በአሜሪካ ሕገ ወጥ ነው የተባለ ስደተኛን እንዳይያዝ አስመልጠዋል የተባሉ ዳኛ ታሰሩ

ዳኛ ሃናህ ዱጋን

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የምስሉ መግለጫ, ዳኛ ሃናህ ዱጋን

በአሜሪካ የዊስኮንሲን ግዛት ዳኛ ጉዳዩን እየተመለከቱ የነበረን ሕጋዊ ሰነድ የሌለው ስደተኛ እዳይታሰር ረድተዋል በሚል በአሜረካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢይ) በቁጥጥር ሥር ዋሉ።

ባለሥልጣናት እንደተናገሩት የኤፍቢአይ ወኪሎች ዳኛ ሃናህ ዱጋንን አርብ ጠዋት በቁጥጥር ስር ውለዋል።

የኤፍቢአይ ዳይሬክተር ካሽ ፓቴል በኤክስ ገጻቸው ላይ አስፍረውት ከደቂቃዎች በኋላ ባጠፉት ጽሁፍ፣ ዳኛዋ ኤዱዋርዶ ፍሎሬስ-ሩይዝ የተባለ ሜክሲኳዊ ከፍርድ ቤት እንዲያመልጥ አድርገዋል ሲሉ ከሰዋቸዋል።

ዳኛ ሃናህ ዱጋን ላይ ሥራን በማደናቀፍ እና ግለሰቡን እንዳይያዝ በመደበቅ ክስ ቀርቦባቸዋል፤ በዚህም ጥፋተኛ ሆነው ከተገኙ እስከ ስድስት ዓመት የሚደርስ እስር ይጠብቃቸዋል።

የዳኛዋ ጉዳይ በፍርድ ቤት በተሰማበት ጊዜ ጠበቃቸው "በቁጥጥር ስር መዋላቸው በጣሙን እንዳሳዘናቸው እና መቃወማቸውን ቀረቡበት" በማለት እስሩ "ለሕዝብ ደኅንነት ሲባል የተፈጸመ አይደለም" ብለዋል።

የዳኛዋን ጉዳያቸው ከሦስት ሳምንት ለመስማት ቀጠሮ ተሰጥቶ በእራሳቸው ዋስትና ተለቀዋል።

የኢሚግሬሽን ዳኛ ከአንድ ሳምንት በፊት ለዳኛዋ መታሰር ምክንያት በሆነው ሕገወጥ ስደተኛ ላይ የእስር ትዕዛዝ አውጥተው እንደነበረ በኤፍቢአይ ለፍርድ ቤት በቀረበ ሰነድ ላይ አስፍሯል።

ይህንንም ተከትሎ ኤዱዋርዶ ፍሎሬስ-ሩይዝ ቀደም ሲል በነበረው ቀጠሮ መሠረት በኤፍቢአይ በተያዙት ዳና ችሎት ቀርቦ ነበር። የአሜሪካ የኢሚግሬሽን እና ጉምሩክ እንኢሁም የኤፍቢአይ ወኪሎች ግለሰቡን ከፍርድ ቤት ይዘው ለመውሰድ በተገኙበት ወቅት ነው ውዝግብ የተፈጠረው።

በዚህ ጊዜ የችሎቱ ዳኛ ሃናህ ዱጋን የኢሚግሬሽን መኮንኖች በስፈራው መኖራቸውን ሲያውቁ ተቆጥተው አብዛኞቹ ወደ ፍርድ ቤቱ ዋና ዳና እንዲሄዱ ማድረጋቸውን በኤፍቢአይ ለፍርድ ቤት የቀረነው የክስ ሕግ ሰነድ አመልክቷል።

የኢሚግሬሽን ወኪሎች ወደ ተባሉት ቦታ በሄዱበት ጊዜ ዳኘዋ ኤዱዋርዶ ፍሎሬስ-ሩይዝን እና ጠበቃውን ለዳኞች በተዘጋቸው የጎን እንዲወጡ በማድረግ አስመልጠዋል ብሏል ሰነዱ።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ባለሥልጣናት እንዳሉት ከአስር ዓመት በፊት ከአሜሪካ እዲባረር ተደርጎ የነበረው ኤዱዋርዶ ፍሎሬስ-ሩይዝ በዳኛዋ ድጋፍ ከፍርድ ቤቱ ወጥቶ ማምለጥ ቢችልም ከደቂቃዎች በኋላ በተደረገበት ክትትል በቁጥጥር ስር ውለወል።

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ፓም ቦንዲ በኤክስ ገጻቸው ላይ እንዳሰፈሩት ዳኛ ዱጋን በቁጥጥር ስር የዋሉት "ሕገወጥ የውጭ አገር ዜጋ በሕግ ቁጥጥር ስር እንዳይውል በመርዳታቸው ነው. . . ማንም ከሕግ በላይ አይደለም።"

ዳኛዋ በቁጥጥር ስር የዋሉት በኒው ሜክሲኮ ግዛት ውስጥ አንድ የቀድሞ ዳኛ የቬንዙዌላ የበሮ በሎች ቡድን አባል ነው የተባለ ግለሰብን በቤታቸው ውስጥ ደብቀዋል ተብለው ከተከሰሱ ከአንድ ቀን በኋላ ነው።

ይህንንም ተከትሎ አቃቤ ሕግ ቦንዲ "አንዳንድ ዳኞች እራሳቸውን ከሕግ በላይ አድርገው የሚመለከቱ ይመስለኛል" በማለት ለፎክስ ኒውስ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ጨምረውም "መረጃዎችን የሚያጠፉ ከሆነ፣ የሕግ ሥራን የሚያደናቅፉ ከሆነ እና ተከሳሾች ከፍርድ ቤት እንዲያመልጡ የሚተባበሩ ከሆነ አንታገሳቸውም።"

የዳኛዋ መታሰርን ተከትሎ በፖለቲከኞች መካከል የተለያየ አስተያየት እየተሰነዘረ ነው።

ሃናህ ዱጋን ለመጀመሪያ ጊዜ ለዳኝነት የተመረጡት በአውሮፓውያኑ 2016 ሲሆን፣ ከዚያም በ2022 ለተጨማሪ ስድስት ዓመታት ለሁለተኛ ጊዜ እንዲያገለግሉ ተመርጠዋል።

በዊስኮንሲን ግዛት ዳኞች የሚመረጡት ከፖለቲካ ወገንተኝነት በራቀ ሁኔታ ቢሆንም የሃናህ ዱጋን ምርጫ በዲሞክራቱ የሚልዋኪ ከተማ ከንቲባ ድጋፍ ተሰጥቶታል።

አሁን በዳኘዋ ላይ የቀረበው የፀጥታ አካላትን ትግባር የማደናቀፍ ክስ ከፍተኛው የአምስት ዓመት እስር እና 250 ሺህ ዶላር ቅጣት፣ እንዲሁም ተፈላጊን መደበቅ ደግሞ አስከ አንድ ዓመት የሚደርስ ,እስር እንዲሁም የ100 ሺህ ዶላር ቅጣትን ያስከትላል።