ኮሮናቫይረስ፡ ቻይና የኮቪድ-19 ክትባት ለሕዝብ እንዲሰጥ ፈቀደች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የቻይና ባለሥልጣናት ቻይናዊው መድሃኒት አምራች ሲኖፋርም ያበለፀገውን የኮቪድ-19 ክትባት ቅድመ ሁኔታ በማስቀመጥ ፈቃድ ሰጡ።
ባለሥልጣናቱ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሱት ድርጅቱ በሶስተኛ ደረጃ ሙከራው ክትባቱ 79 በመቶ ውጤታማ መሆኑን አረጋግጫለሁ ካለ በኋላ ነው።
በቻይና በርካታ በሙከራ ላይ ያሉ የኮሮናቫይረስ ክትባቶች ለአስቸኳይ ጊዜ በሚል ፈቃድ ከተሰጣቸው በኋላ ጥቅም ላይ እየዋሉ ነው።
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ባለፈው ዓመት ሕዳር ወር መጨረሻ ላይ ከቻይናዋ ዉሃን ከተማ መነሳቱ ይታመናል። ከዚያ በኋላ በመላው ዓለም የተዛመተው የተህዋሲው ወረርሽኝ ሚሊዮኖችን ለሞት ዳርጓል።
የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን መነሻ ለማወቅ የሚደረገው ጥረት ቻይናን ከምዕራባውያን ጋር ፍጥጫ ውስጥ ጥሏትቆይቷል።
አሜሪካ እና ሌሎች በርካታ አገራት ቻይና ተህዋሲው በመጀመሪያ እዚያ ሲገኝ በነበሩ መረጃዎች ላይ ሙሉ በሙሉ ግልጽነበረች ወይ ሲሉ ይጠይቃሉ።
ቻይና ስለመዳህኒቱ ምን አለች?
ሐሙስ እለት የቻይና መድሃኒት አምራች ኩባንያ ሲኖፋርም ያበለፀገውን ክትባት በዓለማችን ከፍተኛ ቁጥር ያለውሕዝብ ለመከተብ አንድ እርምጃ ወደፊት ነው ብለው ነበር።
በሐምሌ ወር ቻይና ሶስት የተለያዩ ክትባቶችን ለቁልፍ ሰራተኞች እንዲሁም ከፍተኛ ተጋላጭነት ላላቸው ሰዎች ለአስቸኳይ ጊዜ ጥቅም ላይ እንዲውሉ በሚል ፈቃድ ሰጥታ ነበር።
ይህ ክትባት እስካሁን ድረስም 4.5 ሚሊዮን ክትባት ጥቅም ላይ ውሏል።
ቻይና እስከ የካቲት ወር አጋማሽ ድረስ በአስር ሚሊዮኖች የሚቆጠር ሕዝቧን ለመከተብ እቅድ ይዛ እየሰራች ነው።
ሲኖፋርም እንዲሁ ሌላ ሁለተኛ ክትባት እያበለፀገ ሲሆን፣ ሌሎች በርካታ ክትባቶችም እየተመረቱ ነው።
አንዳንድ ባለሙያዎች ግን ለሲኖፋርም የተሰጠውን ፈቃድ በጥርጣሬ እያዩት ነው።
ለዚህም አንዱ ምክንያታቸው በሙከራው ወቅት የተገኙ መረጃዎች ለሕዝብ ይፋ አለመሆናቸው ነው።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
በቻይና ወይንም ደግሞ በሩሲያ የተሰሩ ክትባቶች ላይ አስተያየት ለመስጠት፣ ስለጥናትና ምርመሩ በዓለም ደረጃበሚታወቁ ሕክምና ጆርናሎች ላይ የተጻፈ አልያም በመንግሥት የቀረበ እና ሂደቱን የሚያሳይ መረጃ በሌለበት፣ ከባድመሆኑን እየተናገሩ ነው።
እነዚሁ ባለሙያዎች አንድን መድሃኒት በአምራቹ ኩባንያ አስተየየት ላይ ብቻ ተመስርቶ መመዘን ጦስ እንደሚኖረውምያሰምሩበታል።
የኮሮናቫይረስን ባለበት ለማቆም ከ60 እስከ 70 በመቶ የሚሆነው የዓለም ሕዝብ መከተብ ይኖርበታል ሲሉ ባለሙያዎችይመክራሉ።
ምዕራባውያን ፋይዘር ፣ባዮንቴክ እና ሞደርና ውጤታማነቱ 95 በመቶ እና 94 በመቶ የሆኑ ክትባቶችን አምርተውበመጠቀም ላይ ናቸው።
በኦክስፎርድ ዩኒቨርስቲ የተመረተው አስትራዜንካ ደግሞ በትናንትናው ዕለት በዩናይትድ ኪንግደም ጥቅም ላይ መዋልእንደሚችል የተፈቀደ ሲሆን፣ ይህም ክትባት 70 በመቶ ሰዎች የኮቪድ-19 ምልክት እንዳያሳዩ ማድረግ ይችላል ተብሏል።
ቻይና ያመረተችውን መድሃኒት ለድሃ አገራት ተመጣጣኝ በሆነ ዋጋ ለመስጠት ቃል ገብታለች።
በዚህ ወር መጀመሪያ ላይም፣ የተባበሩት አረብ ኤሜሬትስ ሲኖፋርም ያመረተውን እና ውጤታማነቱ 68 በመቶ ነው የተባለውን ክትባት መጠቀም ጀምራለች።
ባሕሬን አዋቂ ዜጎቿ ኦንላየን ተመዝግበው ይህንኑ ክትባት በነጻ እንዲወስዱ ጥሪ አቅርባለች።
ፓኪስታን፣ ሐሙስ እለት የሲኖፋርም ክትባት በቻይና መንግሥት ፈቃድ ባገኘ በሰዓታት ውስጥ 1.2 ሚሊዮን ክትባትለመግዛት ሥምምነት ላይ ደርሳለች።
















