በአፍሪካ ዋንጫ እና በእስያ ዋንጫ ምክንያት የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች የሚያጧቸው ተጫዋቾቸ የትኞቹ ናቸው?

ኦናና፣ ሞ ሳላህ እና ሰን

የአፍሪካ ዋንጫ እና የእስያ ዋንጫ በጥር ወር ይከናወናሉ። በዚህ ምክንያት በርካታ የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ክለቦች ተጫዋቾቸቻውን ያጣሉ።

የአፍሪካ ዋንጫ በአይቮሪ ኮስት አስተናጋጅነት ይከናወናል። ኳታር ደግሞ የእስያ ዋንጫን ታስተናግዳለች።

አንዳንድ የአውሮፓ ሊጎች በዚህ ወቅት ጨዋታ የማያስተናግዱ ቢሆንም የእንግሊዝ ፕሪሚር ሊግ ክለቦች ለሳምንታት ተጫዋቾቸቻውን ያጣሉ።

ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪያቸውን እና ግብጽ ብሔራዊ ቡድን አምበል የሆነውን ሞሐመድ ሳላህን የሚኣጡት የሊቨርፑሉ አሰልጣኝ የርገን ክሎፕ ውድድሩ ክለቦች የሚዘጋጁበት ነገር ነው ብለዋል።

"የአፍሪካ ዋንጫው እንደሚኖር እና ሞ መሄድ እንዳለበት አውቀናል" ብለዋል ክሎፕ።

"[ዋታሩ] ኤንዶም የእስያ ዋንጫ ተሳታፊ ነው። ስለዚህ እንደ አመጣጡ እንቀበለዋለን። ይህንን መቋቋም አለብን፣ እናደርገዋለንም።”

የቶተንሃም አሰልጣኝ አንጄ ፖስትኮግሉ አገራቸውን አውስትራሊያን በ2015 የእስያ ዋንጫን እንድታነሳ ረድተዋል። ሁለቱም ውድድሮች ለተጫዋቾቹ አስፈላጊ ናቸው ብለዋል።

"በጣም ከፍ አድርጌ እመለከተዋለሁ። በጣም አስፈላጊ ነው ብዬም አስባለሁ። ብዙ የአውሮፓ ሰዎች የአውሮፓ ዋንቻ በጣም አስፈላጊ ነው ብለው ያስባሉ። ይህ ለእስያ ዋንጫ ወይም ለአፍሪካ ዋንጫ በተመሳሳይ ይሠራል።”

ለመሆኑ የመጨረሻው የተጫዋቾች ምርጫ ተከናውኗል?

አጭሩ መልስ አይደለም የሚል ነው። ስለዚህ ገና አንዳንድ ዘግይተው የሚጨመሩ እና የሚወጡ ተጫዋቾች ሊኖሩ ይችላሉ።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

አንጎላ፣ አልጄሪያ፣ ቡርኪናፋሶ፣ ካሜሩን፣ ኬፕ ቨርዴ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ፣ ግብጽ፣ ኢኳቶሪያል ጊኒ፣ ጋና፣ ጊኒ፣ ጊኒ ቢሳው፣ አይቮሪ ኮስት፣ ጃፓን፣ ሞሪታንያ፣ ሞሮኮ፣ ሞዛምቢክ፣ ናሚቢያ፣ ናይጄሪያ፣ ሴኔጋል፣ ደቡብ አፍሪካ እና ቱኒዚያ የመጨረሻውን የተጫዋቾቻቸውን ይፋ አድርገዋል።

ጋምቢያ፣ ማሊ፣ ዛምቢያ እና ታንዛኒያ እስከ 55 የሚደርሱ ተጫዋቾችን በጊዜያዊነት የመረጡ ቡድኖች ናቸው።

ለአፍሪካ ዋንጫ አንድ ብሔራዊ ቡድን እስከ 27 የሚደርሱ ተጫዋቾችን የመጨረሻ ዝርዝር እስከ ዛሬ ድረስ ማቅረብ አለበት።

አውስትራሊያ፣ ኢራቅ፣ ማሌዢያ እና ደቡብ ኮሪያ ለእስያ ዋንጫ የመጨረሻ ያሏቸውን 26 ተጨዋቾችን ይፋ አድርገዋል።

ቻይና፣ ሆንግ ኮንግ፣ ህንድ፣ ኢንዶኔዢያ፣ ዮርዳኖስ፣ ኪርጊስታን፣ ሊባኖስ፣ ኳታር፣ ሶሪያ፣ ታጂኪስታን፣ የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስ እና ቬትናም እስካሁን እስከ 50 የሚደርሱ ተጫዋቾችን በጊዜያዊነት መርጠዋል።

ባህሬን፣ ኢራን፣ ኦማን፣ ፍልስጤም፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ ታይላንድ እና ኡዝቤኪስታን ጊዜያዊ ተጫዋቾችን ለእስያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ቢያቀርቡም ይፋ አላደረጉም። ስለዚህ ከዚህ በታች የተካተቱት ተጫዋቾች አገራቱ በቅርብ ጊዜ ካደረጓቸው ዓለም አቀፍ ጨዋታዎች የተወሰዱ ናቸው።

የትኞቹ ፕሪሚር ሊግ ክለቦች የትኞቹን ተጫዋቾች ያጣሉ?

