የማንቸስተር ደርቢ እና የሌሎች የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ቤንጃሚን ሼሽኮ እና ኧርሊንግ ሀላንድ

197ኛው የማንቸስተር ደርቢ ኢትሃድ ላይ በሲቲ እና በዩናይትድ መካከል ይከናወናል።

"ይህንን ጨዋታ ለመገመት በጣም ከባድ የሚያደርጉ ብዙ ምክንያቶች አሉ" ይላል የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን።

"ማንቸስተር ዩናይትድ ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በፊት በርንሌይን ማሸነፉ ሊያነሳሳው ቢችልም ግን ማንቸስተር ሲቲ ከብራይተን ጋር ያደረገውን ጨዋታ ስመለከት ጥርጣሬ ገብቶኛል" ይላል።

ለመሆኑ ደርቢውን ማን በአሸናፊነት ያጠናቅቃል?

ሱተን ይህንን ጨምሮ የሳምንቱን ጨዋታዎች እንደሚከተለው ገምቷል።

ቅዳሜ

አርሰናል ከኖቲንግሀም

አርሴናል ከ ኖቲንግሃም ፎረስት

አንጅ ፖስትኮግሉ በመጀመሪያው የፎረስት ጨዋታቸው ብዙ ነገር ይለውጣሉ ብዬ አልጠብቅም።

በማጥቃት ላይ የተመሰረተ አጨዋወትን ቢመርጡም ከጎላቸው ርቀው የሚከላከሉበትን መንገድ በመጀመሪያው ጨዋታቸው የሚከውኑት አይመስለም።

