“ታይዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትገለል ቻይና ስትሞክር ቆይታለች” ታይዋን

የፎቶው ባለመብት, Reuters
የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲ በአገራቸው ያደረጉትን አወዛጋቢ ጉዞ ትክክል ነው ሲሉ ለቢቢሲ ተናግረዋል።
የናንሲ ፔሎሲን ጉብኝት ተከትሎም ቻይና በታይዋን ደሴት ዙሪያ የምታደርገውን መጠነ ሰፊ ወታደራዊ ልምምድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጆሴፍ ው አውግዘዋል።
ናንሲ ፔሎሲ በታይዋን ያደረጉት ጉብኝት “በጣም ጠቃሚ ነው” እና ቻይና እያደረገቸው ባለው “የጠብ አጫሪነት” ምላሽ ዲሞክራቶችን ወደ ታይዋን ከመጋበዝ አያስቆማቸውም ብለዋል።
የቻይና ግዛት የማስፋፋት ከታይዋን በላይ እንደሚሄድም አስጠንቅቀዋል።
ላለፉት ስድስት አመታት የታይዋኑ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጆሴፍ ው አገሪቷ ለበለጠ አለም አቀፍ እውቅና የምታደርገው ዘመቻን ሲመሩ ነበር።
የአሜሪካን የአፈ ጉባኤ ጉብኝትንም ተደራድረው ሲሆን ያመጡት በአሁኑ ወቅት ቻይና የምታደርገውን ወታደራዊ ምላሽ አስፈሪ ሁኔታም መጋፈጥ አለባቸው።
ሆኖም የታይዋን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ይቅርታ የመጠየቅ እቅድ የላቸውም። የአፈ ጉባኤዋ ጉብኝት በርካቶች የረሷት እናም ብዙም መረዳት ያላገኘችውን የታይዋን ደሴት ትኩረት እንድታገኝ ማድረግ ላይ ነው።
ቻይና ታይዋንን እንደ ተገንጣይ ግዛቷ ነው የምታያት ውሎ አድሮም እንደገና በቁጥጥሬ ስር ትሆናለችም በሚልም ነው የምታስባት።
ታይዋን በበኩሏ ራሷን እንደ ነጻ ሃገር ነው የምትመለከተው። የአለም መሪዎች ለታይዋን እውቅና መስጠታቸው ቻይናን ያስቆጣታል በቅርቡ ጉብኝት ያደረጉት የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ናንሲ ፔሎሲና ቤተሰባቸው ላይ ማዕቀብ መጣሉም በዛሬው ዕለት ታውቋል።
“ታይዋን በዓለም አቀፍ ደረጃ እንድትገለል ቻይና ስትሞክር ቆይታለች። “ ብለዋል የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ
"የአሜሪካ ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ፔሎሲ ያለ ከፍተኛ መሪ ታይዋንን መጎብኘታቸው ትልቅ ጠቀሜታ አለው። የታይዋንን ገፅታ ከፍ ለማድረግ እንዲሁም አለም አቀፉ ማህበረሰብ ታይዋን በዲሞክራሲያዊ መንገድ የምትመራ መሆኗን እንዲረዳ እድል ይፈጥራል” ብለዋል።
በአሁኑ ወቅት የተፈጠረውን ቀውስ የቀሰቀሰችው ታይዋን ሳትሆን እውነታዎችን ለመቀየር እየሞከረች ያለችው ቻይና ናት ሲሉ ወቀሳቸውን አቅርበዋል።
“ታይዋን ነጻ ሃገር ናት። ታይዋን በቻይና ላይ ስልጣን እንደሌላት ሁሉ ቻይናም በታይዋን ላይ ምንም አይነት ስልጣን የላትም። እውነታው ይህ ነው” ብለዋል።












