የህንድ ፍርድ ቤት በትዳር ውስጥ ያለ መደፈርን በወንጀልነት ለመፈረጅ ተከፋፍሏል

መደፈር ይቁም የሚል አርማ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የህንድ ፍርድ ቤት በትዳር ውስጥ ያለ መደፈርን ወንጀል ለማድረግ በቀረበው ብያኔ ላይ ሁለት ዳኞች ተቃውሞ ማሰማታቸውን ተከትሎ የመጨረሻ ውሳኔ ማስተላለፍ አልተቻለም ተብሏል።

አንደኛው ዳኛ እንደ መከራከሪያ ያቀረቡት ሃሳብ ብሪታንያ ህንድን ትገዛ በነበረበት ወቅት የነበረውን ህግ ጠቅሰው ወንድ በትዳሩ ውስጥ ቢደፍር ሊከሰስ አይችልም በሚልም የቀረበውን ሃሳብ ነቅፈውታል።

ሁለተኛውን ተቃውሞ ያቀረቡት ዳኛ በበኩላቸው አንድ ግለሰብ ለአካለ መጠን ያልደረሰች ከሆነ በስተቀር ከሚስቱ ጋር የሚያደርገው ግንኙነት መድፈር አይደለም የሚለውን የህንድ የወንጀለኛ መቅጫ ህግ አንቀፅ 375 ለማሻሻል ፈቃደኛ አልሆኑም።

ጉዳዪ በአሁኑ ወቅት ወደ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ ይጠየቅበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ረቡዕ ዕለት በደልሂ ከፍተኛ ፍርድ ቤት የተላለፈው ውሳኔ ከአውሮፓውያኑ 1860 ጀምሮ የነበረው ይህ ህግ እንዲለወጥ ዘመቻ ሲያደርጉ የነበሩ ፌሚኒስት ተሟጋቾችን አሳዝኗል ተብሏል።

ባለፉት አመታተት ከ100 በላይ አገራት በትዳር ውስጥ መደፈርን ወንጀል አድርገውታል። ብሪታንያ ህጓን የቀየረችው በአውሮፓውያኑ 1991 ነው።

ነገር ግን ይህ ህግ እንደ ህንድ ባሉ ሃገራት አይነኬ ሆኖ መቀጠል አለበት በማለት የሚከራከሩ አሉ።

ለዚህም የሚያነሱት ሃሳብ በጋብቻ ውስጥ የሚፈጸም ማንኛውም ወሲብ ፈቃደኝነት የተሞላበትና ሚስት እምቢተኝነቷን ማሳየት አትችልም የሚልም ነው።

ተሟጋቾች በበኩላቸው ያለ ፈቃድ የሚፈጸም ወሲብ ማንም አደረገው ማን መድፈር ነው ይላሉ።

ነገር ግን የህንድ መንግሥት እና የሃይማኖት ቡድኖች ጋብቻ በህንድ ውስጥ የተቀደሰ ነው በማለት አቤቱታውን ለዓመታት ተቃውመውታል።