ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ለትራምፕ አስተዳደር 200 ሚሊዮን ዶላር ክፍያ ሊከፍል ነው

የኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ አካል የሆነው በርናርድ ኮሌጅ መግቢያ በር

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ የአይሁዳውያን ተማሪዎቹን ከጥቃት መከላከል አልቻለም በሚል ለቀረበበት ክስ ለፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ አስተዳደር 200 ሚሊዮን ዶላር ለመክፈል ተስማማ።

ዩኒቨርሲቲው ክፍያውን ለፌደራል መንግሥት በሦስት ዓመታት ጊዜ ውስጥ እንደሚከፍል ዩኒቨርሲቲው ባወጣው መግለጫ ይፋ ያደረገ ሲሆን፣ ይህንኑ በማኅበራዊ ሚዲያም ፕሬዚዳንቱ አረጋግጠዋል።

በምትኩ፣ መንግሥት በመጋቢት ወር ከከለከለው ወይም ካቋረጠው 400 የሚሊዮን የፌዴራል ዕርዳታ የተወሰነውን ለመመለስ ተስማምቷል።

ኮሎምቢያ ባለፈው ዓመት በኒውዮርክ ሲቲ ካምፓስ በእስራኤል እና በጋዛ ጦርነት በተቀሰቀሰው ተቃውሞ ፀረ ሴማዊነትን ለመግታት አልቻለም በሚል በትራምፕ አስተዳደር ዒላማ የተደረገ የመጀመሪያ የትምህርት ተቋም ነበር።

በመጋቢት ወር ከዋይት ሐውስ የሚቀርቡት ጥያቄዎች ለማሟላት ተስማምቶ ነበር።

ከኮሎምቢያ ዩኒቨርሲቲ ጋር የተደረገው ስምምነት ዩኒቨርሲቲዎችን ተጠያቂ ለማድረግ "በአገራችን በሚደረገው ትግል ውስጥ ትልቅ ለውጥ ነው" ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሯ ሊንዳ ማክማሆን ተናግረዋል።

የኮሎምቢያ ተጠባባቂ ፕሬዝዳንት ክሌር ሺፕማን በሰጡት መግለጫ "ይህ ስምምነት ቀጣይነት ያለው የፌደራል መንግሥትን ምርመራ ካለፈ በኋላ አንድ ጠቃሚ እርምጃ ወደፊት [መራመዳችንን] የሚያመለክት ነው" ብለዋል።

ኮሎምቢያ በትራምፕ አስተዳደር እስራኤል በጋዛ ከምታደርገው የጦርነት ዘመቻ ተቃውሞ ጋር እና እንደ 'የልውጥ ጾታ' (ትራንስጀንደር) አትሌቶች እና ልዩነት፣ ፍትሃዊነት እና ማካተት (DEI) ፕሮግራሞች ባሉ ሌሎች ጉዳዮች ምክንያት ክትትል እያደረጉባቸውረ ካሉ ዩኒቨርሲቲዎች ዝርዝር ውስጥ ይገኛል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

በዩናይትድ ስቴትስ ውስጥ ባሉ ከ600 በላይ ዩኒቨርስቲዎች እና ኮሌጆች በድምሩ 8 ቢሊየን ዶላር የሚገመቱ ከ4,000 የሚበልጡ ድጋፎችን ለማቋረጥ ዒላማ ማድረጉን ሴንተር ፎር አሜሪካን ፕሮግረስ የተሰኘ የቲንክ ታንክ ቡድን ገልጿል።

ትራምፕ ረዑዕ በትሩዝ ሶሻል ገጻቸው ላይ "ኮሎምቢያ እንዲሁ አስቂኝ የልዩነት፣ ፍትሃዊነት እና ማካተት ፖሊሲዎቻቸውን ለማስቆም፣ በችሎታ ላይ የተመሰረተ የተማሪዎች ቅብላ ለማድረግ እና በግቢው ውስጥ የተማሪዎቻቸውን የሲቪል ነፃነት ለመጠበቅ ቆርጠዋል" ብለዋል።

