አሜሪካ የዓለም ንግድ ድርጅት ለመምራት የታጩትን አፍሪካዊት ልታግድ መሞከሯ ተገለፀ

ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ

የናይጄሪያ የቀድሞ የገንዘብ ሚኒስትር የዓለም ንግድ ድርጅትን እንዲመሩ መሾማቸው የአሜሪካ መቃወምን ተከትሎ ጥርጣሬ ውስጥ ወድቋል ፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅት እጩዎች ኮሚቴ ንጎዚ ኦኮንጆ-ኢዊላ እንዲሾሙ ሀሳብ ያቀረበው ረቡዕ ነበር።

የዓለም ንግድ ድርጅት የመሩ የመጀመሪያዋ ሴት እና የመጀመሪያዋ አፍሪካዊት ይሆናሉ ተብሎ ተጠብቆ ነበር ፡፡

ነገር ግን የዓለም ንግድ ድርጅት የዓለም ንግድን የመራበትን መንገድ አጥብቃ የነቀፈችው አሜሪካ ሌላ ሴት እያሰበች ነው- የደቡብ ኮሪያዋን ዮ ሚንግ ሂን፡፡

ኦኮንጆ-ኢዊላ በሹመቱ "እጅግ እንደተደሰቱ"ገልጸው ነበር፡፡

ለድርጅቱ አዲስ መሪ ለመፈለግ ለአራት ወራት የተደረገው ጉዞ ዋሺንግተን የደቡብ ኮሪያን የንግድ ሚኒስትርን እንደምትደግፍ በመናገሯ እንቅፋት አጋጠመው፡፡

የዓለም ንግድ ድርጅትን በመተቸት የአሜሪካ የንግድ ጽሕፈት ቤት ድርጅቱ "በእውነተኛ እና በመስኩ ልምድ ባለው ሰው መመራት አለበት" ብሏል ፡፡

ዮ "የድርጅቱን ውጤታማ መሪ ለመሆን የሚያስፈልጉ ብቃቶች ሁሉ አሏት" ይላል መግለጫው ፡፡

አክሎም "ይህ ለዓለም ንግድ ድርጅት እና ለዓለም ዓቀፍ ንግድ በጣም አስቸጋሪ ጊዜ ነው። በ 25 ዓመታት ውስጥ ሁለገብ የታሪፍ ድርድሮች አልተካሄዱም፤ የአለመግባባቶች መፍትሄ አሰጣጡ ሥርዓት ከቁጥጥር ውጭ ሆኗል። ግልፅነትን በተመለከተም በጣም ጥቂት አባላት ብቻ ግዴታቸውን እየተወጡ ነው፡፡ ደርጅቱ ትልቅ ለውጥ የሚያስፈልገው ነው" ብሏል።

መግለጫው ኦኮንጆ-ኢያላ አልተጠቀሰም ፡፡

የድርጅቱ ቃል አቀባዩ ኪት ሮክዌል ስለውሳኔው ላይ ለመወያየት የዓለም ንግድ ድርጅት ልዑካን ከተሰበሰቡ በኋላ አንድ አባል ሀገር ብቻ ኦኮንጆ-ኢዊላን እንዳልደገፈ ተናግረው ነበር ፡፡

"ከአንድ ልዑክ በስተቀር ሁሉም ልዑካን ለሂደቱ ... ለውጤቱ ጠንካራ ድጋፍ አድርገዋል" ብለዋል።

ፕሬዝዳንት ትራምፕ የዓለም የንግድ ድርጅትን "አስፈሪ" እና ለቻይና ያደላ አድርገው የገለጹ ሲሆን በድርጅቱ ውስጥ ቁልፍ የተባሉ አንዳንድ ሹመቶች ቀድሞውኑም ታግደዋል ፡፡

የዓለም የንግድ ድርጅት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከአሜሪካ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በኋላ ስብሰባ ጠርቷል ፡፡

የአሜሪካ መቃወም ናይጄሪያዊቷ እንዳይሾሙ ያግዳል ማለት አይደለም። ሆኖም ዋሽንግተን በውሳኔው ላይ ከፍተኛ ተጽዕኖ ማሳደር ትችላለች ፡፡

የ66 ዓመቷ ኦኮንጆ-ኢዊላ የናይጄሪያ የመጀመሪያዋ ሴት የገንዘብ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው ያገለገሉ ሲሆን በዓለም ባንክ ኢኮኖሚስት ሆነውአገልግለዋል።