ማንቸስተር ሲቲ ከሊቨርፑል እና ቶተንሃም ከማንቸስተር ዩናይትድ፡ የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ግምት

ማንቸስተር ሲቲ ከሊቨርፑል

አሥራ አንደኛው ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ቅዳሜ እና እሑድ ሲከናወኑ ቶተንሃም ከማንቸስተር ዩናይትድ እና ማንቸስተር ሲቲ ከአምናው ሻምፒዮን ሊቨርፑል የሚያደርጓቸው ጨዋታዎች ይጠበቃሉ።

ሊጉን በመምራት ላይ የሚገኘው አርሴናልም ከሰንደርላንድ ጋር ጠንካራ ፉክክር ይጠብቀዋል።

የቢቢሲው የእግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱተን ጨዋታዋቹን እንደሚከተለው ገምግሟል።

ቅዳሜ

ሰንደርላንድ ከአርሴናል

ቶተንሃም ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ቶተንሃም በሜዳው ጥሩ መንቀሳቀስ ባለመቻሉ ለመገመት ይከብዳል።

ቡድኑ በሜዳው ካደረጋቸው አራት ጨዋታዎች አንድ ነጥብ ብቻ ማግኘቱ እና ጎሎችን አለማስቆጠሩ ትልቅ ችግር ነው።

ዩናይትድ ጥሩ መሻሻል ቢያሳይም ከሜዳው ውጭ በሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ገና እምነት አላሳደርኩም።

ባለፈው ዓመት አራት ጊዜ ተገናኝተው ስፐርስ አሸንፏል። ዘንድሮ ዩናይትድን ባስቀድምም ጨዋታው አቻ እንደሚጠናቀቅ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1 - 1

ኤቨርተን ከ ፉልሃም

ኤቨርተን ባለፈው ሳምንት ከሰንድርላንድ ጋር በመጀመሪያው አጋማሽ ጥሩ ተንቀሳቅሷል።

ቡድኑ የአጥቂ ችግር እንዳለበት አሁንም እየታየ ይገኛል።

ፉልሃም ከተከታታይ አራት ሽንፈት በኋላ በሊጉ ግርጌ ላይ የሚገኘውን ዎልቭስን አሸንፏል።

ይህ ጨዋታ ብዙ ጎሎች የሚቆጠሩበት አይመስልም።

ግምት፡ 1 - 1

ዌስት ሃም ከ በረንሌይ

ዌስት ሃም ባለፈው ሳምንት ኒውካስልን ባሸነፈበት መልኩ ይጫወታል?

