት በኋላ ነጻነት ተሰማኝ።

ጀርመን ደግሞ በወቅቱ ስደተኞቹ ወደ ድንበሯ ሲገኑ መኖሪያ ቤት እንዲያገኙ ለማድረግ ስትጥር ነበር። ነገር ግን የስደተⶉች ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ ሲመጣ ሁኔታው ከቁጥጥር ውጪና ከአቅም በላይ እየሆነ መጣ።

ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ስዊድን የሚመጡት ስደተኞችንም ቢሆን ከከተማ ራቅ ወዳሉ ስፍራዎች መወሰድ ተጀመረ። ምንም እንኳን አገሪቱ ስደተኞችን መቀበል ባታቆምም ሁኔታዎች ግን እየከበዱ መጡ።

ቀስ በቀስም 2016 ላይ ስደተⶉች በባልካን አገራት በኩል የሚገቡበት መንገድ ተዘጋ። በዚህም ምክንያት ወደ አውሮፓ የሚገቡት ስደተኞች ቁጥር መቀነስ አሳየ።

የአውሮፓ ሕብረትም ከቱርክ ጋር ስምምነት ላይ ደረሰ። ሕብረቱ ለቱርክ በቢሊየኖች የሚቆጠሩ ዶላሮችን ለመስጠትና አገሪቱ ደግሞ በተራዋ ግሪካ ደሴት የመጡ የሶሪያ ስደተኞችን ተመልሳ እንድትቀበል ተስማሙ። ይህም ስምምነት የስደተኞችን ቁጥር በእጅጉ ቀነሰው።

በጀርመን 2015 ላይ በአዲስ ዓመት ዋዜማ አንዲት ጀርመናዊት ወጣት ከሰሜን አፍሪካ በመጡ ሰዎች ጥቃት ደረሰባት። በተጨማሪም በገና ወቅት ከቱኒዚያ በመጣ አንድ ስደተኛ የተፈጸመው የሽብር ጥቃት ጀርመናውያን ለስደተኞች ያላቸውን አመለካከት ቆም ብለው እንዲያጤኑ አስገድዷቸዋል።

በስዊድንም ቢሆን ከስደተⶉች ጋር የተያያዙ ወንጀሎች የፖለቲከኞች መከራሪያ ነጥብ መሆነ ጀመሩ። የአገሪቱ ፖሊስም ቢሆን ስደተⶉች በብዛት በሚኖሩበት አካባቢ የወንጀል ቁጥር ከፍ ያለ እንደሆነ አልካደም።

ላራ ታሃን በአሁኑ ወቅት ጀርመን ውስጥ መኖር ጀምራለች። ''ሴት ልጄ ትምህርት ቤት ጥሩ ሁኔታ ላይ ነች። ሁለታችንም ጀርመንኛ በአግባቡ መናገር የቻልን ሲሆን ብዙ ጓደⶉችንም አፍርተናል''

በቱርክ ያለውም ሁኔታ በእጅጉ ተቀያይሯል። አገሪቱ ከስደተⶉች መተላለፊያነት ወደ ስደተኞች ዋነኛ ማዕከልነት ተቀይራለች። በአንዳንድ አካባቢዎች የሶሪያ ስደተⶉች ብቻ የሚኖሩባቸው መንገዶች አሉ። ሱቆቹም፣ ምግብ ቤቶቹም የሶሪያውያን ነው።

በዚህም ምክንያት በርካታ ሶሪያውያን ወደ አገራቸውም ሆነ ወደ ሌላ የአውሮፓ አገር መሄድ አይፈልጉም። ምክንያቱም አብዛኛዎቹ ቱርክ ውስጥ ተደላድለውና ቤተሰብ መስርተው መኖር ጀምረዋል፤ እንዲሁም ጥሩ የገቢ ምንጭ አላቸው።