ትራምፕ ቃለ መሃላ ከፈጸሙ ከአንድ ወር በኋላ፣ አስተዳደሩ በፀረ ሴማዊነት ክስ ኮሎምቢያን 400 ሚሊዮን ዶላር የፌዴራል ፈንድ ነጠቋል።

የገንዘብ ድጋፉ መቋረጥ ለዩኒቨርሲቲው ጥናት ድርስ ስጋት ፈጥሯል፣ ይህም የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት ሺፕማን በሰኔ ወር ነገሮች "ወሳኝ ነጥብ" ላይ መድረሳቸውን እንዲናገሩ አድርጓቸዋል።

የዋይት ሐውስ ውሳኔ ኮሎምቢያ በአስተዳደሩ የሚጠየቀውን የካምፓስ ሕግ ለውጥ እንዲያወጣ፣ የመካከለኛው ምሥራቅ ጥናት ዲፓርትመንቱን እንደገና ማደራጀትን እና ተማሪዎችን ከግቢ የማስወጣት እና የማሰር ስልጣን ያለው "ልዩ መኮንኖች" ቡድን መቅጠርን ይጨምራል።

ኮሎምቢያ ስምምነቱን ተከትሎ፣ አብዛኛዎቹ የተሰረዙ ወይም የቆሙ እርዳታዎች ወደነበሩበት ይመለሳሉ ብሏል።

ስምምነቱ ኮሌጁ ቀደም ሲል ያሳወቃቸውን ብዙ ለውጦችን ያቀፈ ሲሆን የስምምነቱን አፈፃፀም ለመገምገም በጋራ የተመረጠ ገለልተኛ የቁጥጥር ቡድን እንደሚመደብ ያካትታል።

ከእነዚያ ማስተካከያዎች መካከል በዩኒቨርሲቲው ካምፓስ ውስጥ የጋዛ ተቃውሞ አካል የሆኑትን ተማሪዎችን መቅጣት፣ ተቃዋሚዎች የካምፓስ መታወቂያ እንዲያሳዩ፣ በሰላማዊ ሰልፎች ወቅት የፊት ጭንብል አለመፍቀድ፣ የተማሪ ቡድኖችን የበለጠ ቁጥጥር ማድረግ እና በግቢው ውስጥ ያሉ መኮንኖችን ማስፋት ይገኙበታል።

ዩንቨርስቲው ስምምነቱ ጥፋትን መቀበል አይደለም ብሏል።

ኮሎምቢያ በመጋቢት ወር የትራምፕ አስተዳደር ጥያቄዎችን ለማክበር ፈቃደኛ መሆኑ የ'አይቪ ሊግ' ኮሌጅ ነፃነቱን አሳልፎ እንደሰጠ የሚሰማቸው አንዳንድ ሰዎች ከፍተኛ ትችት ገጥሞታል።

ሐርቫርድ ተቃራኒውን አካሄድ ወስዷል።

ምንም እንኳን መንግሥት በቢሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ለዩኒቨርሲቲው መስጠት ቢያቆምም እና ዓለም አቀፍ ተማሪዎችን የመመዝገብ አቅሙን ለማቆም ቢንቀሳቀስም ሐርቫርድ አስተዳደሩን ከስሷል።

በአገሪቱ ሀብቱሙ ዩኒቨርሲቲ በሆነው በሐርቫርድ የአገሪቱ ከፍተኛ የመንግሥት አካል በዋይት ሐውስ መካከል ያለው የፍርድ ቤት ክርክር ሰኞ ዕለት ተጀምሯል።

የትራምፕ አስተዳደር የትምህርት ተቋማት በኮሎምቢያ አቅጣጫ የበለጠ እንደሚሄዱ ተስፋ እንዳለው ጠቁሟል።