አንዳንድ ተጫዋቾችም ጥሩ መንቀሳቀስ ችለዋል።

በርንሌይ ጠንካራ ተፎካካሪ መሆኑን አሳይቷል።

ግምት፡ 2 - 1

ሰንደርላንድ ከ አርሴናል

ሰንደርላንድ ጨዋታዎችን በማጥቃት መጀመሩ ውጤታማ ቢያደርገውም ከአርሴናል ጋር የሚያዋጣው አካሄድ አይመስልም።

አርሴናል ጥሩ ሳይንቀሳቀስ ማሸነፍ እንደሚችል ከስላቪያ ፕራግ ጋር አሳይቷል።

የቡድኑን አጨዋወት ጥያቄ ውስጥ የሚያስገቡ ሰዎች ቢኖሩም ዋናው ግብ ስኬታማ መሆን ነው።

አርሴናል በብዛት 1 ለምንም የሚያሸንፍ ቡድን ቢሆንም ብዙ ጎሎችንም የሚያስቆጥርባቸው ጨዋታዎች አሉ።

ግምት፡ 0 - 2

ቼልሲ ከ ዎልቭስ

ቼልሲ በዓለም የክለቦች ዋንጫ ምክንያት ተጫዋቾችን ማፈራረቅ እንደተገደደደ አሠልጣኝ ኤንዞ ማሬስካ ገልጸዋል።

ለቡድኑ ወጥ አለመሆን አንደኛው ምክንያት ቢሆንም ዎልቭስ ካለበት አቋም አንጻር ጨዋታው የሚከብዳቸው አይሆንም።

ዎልቭስ በቡኩሉ በሚፈለገው ልክ እየተንቀሳቀሰ ኤእደለም። አሰልጣኝ ቪቶር ፔሬራም ተሰናብተዋል።

ግምት፡ 2 - 0

እሑድ

ክሪስታል ፓላስ ከብራይተን

አስቶን ቪላ ከ በርንመዝ

ቪላ ውጤታማ በመሆን የጀመረው ጉዞ ባለፈው ሳምንት አንፊልድ ላይ ተቀጭቷል።

በርንመዝ ለየትኛውም ቡድን አስቸጋሪ ሊሆን ይችላል።

አሠልጣኝ ኡናይ ኤምሬ በታክቲክ ረገድ ባመኑበት መንገድ መጓዛቸው ከሊቨርፑል ጋር ዋጋ አስከፍሏቸዋል። በርንመዝም ይህንን መንገድ ሊከተል ይችላል።

ባለፈው ዓመት በርንመዝ ባለቀ ሰዓት አስቆትሮ አቻ ተለያይተዋል።

ግምት፡ 1 - 1

ብሬንትፎርድ ከ ኒውካስል

ኒውካስል ባለፈው ሳምንት በዌስት ሃም ሲሸነፍ ሌላ ቡድን መስሎ ነበር።

ቡድኑ በመከላከል ረገድ ጥሩ ቢሆንም ጎሎችን አያስቆጥርም።

ብሬንትፎርድ በመልሶ ማጥቃት መጫወትን የሚመርጥ ቡድን ነው።

ግምት፡ 0 - 0

ክሪስታል ፓላስ ከ ብራይተን

ይህንን ጨዋታ ባለፈው ዓመት ፓላስ በሜዳውም ከሜዳው ውጭም አሸንፏል።

ሁለቱ ቡድኖች በሊጉ አጋማሽ ላይ ተቀራርበው ተቀምጠዋል።

ባለፈው ሳምንት ሁለቱም ቡድኖች በቀላሉ አሸንፈዋል።

ፓላስ በአውሮፓ በሳምንቱ አጋማሽ መድረክ ባይጫወት እንደሚያሽነፍ እገምት ነበር።

ግምት፡ 1 -1

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ሊድስ

ሁለቱ ቡድኖች የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ የሚጫወቱበት መርሐ ግብር ነው።

ፎረስት ባለፈው ሳምንት ዩናይትድ ለማሸነፍ ተቃርቦ ነበር። አJልጣኝ ሾን ዳይሽ የመጀመሪያ ድላቸውን አላስመዘገቡም።

ሊድስ ከሜዳው ውጭ ጎል አስቆጥሮ ነጠብ ማግኘት የቻለው ዎልቭስ ሜዳ ላይ ነበር።

ከሜዳ ውጭ ያለው ደካማ ጉዞ ለፎረስት መልካም ዕድል ይመስላል።

ግምት፡ 2 - 0

ማንቸስተር ሲቲ ከ ሊቨርፑል

ሊቨርፑል ደካማ ጉዞው ማብቃቱን የሚያረጋግጥበት ጨዋታ ነው።

ላለፉት ዓመታት ሁለቱ ቡድኖች አቻ ቢለያዩም ይህ ግን ለማሸነፍ የሚጥሩበት ጨዋታ እንደሚሆን እገምታለሁ።

ዋንጫው የአርሴናል በመሆኑ ማንም ጨዋታውን ያሸንፍ ለሁለተኛ ደረጃ የሚደረግ ፉክክር ነው የሚሆነው።

ሁለቱም ቡድኖች ከመድፈኞቹ ጋር የሚፎካከሩበት ደረጃ ላይ አይገኙም።

ግምት፡ 2 - 1