በደቡብ ወሎ በጫጉላ ሥነ ሥርዓት ላይ የፈነዳው ቦምብ ሙሽራውን ገደለ የሚሉና ሌሎችም

አበባ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ኢትዮጵያ

በደቡብ ወሎ ዞን ቦረና ወረዳ በጫጉላ ሥነ ሥርዓት ላይ በፈነዳ ቦምብ የሰዎች ሕይወት ማለፉንየኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት ዘገበ።

ሙሽሮቹ ጫጉላ ውስጥ ሆነው ከሚዜዎቻቸው ጋርሲጫዎቹ አደጋው የተከሰተ ሲሆን ሙሽራውን ጨምሮ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ፖሊስ አስታወቋል።

***

የጊኒ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር አልፋ ኮንዴ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት ለማድረግ ነገ አዲስ አበባ እንደሚገቡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ፕሬዚደንቱ ከነገ ጀምሮ የ3 ቀናት ጉብኝት እንደሚያደርጉ የተገለፀ ሲሆን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ ጋር በሁለትዮሽ ግንኙነት እና በአህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ጂቡቲ

ባሳለፍነው ሳምንት በጂቡቲ የባህር ዳርቻ በተገለበጡ ሁለት ጀልባዎች ሕይወታቸው ካለፈው 58 ሰዎች 57ቱ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ጀልባዎቹ ከጂቡቲ ወደ የመን ለመሄድ ብዙ ርቀት ሳይጓዙ ነበር የመገልበጥ አደጋው ያጋጠማቸው።

መካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ

የመካከለኛው አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት ፎስቲን ቶደራ ከ14 የአማፂያን ቡድኖች ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱ ከአንድ ሚሊየን በላይ ሰዎች እንዲፈናቀሉ ምክንያት የሆነውን ላለፉት 6 ዓመታት የነበረውን ግጭት ለማስቆም ያለመ ነው።

የፊርማ ሥነ ስርዓቱ በሱዳን መዲና ካርቱም ፕሬዚዳንት ኦማር ሀሰን አልበሽር በተገኙበት ተከናውኗል።

ዚምባብዌ

የዚምባብዌ ፍርድ ቤት የኤች ኤይ ቪ የሚፈውስ መድሃኒት አለኝ በማለት ያልተረጋገጠ መድሃኒት ሲሸጥ የነበረው ሰባኪ ላይ የ700 ዶላር ቅጣት አስተላለፈ።

ሰባኪው ዋልተር ማጋያ የመድሃኒት ቁጥጥር ደንብን በመተላለፍ መድሃኒቱን በመሸጣቸው፤ ባለፈው ህዳር ወር ነበር በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋሉት።

በዚምባብዌ 1.3 ሚሊዮን ሰዎች ቫይረሱ በደማቸው ይገኛል።

ማሌዥያ

ሁለት ሩሲያዊን ማሌዢያ ጎዳና ላይ የህጻን ልጃቸውን እግር በማንጠልጠል ወደ አየር ላይ እየወረወሩ በፈጸሙት ትርኢት በፖሊስ ተያዙ።

ጥንዶቹ በአራት ዓመቷ ሴት ልቻቸው ላይ ፈጸሙት በተባለው ማንገላታት ምርመራ እንደተረገባቸው ፖሊስ ተናግሯል።

ፈረንሳይ

በፓሪስ በህንፃ ላይ በተነሳ እሳት አንድ ህፃንን ጨምሮ 10 ሰዎች መሞታቸውን የአገሪቱ የእሳት አደጋ መከላከል ባለስልጣናት ገለፁ።

6 የእሳት አደጋ ሰራተኞችን ጨምሮ ከ30 የሚበልጡ ሰዎች ጉዳት ያጋጠማቸው ሲሆን 50 የሚሆኑ ሰዎች ከህንፃው መውታት መቻላቸውም ታውቋል።

ፖሊስ አሳቱ ሆን ተብሎ ሳይነሳ አይቀርም በሚል አንዲት ተጠርጣሪን በቁጥትር ስር አውሏል።

ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሚኒስትሮቿ እስከ ህይወታቸው መጨረሻ ደመወዝና ሌሎች ጥቅማ ጥቅሞች የሚያስገኛቸውን ህግ አፀደቀች።

በዚህም መሰረት የቀድሞ ሚኒስትሮች 2ሺ ዶላር (አምሳ ስድስት ሺ ብር) ደመወዝ በየወሩ ይከፈላቸዋል።

በዛሬው ዕለት መንግሥት ባወጣው መግለጫ ክፍያው የባለስልጣኖቹን ኃብት ለማካበት ታስቦ እንዳልሆነ ተገልጿል።

ጃፓን

የጃፓኑ ምክትል ሚኒስተር ታሮ አሶ ለጃፓን የውልደት መጠን መቀነስ የእድሜ ባለፀጎችን ተወቃሽ ማድረግ እንደማይገባ ተናገሩ።

የ78 ዓመቱ ሚኒስትር የእድሜ ባለፀጎችን ከአገሪቱ ኢኮኖሚና የህክምና ወጭ ጋር ማያያዝ ተገቢ አይደለም ይልቁኑ ልጅ የማይወልዱት ናቸው ጥፋተኛ ብለዋል።

የባለፈው ዓመት መረጃ እንደሚያሳየው በጃፓን የውልደት መጠን በ448 ሺህ ቀንሷል።

እንግሊዝ

በእስላማዊ ታጣቂ ቡድን የተያዘው እንግሊዛዊ አምባሳደር በሕይወት ሳይኖር አይቀርም ሲሉ የእንግሊዝ የደህንነት ሚኒስትር አስታወቁ።

የፎቶግራፍ ጋዜጠኛው ጆን ካንትሌ ከዛሬ ስድስት ዓመት በፊት በእስላማዊ ቡድን ተጠልፎ ያመለጠ ቢሆንም ከወራቶች በኋላ እንደገና ሊያዝ ችሏል።

ሚኒስትሩ ይህን ዜና ያበሰሩት እስላማዊ ቡድኑ ከሁለት ዓመት በፊት ባሰራጨው ተንቀሳቃሽ ምስል ላይ መታየቱን ተከትሎ ነው።