በርንማውዝ - 2

ዳንጎ ኦውታራ (አጥቂ፣ ቡርኪናፋሶ)

አንትዋን ሴሜንዮ (አጥቂ፣ ጋና)

አርሰናል - 3

ሞሃመድ ኤልኔኒ (አማካይ፣ ግብጽ)

ታኬሂሮ ቶሚያሱ (ተከላካይ፣ ጃፓን)

አማካዩ ቶማስ ፓርቴይ በጋና ጊዜያዊ ቡድን ውስጥ ቢካተትም የመጨረሻ ቡድን ውስጥ በጉዳት ምክንያት አልተካተተም።

አስቶንቪላ - 1

በርትራንድ ትራኦሬ (አማካይ፣ ቡርኪናፋሶ)

ብሬንትፎርድ - 4

ሳማን ጎዶስ (አማካይ፣ ኢራን)

ኪም ጂ-ሶ (ተከላካይ፣ ደቡብ ኮሪያ)

ፍራንክ ኦንያካ (አማካይ፣ ናይጄሪያ)

ዮአን ዊሳ (አጥቂ፣ ዲሞክራቲክ ኮንጎ)

ብራይተን - 2

ሳይመን አዲንግራ (አጥቂ፣ አይቮሪ ኮስት)

ካኦሩ ሚቶማ (አጥቂ፣ ጃፓን)

ቼልሲ - 1

በርንሊ - 0

ኒኮላስ ጃክሰን (አጥቂ፣ ሴኔጋል)

ክሪስታል ፓላስ - 1

ጆርዳን አየው (አጥቂ፣ ጋና)

ኤቨርተን - 1

ኢድሪሳ ጉዬ (አማካይ፣ ሴኔጋል)

ፉልሃም - 3

ፎዴ ባሎ ቱሬ (ተከላካይ ፣ ሴኔጋል) ከኤሲ ሚላን በውሰት የፈረመ

ካልቪን ባሴይ (ተከላካይ፣ ናይጄሪያ)

አሌክስ ኢዎቢ (አማካይ፣ ናይጄሪያ)

ሊቨርፑል - 2

ዋታሩ ኤንዶ (አማካይ፣ ጃፓን)

ሞሃመድ ሳላህ (አጥቂ፣ ግብፅ)

ሉተን - 1

ኢሳ ካቦሬ (ተከላካይ፣ ቡርኪናፋሶ)

ማንቸስተር ሲቲ - 0

ማንቸስተር ዩናይትድ - 3

ሶፊያን አምራባት (አማካይ፣ ሞሮኮ) በውሰት ከፋዮረንቲና የፈረመ

አማድ ዲያሎ (አጥቂ፣ አይቮሪ ኮስት)

አንድሬ ኦናና (ግብ ጠባቂ፣ ካሜሩን)

ኒውካስል - 0

ኖቲንግሃም ፎረስት - 6

ኦላ አይና (ተከላካይ፣ ናይጄሪያ)

ሰርጅ ኦሪየር (ተከላካይ፣ አይቮሪ ኮስት)

ዊሊ ቦሊ (ተከላካይ፣ አይቮሪ ኮስት)

ቺኩ ኩያቴ (አማካይ፣ ሴኔጋል)

ሙሳ ኒያካቴ (ተከላካይ፣ ሴኔጋል)

ኢብራሂም ሳንጋሬ (አማካይ፣ አይቮሪ ኮስት)

ሼፊልድ ዩናይትድ - 2

ያስር ላሩቺ (ተከላካይ፣ አልጄሪያ) ከትሮይስ በውሰት የፈረመ

አኒስ ቤን ስሊማን (አማካይ ፣ ቱኒዚያ)

ቶተንሃም - 3

ይቭ ቢሱማ (አማካይ፣ ማሊ)

ሶን ሄንግ-ሚን (አጥቂ፣ ደቡብ ኮሪያ)

ፓፔ ማታር ሳር (አማካይ፣ ሴኔጋል)

ዌስትሃም - 2

ናዬፍ አገርድ (ተከላካይ፣ ሞሮኮ)

መሃመድ ኩዱስ (አማካይ ፣ ጋና)

ዎልቭስ - 4

ህዋንግ ሄ-ቻን (አማካይ፣ ደቡብ ኮሪያ)

ጀስቲን ሃብነር (ተከላካይ፣ ኢንዶኔዥያ)

ራያን አይት-ኑሪ (ተከላካይ፣ አልጄሪያ)

ቡባካር ትራኦሬ (መሃል ሜዳ፣ ማሊ)