በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ትርፉ መጨመሩን ሳምሰንግ አስታወቀ

የሳምሰንግ ስልክ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የኮሮናቫይረስ ወረርሽኝን ስርጭት ለመግታት የወጡት መመሪያዎችን ተከትሎ ሚሊዮኖች ከቤት ሆነው ስራቸውን ማከናወን እንዲሁም በርቀት ለመማር ተገደዋል።

ይህም ሁኔታ የኤሌክትሮኒክስ ቁሳቁሶች አምራች ለሆነው ሳምሰንግ ትርፉ እንዲጨምር ምክንያት ሆኗል።

በአለም ግዙፉ ዘመናዊ የተንቀሳቃሽ ስልክ አምራች የሆነው ሳምሰንግ ከባለፈው አመት ጋር ሲወዳዳር 23 በመቶ የትርፍ ጭማሬ ማግኘቱን አስታውቋል።

በተለይም የኮምፒውተር መቀያየሪያ ምርቶች በተለይም የኮምፒውተር መረጃዎች የማስቀመጫ ቋት ፍላጎት በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር በአለም አቀፉ ገበያም ዘንድ ዋጋውን አንሮታል።

የደቡበ ኮሪያ ኩባንያ ሳምሰንግ እንዳሳወቀው በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት ተማሪዎችና ሰራተኞች ከቤት በመስራታቸው የሚሰሩባቸውን መረጃዎችን የሚያስቀምጡበት የኮምፒውተር መተግበሪያዎች ፍላጎት አሻቅቧል። በተንቀሳቃሽ ስልኮች ላይ ያለው ፍላጎት ይህን ያህል አልጨመረም ተብሏል።

ሌሎች ኩባንያዎች እንዲሁ የኮምፒውተር መረጃ ቋት (ሜሞሪ ቺፕ) የሚያመርቱ የኮሪያው ኤስኬ ሂኒክስና የአሜሪካው ማይክሮን ቴክኖሎጂም ሰዎች በቤታቸው በመገደባቸውና ኢንተርኔትን በመጠቀም የሚያደርጓቸው ስብሰባዎችና ፊልሞች መመልከት እንደተጠቀሙና ትርፋቸው እንደጨመረ ከሰሞኑ አስታውቀዋል።

አዳዲስ የጋላክሲ ኖትና ታጣፊ የጋላክሲ ዚ ተንቀሳቃሽ ስልኮችን ለማስተዋወቅ በዝግጅት ላይ ያለው ሳምሰንግ በመጪው ወራት የስልክ ሽያጮች እንደሚያንሰራራም ግምቱን አስቀምጧል።

ምንም እንኳን በገበያው ያለው ውድድር የጠነከረ ቢሆንም ሳምሰንግ ይህንን ሰብሮ መውጣት እንደሚችል ያምናል።

በኮሮናቫይረስ ወረርሽኝ ምክንያት አዳዲስ የቴክኖሎጂ ተንቀሳቃሽ ስልክ ፍላጎት ቢቀንስም ኩባንያዎች አዳዳዲስ ምርቶቻቸውን እያስተዋወቁ ነው።

በሚያዝያ ወር አፕል አይፎን ኤስ ኢ የተባለ አዲስ ምርት ሲያስተዋውቅ ከሳምነት በፊትም የቻይናው ኩባንያ ዋን ፐላስ አዲስ ምርት አውጥቷል። ሁዋዌ ፒ40 አዲስ ስልኩን ወደ ገበያ አውጥቷል።

በዚህ አመትም አይፎን 12ና ጉግል ፒክስል 5ና 4ኤ አዳዲስ ምርቶች ለገበያ እንዲወጡ እቅድ ተይዟል።

ኮሮና