በዲሞክራቲክ ኮንጎ በቤተ ክርስቲያን ላይ በተፈጸመ ጥቃት 10 ሰዎች ተገደሉ

ወታደሮች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ በሰንበት የጸሎት ሥነ ሥርዓት ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመ የቦንብ ትቃት 10 ሰዎች ሲገደሉ 39 ደግሞ ቆሰሉ።

የአገሪቱ መንግሥት ካሲንዲ ተብሎ በሚጠራው እና በምሥራቃዊ የኮንጎ ክፍል ውስጥ በሚገኘው ቤተክርስቲያን ላይ የተፈጸመውን የቦንብ ጥቃት ከአይኤስ ጋር ግንኙነት ያለውን ቡድን አድርሶታል ሲል ወንጅሏል።

በጥቃቱ በቤተክርስቲያኑ የዕሁድ ጸሎትን ሲታደሙ የነበሩ 10 ሰዎች እንደተገደሉ ባለሥልጠናት አስታውቀዋል።

ከሟቾች በተጨማሪ 39 ሰዎች ለጉዳት የተዳረጉበትን ይህንን ጥቃት የአገሪቱ ወታደራዊ ተቋም “የሽብር ድርጊት” ነው ሲል የፈረጀው ሲሆን፣ ፈጻሚው ‘አላይድ ዲሞክራቲክ ፎርስስ’ ወይም ‘ኤዲኤፍ’ ነው ሲል ከሷል።

የተጠቀሰው ቡድን በምሥራቃዊ ዲሞክራቲክ ኮንጎ ውስጥ ሰፊ እንቅስቃሴ የሚያደርግ የአማጺ ቡድን ነው።

የኮንጎ መንግሥት ባወጣው መግለጫ በ‘ኤዲኤፍ’ የተፈጸ ነው ያለውን የቦምብ ጥቃት “አጥብቆ ያወግዟል።”

በመግለጫው መንግሥት “በእዚህ አስቀያሚ የሽበር ጥቃት” ቤተሰቦቻቸወን ላጡ ሰዎች የተሰማውን “ጥልቅ ሐዘን” ገልጿል።

በዲሞክራቲክ ኮንጎ የተሰማራው የተባበሩት መንግሥት ድርጅት ተልዕኮ በካሲንዲ የተፈጸመውን “አስነዋሪ” ያለውን ጥቃት አውግዟል።

“ይህ የሽብር ጥቃት በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ሠራዊት በተለያዩ የጦር ግንባሮች ሽንፈት በደረሰበት ኤዲኤፍ እንደተፈጸመ ግልጽ ነው” ሲል የአገሪቱ መንግሥት ቃል አቀባይ አንቶኒ ሙላሻይ ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ ጨምረውም ለጥቃቱ መደበኛ ያልሆነ ቦምብ ጥቅም ላይ መዋሉንም ተናግረዋል።

ካሲንዲ የኤዲኤፍ እንቅስቃሴ ጠንክሮ ከሚታይበት ቢኒ ከተባለ አከባቢ የ8 ኪሎ ሜተር ርቀት ያለው ነው።

ባለፈው ወር የሀገሪቱ የተመድ ተወካይ በጽጥታው ምክር ቤት ቀርበው የጸጥታ ችግር ከዲአር ኮንጎ ዋነኛ ፈተናዎች መካከል አንዱ ነው።

በአውሮፓውያኑ 1990ዎቹ ብቅ ያለው ኤዲኤፍ የተፈጠረው በኡጋንዳ በተፈጠረ ውስጣዊ ቅሬታ የተፈጠረ ነው።

ሆኖም በዲአር ኮንጎ እንደአዲስ መታየት ከጀመረ በኃላ በኮንጎ ተከታታይ ጥቃት እየፈጸመ አለማቀፋዊ የጀሃዲስቶች ገጽታ እየያዘ ይገኛል።

ኤዲኤፍ የሚፈጽማቸውን ጥቃቶች ከአይ ኤስ ጋር እያያዘም እየገለጸ ይገኛል።