በትራምፕ አስተዳደር ምክንያት የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ፕሬዝዳንት ሥራ ለቀቁ

የጋዛን ጦርነት ለመቃወም አደባባይ የወጡ ሰዎች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ጊዜያዊ ፕሬዝዳንት በትራምፕ አስተዳደር ምክንያት ከሥራቸው ለቀቁ።

ዩኒቨርስቲውን ከነሐሴ ጀምሮ እየመሩ ያሉት ካትሪና አርምስትሮንግ በዩኒቨርስቲው እየተደረገ ባለው ለውጥ ምክንያት ነው ከሥራቸው ለመልቀቅ የወሰኑት።

ከሳቸው ቀድመው የነበሩት ፕሬዝዳንት የተማሪዎችን የጋዛ ጦርነት ተቃውሞ በተመለከተ በተከተሉት አሠራር ምክንያት ነበር ከሥልጣን የወረዱት።

የፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕን አስተዳደር ለማስደሰት በሚል ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ የፖሊሲ ለውጦች ለማድረግ ከአንድ ሳምንት በፊት ተስማምቷል።

ይህንን ስምምነት ተከትሎም ጊዜያዊ ፕሬዝዳንቷ ለመልቀቅ ወስነዋል።

ትራምፕ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች "ፀረ ሴማዊነትን እና አይሁዳውያን ተማሪዎች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ታግሰዋል" ብለው ሲተቹ ነበር።

የጋዛ ጦርነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደባቸውን ዩኒቨርስቲዎች ዒላማ ያደረጉት ትራምፕ፣ ለዩኒቨርስቲው ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የፌደራል መንግሥት በጀት እንደማይለቁም ሲዝቱ ተደምጠዋል።

ከፕሬዝዳንትነት የለቀቁት ካትሪና ቀድሞ ወደነበራቸው የዩኒቨርስቲው የሕክምና ክፍል ኃላፊነት የሚመለሱ ይሆናል።

የዩኒቨርስቲው የቦርድ አጋር ሊቀ መንበር ክሌር ሺፕማን ይተኳቸዋል ተብሏል።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ትራምፕ ኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ እና ሌሎችም ዩኒቨርስቲዎች "ፀረ ሴማዊነትን እና አይሁዳውያን ተማሪዎች ላይ የሚደርስ ጥቃትን ታግሰዋል" ብለው ሲተቹ ነበር።

የጋዛ ጦርነት በመቃወም ሰላማዊ ሰልፍ የተካሄደባቸውን ዩኒቨርስቲዎች ዒላማ ያደረጉት ትራምፕ፣ ለዩኒቨርስቲው ወደ 400 ሚሊዮን ዶላር የፌደራል መንግሥት በጀት እንደማይለቁም ሲዝቱ ተደምጠዋል።

ከፕሬዝዳንትነት የለቀቁት ካትሪና ቀድሞ ወደነበራቸው የዩኒቨርስቲው የሕክምና ክፍል ኃላፊነት የሚመለሱ ይሆናል።

የዩኒቨርስቲው የቦርድ አጋር ሊቀ መንበር ክሌር ሺፕማን ይተኳቸዋል።

"ኃላፊነቱን የምቀበለው ከባድ ጊዜ እንደሚጠብቀን በመረዳት ነው። የዩኒቨርስቲውን ዓላማ ለማሳካትና አስፈላጊ ለውጥ ለማምጣት እሠራለሁ" ሲሉ ተናግረዋል።

የዩኒቨርስቲው የቦርድ ባለ አደራ ኃላፊ ዴቪድ ጄ ግሪንዋልድ "ዶ/ር ካትሪና አርምስትሮንግ ኃላፊነቱን የወሰደችው በዩኒቨርስቲው ታሪክ ፈታኝ በሆነ ወቅት ነው። ያለመታከትም አገልግላለች" ብለዋል።

ዩኒቨርስቲው በትራምፕ አስተዳደር ጫና ምክንያት ተቃውሞዎች ሲካሄዱ ተማሪዎች የፊት ጭምብል እንዳያጠልቁ ለመከልከል ተስማምቷል።

የተወሰኑ የትምህርት ክፍሎች ላይም ለውጥ ለማድረስ ከስምምነት ደርሷል።

የጋዛን ጦርነትና አሜሪካ ለእስራኤል የምታደርገውን ድጋፍ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎች መካሄድ የጀመሩት ከኒው ዮርክ ኮሌጅ ነው።

ከኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ በተጨማሪ 60 ዩኒቨርስቲዎች የፌደራል መንግሥት የገንዘብ ድጋፍ እንደሚቋረጥባቸው ትራምፕ አስታውቀዋል።

የኮሎምቢያ ዩኒቨርስቲ ተመራቂው የመብት ተሟጋች ማሕሙድ ካሊል በፌደራል መንግሥቱ በቁጥጥር ሥር መዋሉ አይዘነጋም።

አሜሪካ ለመኖር ሕጋዊ ፈቃድ ቢኖረውም ትራምፕ ማሕሙድና ሌሎችም ፍልስጤምን የሚደግፉ የመብት ተሟጋቾች "ሐማስን ይደግፋሉ" ብለው ፈርጀዋል።

የ30 ዓመቱ ማሕሙድ ጠበቃ እንዳሉት፣ ማሕሙድ የነጻ ንግግር መብቱን ተጠቅሞ ለፍልስጤም ድምጽ በመሆን የጋዛን ጦርነትና አሜሪካ የምታደርገውን ድጋፍ ተቃውሟል።