የከሸፈው የቦሊቪያ መፈንቅለ መንግሥት መሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ

የቀቅደሞው አገሪቱ ጦር መሪ ጄኔራል ሁዋን ሆዜ ዙኒጋ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የቦሊቪያ ርዕሰ መዲና ላ ፓዝ የሚገኘው የፕሬዚዳንቱ ቤተ መንግስት በወታደሮች ከተወረረ ከሰዓታት በኋላ የአገሪቱ ፖሊስ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን መሪ በቁጥጥር ስር አዋለ።

የታጠቁ ተሽከርካሪዎች እና ወታደሮች ቁልፍ የመንግሥት ቢሮዎች የሚገኙበት ሙሪሎ አደባባይ ላይ ተሰማርተው ነበረ ቢሆንም በኋላ ላይ ሁሉም ተመልሰዋል ወጥተዋል።

ጦሩን የመራው ጄኔራል ሁዋን ሆዜ ዙኒጋ “ዲሞክራሲን እንደገና ማዋቀር” እንደሚፈልግ ተናግሮ ለአሁኑ ፕሬዝዳንት ሉዊስ አርሴን ቢያከብራቸውም የመንግሥት ለውጥ እንደሚመጣ አስታውቋል።

ጄነራሉ አሁን በቁጥጥር ስር ይገኛል።

ፕሬዝዳንት አርሴ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን አውግዘው፣ ህዝቡ "እንዲደራጅ እና... ለዲሞክራሲው እንዲታገል" ጥሪ አቅርበዋል።

ከፕሬዝዳንቱ ቤተ መንግስት በአገሪቱ ቴሌቪዥን ባስተላለፉት መልዕክት "የቦሊቪያውያንን ህይወት ለመቅጠፍ የተደረገውን መፈንቅለ መንግስት በድጋሚ መፍቀድ አይገባንም” ብለዋል።

ንግግራቸውን ተከትሎ የዴሞክራሲ ደጋፊዎች መንግሥትን በመደገፍ ወደ ጎዳና ወጥተዋል።

የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን ተከትሎ ፕሬዝዳንት አርሴ አዲስ ወታደራዊ አዛዦችን እየሾሙ መሆኑን አስታውቀዋል።

ጄነራል ዙኒጋ የቀድሞውን የቦሊቪያ መሪ ኢቮ ሞራሌስን በግልጽ መተቸቱን ተከትሎ ከስልጣኑ ተባሮ ነበር።

ሞራሌስም የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራውን በማውገዝ በጄነራል ዙኒጋ እና “በግብረ አበሮቹ” ላይ የወንጀል ክስ እንዲመሰረትባቸው አሳስበዋል።

የአገሪቱ አቃቤ ህግም የወንጀል ምርመራ ከፍቷል።

ጦሩ ዋና ዋና ቦታዎችን ተቆጣጥሯል

የፎቶው ባለመብት, Shutterstock

ይህ በአጭር ጊዜ የተጠናቀቀ እና ግራ ቀኙን ያላገናዘበ ወታደራዊ አመጽ እንጂ የስልጣን ግልበጣ አለመሆኑ ግልጽ እየሆነ መጥቷል።

የጄነራል ዙኒጋ ወታደራዊ አመጽ የተናጠል ክስተት መሆኑን ለማረጋገጥ ቀጣይ ሳምንታት ቁልፍ ይሆናሉ።

መንግሥት አሁን የበለጠ የተጋለጠ ይመስላል። በዚህ ምክንያት ሌሎች የፕሬዝዳንት አርሴን አስተዳደር ለማፍረስ ከወታደራዊ ይልቅ ፖለቲካዊ መንገድን ሊሞክሩ ይችላሉ።

ሆኖም ፕሬዝዳንቱ ተጽዕኖ ፈጣሪ የሆኑት የቀድሞው ፕሬዚዳንት እና የግራ ፖለቲካ መሪ የነበሩትን የኢቮ ሞራሌስን ድጋፍ ሊተማመኑ ይችላሉ።

ሞራሌስ ደጋፊዎቻቸው የመፈንቅለ መንግስቱ ሙከራው እንዲያበቃ ወደ አደባባይ በመውጣት እንዲጠይቁ ጥሪ አቅርበዋል።

ጄነራል ዙኒጋ በወታደሮች ከተወሰደ በኋላ ከሙሪሎ አደባባይ “ይህችን የትውልድ አገራችንን መልሰን እንወስዳታለን” ብሏል።

"ሀገርን ያፈረሱ ወንበዴዎች ሀገርን ተቆጣጥረዋል" ሲሉ አክሏል።

ሰኞ ዕለት በቴሌቭዥን ቀርቦም ሞራሌስን በሚቀጥለው ዓመት ለምርጫ ከተወዳደሩ አስራቸዋለሁ በማለት የቀድሞው ፕሬዚዳንት ላይ እገዳ ቢጣልባቸውም ከሥራው ተባሯል።

የመንግስት ደጋፊዎች መፈንቅለ መንግስቱን ዜና ከሰሙ በኋላ አደባባይ ወጥተዋል

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የቀድሞ አጋሮች ነበሩት አርሴ እና ሞራሌስ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዓይን ለዓይን ብዙም ባይተያዩም በቦሊቪያ የፖለቲካ ለውጥ ለማምጣት የሞከሩትን ወታደሮች ለማውገዝ አንድ ሆነዋል።

በ2019 ፕሬዘዳንት ሞራሌስ የፕሬዚዳንታዊ ምርጫን ውጤትን ለማጭበርበር እየሞከሩ ነው በማለት በወታደሮች በጉልበት ተገደው ወደ ሜክሲኮ በግዞት ተልከዋል።

በ2005 ኢቮ ሞራሌስ ሥልጣን ከመያዛቸው በፊት ቦሊቪያ በአሜሪካ አህጉር ካሉት አገራት የፖለቲካ አለመረጋጋት ከማይታይባቸው አንዷ ነበረች። በስልጣን ቆይታቸውም ህዝብ በጣም የሚፈልገውን መረጋጋት አምጥቷል።

የ2019 ምርጫን ተከትሎ አለመረጋጋት ከተፈጠረ በኋላ የተመረጡት ፕሬዝዳንት አርሴ በአካባቢው አገራት ፈጣን ምላሽ ልባቸው ተነክቷል።

እንደ ቬንዙዌላ እና ኮሎምቢያ ያሉ የግራ ክንፍ መንግስታት እየሆነ ያለውን ነገር በማውገዝ ዲሞክራሲ እንዲሰፍን ጥሪ አቅርበዋል። ዋሽንግተንም መረጋጋትን ጠይቃለች።

የሶሻሊዝም አገዛዙን የሚቃወሙ ቦሊቪያውያን ጭምር በደቡብ አሜሪካ ምድር አስከፊ የሰብአዊ መብት ታሪክ ያላቸው ወታደሮች በዲሞክራሲያዊ መንገድ የተመረጡ መሪዎችን በጠመንጃ በማስወገድ ወደ ጨለማ ጊዜ መመለስን አይፈልጉም።