አርሰናል ቡካዮ ሳካን፣ ዊሊያን ሳሊባን እና ካይ ሃቨርትዝን በጉዳት ቢያጣም እነሱን የሚተኩ ተጫዋቾች አሉት።

መድፈኞቹ ሊከብዳቸው ቢችልም ጨዋታውነ በአሸናፊነት ያጠናቅቃሉ።

ግምት፡ 2 - 0

ቦርንመዝ ከ ብራይተን

ሁለቱም ቡድኖች ከዓለም አቀፍ ጨዋታዎች በፊት ማሸነፍ ችለዋል።

ቦርንመዝ ቶተንሃምን ሲያሸነፍ ብራይተን ደግሞ ማንቸስተር ሲቲን መርታት ችሏል።

ባለፈው ዓመት ብራይተን በሜዳውም ከሜዳው ውጭም 2 ለ 1 አሸንፏል።

በዚህ ጨዋታ ቦርንመዝ ተመሳሳይ ውጤት ያስመዘግባል ብዬ አላስብም።

ግምት፡ 1 - 1

ክሪስታል ፓላስ ከ ሰንደርላንድ

ማርክ ጉየ ወደ ሊቨርፑል አለመዘዋወሩ ለፓላስ ጥሩ የሚባል ዜና ነው።

ተጫዋቹም የዝውውሩን ወቅት በመልካም መንገድ አሳልፏል።

የፓላሶቹ አዳም ዋርተን እና ኢስማኢላ ሳር በጉዳት ባይሰለፉም አሰልጣኝ ኦሊቨር ሳር ቡድናቸውን በደንብ ማዋቀር ይችሉበታል።

ሰንደርላንድ የመጀመሪያዎቹን ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ ችለዋል።

ከሜዳ ውጭ ለማሸነፍ ግን ገና ናቸው።

ግምት፡ 1 - 0

ኤቨርተን ከኒውካስል

ኤቨርተን ከ አስቶን ቪላ

ወደ ድንቅ አቋሙ በመመለስ ላይ የሚገኘው ጃክ ግሪሊሽ የቀድሞ ክለቡን ይገጥማል።

ግሪሊሽ እና ኢሊማን ንዳዬ ኤቨርተን ድንቅ የማጥቃት አንቅስቃሴ እንዲያደርግ እያገዙ ላይ ይገኛሉ።

ከአቋም አንጻር ኤቨርተን ጨዋታውን ያሸንፋል ማለት ቢቻልም ቪላ መሸነፉን አይቀጥልም።

ቪላ በጥሩ አቋም ላይ አይገኘም። አዳዲስ ተጫዋቾችንም ባለቀ ሰዓት አስፈርሟል። ቡድኑ ወደ ጥሩ አቋሙ መመለሱ አይቀርም።

ግምት፡ 1 - 1

ፉልሃም ከ ሊድስ

የሁለቱን ቡድኖች ተጫዋቾች እርስ በእርስ ማወዳደር አስፈላጊ ነው።

ፉልማ ከቼልሲ ባደረገው ጨዋታ በተሰጡት ውሳኔዎች ዕድለኛ አልነበረም።

ሊድስ የተቀናቃኙን ያህል ጥልቀት ያለው ቡድን የለውም።

ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት ጨዋታ ቢሆንም ውጤቱ የተለየ አይሆንም።

ግምት፡ 2 - 0

ኒውካስል ከ ዎልቭ

ሁሉቱም ቡድኖች እስካሁን ማሸነፍ አልቻሉም።

ኒውካስል ሁለት ጊዜ አቻ ወጥቶ በሊቨርፑል ተሸንፏል።

አሌክሳንድር ኢሳቅን በመሸኘት አዲስ የፈረሙት ኒክ ዎልሜድ እና ዮዋን ዊሳ ከቡድኑ ጋር የሚፈጥሩት ቅንጅት ይጠበቃል።

በየርገን ስትራንድ የሚመራው የዎልቭስ አጥቂ መስመር ጠንካራ መሆኑን አሳይቷል።

ግምት፡ 3 - 1

ዌስት ሃም ከ ቶተንሃም

ዌስት ሃም ወደ ኖቲንግሃም አቅንቶ 3 ለምንም ያሸንፋል ብዬ አልገመትኩም ነበር።

ቡድኑ በዚሁ መቀጠል ቢኖርበተም የሚያሳካው አይመስለኝም።

ቶተንሃም በሜዳው በበርንመዝ ከተሸነፈ በኋላ ጥንካሬውን ማስመስከር ይኖርበታል።

የቶማስ ፍራንክ ቡድን ሚዛኑን የጠበቀ ሲሆን ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 2

ብሬንትፎርድ ከ ቼልሲ

ብሬንትፎርድ ከ ቼልሲ

ብሬንትፎርድ በሰንደርላንድ መሸነፉ ለቡድኑም የሚዋጥ አይመስልም።

ቀጥሎ ደግሞ ቪላን አሸነፉ።

ቼልሲ ካለው አጀማመር እና ከቡድኑ አንጻር በቀላሉ ሊያሸንፍ ይችላል ቢባልም ብሬንትፎርድ ጠንካራ ተፎካካሪ ይሆናል።

ሁለቱ ቡድኖች ባለፉት ሦስት ጨዋታዎች አቻ ተለያይተዋል።

ግምት፡ 1 - 1

እሑድ

በርንሌይ ከ ሊቨርፑል

ኢሳቅ በዚህ ጨዋታ በቋሚነት የሚሰለፍ አይመስለኝም።

ሊቨርፑል ለማሸነፍ የተጫዋቹን መሰለፍ የሚጠብቅበት ጨዋታም አይሆንም።

በርንሌይ ከማንቸስተር ዩናይትድ ጋር እንዳደረገው ተጋጣሚውን እንዳይንቀሳቀስ ለማድረግ ይሞክራል።

የአርን ስሎት ቡድን ወደ ጥሩ አቋሙ መድረስ ባይችልም ሦስቱንም ጨዋታዎቹን ማሸነፍ ችሏል።

ይህ ደግሞ ለቡድኑ ጥሩ ስሜትን የሚፈጠር ሲሆን ለተጋጣሚዎች ደግሞ አስጊ ይሆናል።

ግምት፡ 0 - 3

ዩናይትድ ከሲቲ

ማንቸስተር ሲቲ ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ብሪያን ምቡሞ በመልሶ ማጥቃት ሲቲን ሊቀጣ የሚችል ሲሆን የሲቲው ግብ ጠባቂ ጀምስ ትራፎርድ አስተማማኝ አይደለም።

ዩናይትድ ጎል ማስቆጠር ቢችልም ሲቲ በሜዳው በርካታ ዕድሎችን ይፈጥራል።

ሲቲ ከመጀመሪያዎቹ ሦስት ጨዋታዎች ሁለቱን ተሸንፏል። በሻምፒዮንስ ሊግ በቀጣይ ሳምንት አጋማሽ ናፖሊን ቀጥሎ ደግሞ አርሰናልን ይገጥማል።

አዲስ ፈራሚው ግብ ጠባቂ ጂያንሉጂ ዶናሩማ በቋሚነት ከተሰለፈ ቡድኑ ይሻሻላል።

ዩናይትድም በተመሳሳይ ቦታ ላይ ክፍተት አለበት።

ዩናይትድ ያስፈረመው ግብ ጠባቂው ሴኔ ላመንስ ያለው አቋም እና በሊጉ የሚኖረው ተጽዕኖ ተጠባቂ ነው።

ግምት፡ 2 - 1