የቀድሞ ነፃ ትግል ተፋላሚና ተዋናይ ሻድ ጋስፓርድ ልጁን ከመስጠም አድኖ ህይወቱ አለፈ

ሻድ ጋስፓርድ

የፎቶው ባለመብት, Paul Archuleta

በኢንተርቴይንመንቱ ዘርፍ ከፍተኛ ስፍራ የሚሰጠው የነፃ ትግል ፍልሚያ 'ወርልድ ረስሊንግ ኢንተርቴይንመት የቀድሞ ተፋላሚና ኮከብ የነበረው ሻድ ጋስፓርድ አስከሬን በሎስ አንጀለስ በሚገኘው ቬኒስ የባህር ዳርቻ ተገኝቷል።

የ39 አመቱ ሼድ ጋስፓርድ ከአስር አመት ልጁ ጋር ከአራት ቀናት በፊት እየዋኘ በነበረበት ወቅት ባልተጠበቀ ማእበል መመታቱን ተከትሎ ለህይወት አዳኞቹ ለልጁ ቅድሚያ ሰጥተው እንዲያድኑት መናገሩን ተከትሎ ልጁ መትረፍ ችሏል።

የህይወት አዳኞቹ ልጁን ቢያድኑም ሼድ ግን በመስጠሙ በተጨማሪም ለቀናት ያህልም አስከሬኑ ሊገኝ አልቻለም ነበር።

"ሻድ በውቅያኖሱ ሰጠመ ነገር ግን ልጁን መጀመሪያ እንዲያድኑት ለህይወት አዳኞቹ ትእዛዝ ሰጥቶ ነው። ይህ ነው የአባት ፍቅር" በማለት ታዋቂው ተዋናይ ድዋይን ጆንሰን ወይም ዘሮክ ፅፏል።

የ Instagram ይዘትን ይለፉት, 1
ይዘቱን Instagram ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በInstagram. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የInstagram ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ Instagram ይዘት መጨረሻ, 1

አክሎም ሻድ "ታላቅ ሰው ነበር። ለባለቤቱ፣ ለልጁ እንዲሁም ለቤተሰቡ ያለኝን ጥልቅ ሐዘን መግለፅ እፈልጋለሁ። ያፅናቸው። ሞቱ ያማል" ብሏል።

የተዋናዩ ባለቤት ሲሊያናም የባለቤቷ አስከሬን ከመገኘቱ በፊት ልጇን ያዳኑትን አካላት አመስግናም ባሏም ፍለጋ ላይ ተስፋ እንዳላት ገልፃ ነበር። "ሻድ ታጋይ፣ ብርቱና ድንቅ ነፍስ ያለው ሰው ነው። በሰላም እንደሚገኝም ተስፋችን ነው፤ ፀሎትም እያደረግን ነው" ብላለች።

የ Instagram ይዘትን ይለፉት, 2
ይዘቱን Instagram ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በInstagram. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የInstagram ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ Instagram ይዘት መጨረሻ, 2

ሆኖም በትናንትናው ዕለት በቬኒስ ባህር ዳርቻው ላይ ህይወት አዳኞች አስከሬን ማግኘታቸውን ሪፖርት መደረጉን ተከትሎ የሻድ መሆኑም ተረጋግጧል።

"በአለም ላይ ላሉ የሻድ ጋስፓርድ አድናቂዎች ጋር በመሆን ሻድ የሚገርም ተሰጥኦ ያለው እንዲሁም ድንቅ አባት መሆኑን ልንዘክረው እንፈልጋለን" በማለት ሌላኛው የትግል ተፋላሚ ትሪፕል ኤች ገልጿል።

የ X ይዘትን ይለፉት
ይዘቱን X ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ X ይዘት መጨረሻ

የ Instagram ይዘትን ይለፉት, 3
ይዘቱን Instagram ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በInstagram. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የInstagram ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ Instagram ይዘት መጨረሻ, 3

"የሻድ መጨረሻ መሆኑን መስማት አንፈልግም ነበር። ቢሆንም ያለውን ተቀብለን እሱን በማጣታችን እናዝናለን እናም ህይወቱን እንዲሁም ድንቅ አባትነቱን እንዘክራለን" በማለት ሌላኛው ተፋላሚ ታይረስ ፅፏል ።

አክሎም "የአባትነት ትርጉሙ አንተ ነህ። ህይወትን ልጅህን ለማዳን መስዋዕት የሆንከው" ብሏል።

ከነፃ የትግል ተፋላሚነቱ ከአስር አመት በፊት ከተሰናበተ በኋላ በተለያዩ ፊልሞች ላይ ተውኗል። ከነዚህም መካከል በጎርጎሳውያኑ 2015 ከኬቪን ሃርትና ዊል ፌረል ጋር የተወነበት ጌት ሃርድ ይጠቀሳል።

ዝነኛው የነፃ ትግል ተፋላሚው ዴቭ ባውቲሳ ስለ ሻድ በሚናገርበት ወቅት እያለቀሰም ነበር "ከህይወት በላይ ታላቅ ነበር" ብሏል።

የ Instagram ይዘትን ይለፉት, 4
ይዘቱን Instagram ይፈቅዳሉ?

ይህ ጽሑፍ በInstagram. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የInstagram ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።

ማሳሰቢያ፡ የሦስተኛ ወገን ይዘቶች ማስታወቂያ ሊኖራቸው ይችላል

የ Instagram ይዘት መጨረሻ, 4

ዴቭ ሻድን ያየው ለመጨረሻ ጊዜ በኤምቲቪ የሙዚቃ ሽልማት ላይ ሲሆን "የተለያየ ፈልሞች ላይ በመተወን ስሙን እየተከለ ነበር። አሁን የለም፣ ሄዷል። ህልሞቹንም ማሳካት አይችልም" ካለ በኋላ

"ሁላችንም ቢሆን ከህይወቱ ጉዞ እንዲሁም ለልጁ ከከፈለው መስዋዕትነት ልንማር ይገባልም"ብሏል