ሙሽሪት በሰርጓ ቀን ዋዜማ ጉድጓድ ውስጥ ገብታ ሞተች

የፎቶው ባለመብት, Fauziyya Kabir Tukur/BBC
በሰሜን ናይጄሪያ ፋቲማ አቡባካር የተባለች የ16 ዓመት ሙሽራ ድንገት ጉድጓድ ውስጥ ገብታ ሞታለች።
የፋቲማ አቡበከር ሰርጓ ሐሙስ ለታ ነበር። ከሰርጉ ቀን በፊት በነበረ ዝግጅት ነው ድንገት ጉድጓድ ውስጥ የገባቸው።
አባቷ ለቢቢሲ እንደተናገሩት ረቡዕ ለታ ፈቲማ በአክስቷ ቤት ግቢ በነበረ ጉድጓድ በቅርበት ቆማ ነበር።
"ልጄ በሰርጓ እጅግ ተደስታ ነበር። ትጫወትና ትስቅ ነበር ከጓደኞቿ። ከእጮኛዋ ጋርም እጅግ ይዋደዱ ነበር" ብለዋል።
ሙሽራው ለጊዜው በሐዘን ምክንያት ጤናው ተቃውሶ መናገር አቅቶታል።
የሟች ፋጢማ አባት ለቢቢሲ እንደተናገሩት ለሰርግ የጣሉት ድንኳን ለለቅሶ እንዲሆን ሆኗል።












