በበርካታ የአፍሪካ አገራት የወጣቶች ሱስ እየሆነ ያለው የእግር ኳስ ውርርድ [ቤቲንግ]

በእግር ኳስ አማካይነት የሚደረግ የውርርድ ቁማር [ቤቲንግ] ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ የአፍሪካ አገራት ውስጥ በከፍተኛ ሁኔታ ተስፋፍቷል።

በዚህ ውርርድ ውስጥ ለእግር ኳስ ከፍተኛ ፍቅር ያላቸው ታዳጊዎች እና ወጣቶች ዋነኛ ተሳታፊዎች ናቸው። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ባለሙያዎች እንደሚሉት ይህ የውርርድ ቁማር በበርካቶች ዘንድ ወደ ሱስነት እየተሸጋገረ ነው።

ይህ ቪዲዮ በውርርድ [ቤቲንግ] ውስጥ የሚሳተፉ የካሜሩን ወጣቶች ያሉበትን ሁኔታ በምሳሌነት ይዳስሳል።