ሩሲያ እክል የገጠማቸውን ባለሙያዎቿን ከህዋ ለመመለስ ባዶ መንኮራኩር ልትልክ ትችላለቸ ተባለ

መንኩራኩር

የፎቶው ባለመብት, Reuters

በህዋ ላይ ያሉ ሶስት የሩሲያ ባለሙያዎች መንኮራኩራቸው እክል ማገጠሙን ተከትሎ የሩሲያ የህዋ ኤጀንሲ ከታሰበው ጊዜ በፊት ባለሙያዎቹን ለመመለስ ባዶ መንኮራኩር ወደ ዓለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ ለመላክ እያሰበ እንደሆነ ገልጿል።

የሩሲያ የጠፈር ምርምር ተቋም እና ናሳ መንኮራኩሯ ጠፈር ላይ ሳለች በምን ምክንያት መሸንቆር እንዳጋጠማት ገልጽ አይደለም ብለዋል።

ይሁን እንጂ በመንኩራኩሯ ላይ የደረገው ጉዳት በሚትሮይድ ተመትታ አለመሆኑ ተገልጿል።

መንኮራኩሯ ላይ አነስተኛ ቀዳዳ መፈጠር የጀመረው ጠፈርተኞቹ መደበኛ የስራቸውን ለማድረግ ዝግጅት እያደረጉ ሳለ ነበር።

ሶስቱ ባለሙያዎች እንዴት ወደ ምድር ይመለሱ የሚለው ጉዳይ ገና አልተወሰነም።

ሆኖም ሊተገበር የሚችለው አማራጭ ግን ሌላ መንኮራኩር መላክ እንደሆነ ተገምቷል።

የመሆን ዕድሉ ዝቅተኛ የሆነው አማራጭ ደግሞ እክል የገጠመውን የመንኮራኩር አካለ በመተው እንዲመለሱበት ማድረግ ነው።

ኤም ኤስ 22 የሚል ስያሜ ያላት ይህች መንኮራኩር ሁለት ሩሲያውያንን እና አንድ የነሳ ባለሙያን ይዛ ነበር ባለፈው መስከረም ወደ ጠፈር ያመራችው።

የዓለም አቀፉ ህዋ ጣቢያ የናሳ ሃላፊ መጪው የካቲት ወር ሌላ መንኮራኩር የሚላክበት ጊዜ ሊሆን እንሚችል ጠቅሰው በተከታዩ ወር መጋቢት ባለሙያዎች ወደ ምድር ይመለሳሉ ብለዋለ።

ነሳ ሁሉም ባለሙያዎች አደጋ ላይ እንዳልሆኑ ገልጿል።

ዓለም አቀፉ የህዋ ጣቢያ እንደ አውሮፓውያኑ በ1998 የተመሰረተ ሲሆን ከምድር 400 ኪሎ ሜትር ርቆ ይገኛል።

የህዋ ባለሙያዎችም ለወደፊት የህዋ ሳይንስ ሚረዱ ሙከራዎችን እና ጥናቶችን በጣቢያው ያደርጋሉ።