የአውሮፓውያን ቀን አቆጣጠርን የሚከተሉት 2023 አዲስ ዓመትን ተቀበሉ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠርን የሚከተሉት አብዛኛው የዓለማችን ክፍል አዲሱን 2023 ዓመት ተቀበሉ።
በመላው ዓለም በሚገኙ ከተሞች ነዋሪዎች በብዛት ተሰባስበው በርችት ትዕይንት አዲሱን ዓመት ተቀብለዋል።
ለንደን ከተማ 12 ደቂቃዎች ከሙዚቃ ጋር የተዋሃድ የርችት ሥነ-ስርዓት አድርጋ አዲሱን ዓመት ተቀብላለች። የከተማዋ ከንቲባ ሳዲቅ ካሃን ይህ ትዕይንት በአውሮፓ ትልቁ ነው ብለዋል።

የፎቶው ባለመብት, Reuters
ከኮቪድ ስርጭት ጋር በተያያዘ ከተጣሉ ክልከላዎች በኋላ በሰዎች ለአዲስ ዓመት አቀባበል በበርካታ ከተሞች በብዛት ሲሰባሰቡ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
ለንደን በነበረው የአዲስ ዓመት አቀባበል በሥነ-ሰርዓቱ ከ100ሺህ በላይ ሰዎች ወደ አደባባይ መውጣታቸው ተገልጿል።
በለንደኑ ርችት በሞት የተለዩት ዳግማዊት ንግሥት ኤልዛቤጥ ታውሰዋል።
የምስራቅ አፍሪካ አገራቱ ኬንያ እና ኡጋንዳም በርችት ሥነ-ስርዓት አዲሱን 2023 ተቀብለዋል። በካይሮ ግብጽ ደማቅ የርችት ስነ-ስርዓት ተከናውኗል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ዩክሬን በ2023 ትግሏን ትቀጥላለች- ዜሌንስኪ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ዩክሬን በ2023 ትግሏን ትቀጥላለች ያሉት ፕሬዝዳንት ቮሎድሚር ዜሌንስኪ ናቸው። ፕሬዝዳንቱ አገራቸው “ለየትኛም ነገር ዝግጁ ነች” ብለዋል።
በአዲስ ዓመት ዋዜማ ንግግራቸው "ይህ ዓመት የመመለስ ይሆናል” ብለዋል። “ሕዝባችን ወደ መኖሪያው የሚመለስበት፣ ወታደሮች ወደ ቤተሰቦቻቸው የሚመለሱበት፣ ስደተኞች ወደ ዩክሬን የሚመለሱበት” ይሆናል ብለዋል።
የዩክሬን መዲና ኪዬቭ ጎዳናዎች ግን እንደ ተቀሩት የአውሮፓ አገራት መዲናዎች ሰዎችን አላስተናገዱም።
ከተማዋ ከምሽት 5 ሰዓት በኋላ የእንቅስቃሴ ክልከላ ስለተጣለባት ጎናዎቿ ጭር ብለዋል።

የፎቶው ባለመብት, AFP
ፑቲን በበኩላቸው አዲሱን ዓመት ከወታደሮቻቸው ጋር ብርጭቆ እያጋጩ ተቀብለዋል።
የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያ ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በወታደሮች ተከበው በሻምፓኝ የተሞላ መጠጥ ሲያጋጩ አሳይቷል።
ያለፈው ዓመት “መልካም አጋጣሚዎችን” መፍጠራቸው እና በአዲሱ ዓመት “ሩሲያውያን እውነተኛ ነጻነትን እንቀዳጃለን” ብለዋል።
ይህ አብዛኛው የዓለማችን ክፍል የሚጠቀምበት የግሪጎሪያን ቀን አቆጣጠር በሮማው ጻጻስ ጆርጅ ስምንተኛ በ1582 የተዋወቀ ነበር።












