አልጄሪያ ለሥራ አጦች ወርሃዊ ክፍያ ልትሰጥ ነው

የፎቶው ባለመብት, AFP
ከፍተኛ የሥራ እጦት ባለባት አልጄሪያ መንግስት ለወጣቶች የሥራ አጥነት ድጎማ እንደሚጀምር ፕሬዝዳንቱ ተናገሩ።
ፕሬዝዳንት አብደልማጂድ ተቡን ለጋዜጠኞች እንደተናገሩት ከ19 እስከ 40 ዓመት ለሆናቸው ሥራ ፈላጊዎች ከመጋቢት ጀምሮ ወርሃዊ ክፍያ ያገኛሉ።
ለክፍያው ብቁ የሆኑ ዜጎች ሥራ እስኪያገኙ ድረስ በወር ወደ 100 ዶላር የሚጠጋ ክፍያ እና አንዳንድ የሕክምና ጥቅማጥቅሞችን ያገኛሉ።
ተቡን አክለውም ይህን መሰሉን ጥቅማ ጥቅም በማስተዋወቅ ከአውሮፓ ውጪ አልጄሪያ የመጀመሪያዋ ሀገር መሆኗን አስታውቀዋል።
በአልጄሪያ ከ600 ሺህ በላይ ስራ አጦች እንዳሉም አክለዋል።








