በቴክሳስ በደረሰ ጅምላ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ሞተዋል

ቴክሳስ ግዛት ውስጥ በደረሰ ጅምላ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች ሞተዋል

የፎቶው ባለመብት, AFP

ዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ በቴክሳስ ግዛት በደረሰ ጅምላ ጥቃት ቢያንስ አምስት ሰዎች እንደተደገሉ ታውቋል።

በግዛቲቱ በአንድ ወር ውስጥ ለሁለተኛ ጎዜ በተከሰተው የጅምላ መሣሪያ ታጥቆ ያገኘው ሰው ላይ እየተኮሰ የነበረውን ታጣቂ በማስቆም ላይ ሳለ ተመትቶ መውደቁ ተነግሯል።

ታጣቂው መኪናው ውስጥ ሳለ ነበር መንገደኞች እና ሞተር ብስክሌተኞች ላይ ይተኩስ የነበረው። ከዚያም አንድ መኪና ሰርቆ ጥቃቱን አጠናከረ። በዚህ መሃል አንድ ፖሊስ በተኮሰው ጥይት ተመትቶ ሊሞት ችሏል።

በ30ዎቹ አጋማሽ ላይ እንደሚገኝ የተነገረለት ነጭ የጅምላ ጥቃት አድራሽ ለምን ጥቃቱን እንዳደረሰ እስካሁን አልታወቀም።

ከአራት ሳምንታት በፊት እንዲሁ ቴክሳስ ግዛት ውስጥ ኤል ፓሶ በተሰኘች ከተማ አንድ ጅምላ ገዳይ የ22 ሰዎችን ሕይወት መቅጠፉ አይዘነጋም።

ጥቃት አድራሹ ምሽት 4፡00 ሰዓት ገደማ መሃል መንገድ መኪናው ውስጥ ሳለ ፖሊሶች ሲያስቆሙት ነው መተኮስ የጀመረው ተብሏል።

በትላንትናው ጥቃት ቢያንስ 20 ሰዎች ቆስለዋል፤ ከእነዚሀም ውስጥ ሶስቱ አባሎቼ ናቸው ብሏል ፖሊስ። ነገር ግን ሁሉም ተጎጂዎቹ በጥይት የተመቱ ሳይሆኑ ጥቃቱን ለማምለጥ ሲሞክሩ የተጎዱም አሉበት ሲል የከተማዋ ፖሊስ አክሏል።

የኦዴሳ ከተማ ሆስፒታል ከተጎጂዎቹ መካከል የሁለት ዓመት ሕፃን እንደሚገኝ አሳውቆ 7 ሰዎች በሞት እና ሕይወት መካከል ናቸው ብሏል።