እስራኤል በየመን ሁቲዎች ላይ በፈጸመችው ጥቃት ስምንት ሰዎች መገደላቸው ተዘገበ

በየመን ዋና ከተማ ከጥቃቱ በኋላ የሚታይ ጭስ

የፎቶው ባለመብት, Reuters

የሁቲ ታጣቂዎች በእስራኤል ላይ በተደጋጋሚ ለሚሰነዘሩት የሰው አልባ አውሮፕላን እና የሚሳኤል ጥቃት ምላሽ ለመስጠት የአየር ኃይሉ በየመን "ከባድ ጥቃት" መፈጸሙን የእስራኤል ጦር አስታወቀ።

የእስራኤል መከላከያ ኃይል እንደገለጸው ከሆነ በዋና ከተማዋ ሰነዓ በደርዘን በሚቆጠሩ አውሮፕላኖቹ የሁቲ የደህንነት እና የስለላ አገልግሎቶች እና የጦር ኃይሎች ተቋማት ላይ የቦምብ ጥቃት ፈጽመዋል።

በሁቲ የሚመራው የጤና ሚኒስቴር የእስራኤልን ጥቃት "አሰቃቂ ወንጀል" በማለት ኮንኗል። የሲቪል ተቋማት እና የመኖሪያ ሕንፃዎች መመታታቸውን እና የስምንት ሰዎች ሕይወት ማለፉን ተናግሯል።

በእስራኤል የቀይ ባህር ሪዞርት ኢላት ሁቲዎች በፈጸሙት የሰው አልባ ጥቃት 22 ሰዎች ከቆሰሉ ከአንድ ቀን በኋላ የተፈጸመ ጥቃት ነው።

ሁቲዎች ከ10 ዓመታት በፊት ዓለም አቀፍ እውቅና ያገኘውን መንግሥት ካባረሩ እና የእርስ በርስ ጦርነት እንዲፈጠር ካደረጉ በኋላ አብዛኛውን የሰሜን ምዕራብ የመን ተቆጣጥረዋል።

መስከረም 2016 በእስራኤል እና በሐማስ መካከል በጋዛ ጦርነት ከጀመረ በኋላ ፍልስጤማውያንን በመደገፍ እስራኤልን እና ዓለም አቀፍ መርከቦችን በደቡብ ቀይ ባህር እና በኤደን ባሕረ ሰላጤ ላይ ማጥቃት ጀመረዋል።

እስራኤል፣ በየመን ሁቲዎች በአገሪቱ ላይ ለተተኮሱት በመቶዎች ለሚቆጠሩ ሚሳኤሎች እና ሰው አልባ አውሮፕላኖች አፀፋዊ እርምጃ በመውሰድ ብዙ የአየር ጥቃት ፈጽማለች።

የእስራኤል ጥቃት ተከትሎ ሃሙስ ከሰአት በኋላ በከተማዋ በሚገኙ ቢያንስ ሦስት ቦታዎች ላይ ትልቅ ጥቁር ጭስ ሲወጣ የሚያሳዩ ቪዲዮዎች ታይተዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በሁቲ የሚተዳደረው አል-ማሲራህ ቲቪ የንቅናቄው መሪ አብዱል ማሊክ አል-ሁቲ ንግግር ከማስተላለፉ በፊት ነው።

አልማሲራህ እንደዘገበው ጥቃቱ ያነጣጠረው በማይን እና ሳባኢን በሚገኙ የመኖሪያ አካባቢዎች እንዲሁም በዳህባን የኃይል ማመንጫ ጣቢያ ላይ ነው። በርካታ የወደሙ ሕንፃዎችን የሚያሳዩ ፎቶግራፎችን ለቋል።

የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ዶ/ር አኔስ አል-አስባሂ "በሲቪል፣ በአገልግሎት እና በመኖሪያ ተቋማት ላይ ሆን ተብሎ እና ስልታዊ በሆነ መልኩ አነጣጥሯል" ሲሉ የእስራኤል ጦርን የከሰሱ ሲሆበን ይህም "በሁሉም ረገድ የጦር ወንጀል ነው" ብለዋል።

ስምንት ሰዎች መሞታቸውንና 142 ሰዎች መቁሰላቸውን እና ሰላማዊ ሰዎችም እንደሚገኙበት ገልጸዋል። የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች በፍርስራሽ ውስጥ ጉዳት የደረሰባቸውን ሰዎች ፍለጋ ላይ መሆናቸውንም አክለዋል።

ጥቃቱ የተፈፀመው በሃውቲ የሚተዳደረው አል-ማሲራህ ቲቪ የንቅናቄው መሪ አብዱል ማሊክ አል-ሁቲ ንግግር ከማስተላለፉ በፊት ነው

የፎቶው ባለመብት, Reuters

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

የእስራኤል መከላከያ ሚኒስትር እስራኤል ካትስ አገራቸው "በሰንዓ በሚገኙ የሁቲ አሸባሪ ድርጅት የሽብር ዒላማዎች ላይ ኃይለኛ ጥቃት አድርሳለች" ሲሉ ኤክስ ላይ ጽፈዋል።

የአይዲኤፍ በመግለጫው እንዳስታወቀው ዒላማ ከተደረጉት ውስጥ የሁቲ ወታደራዊ ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ዋና መስሪያ ቤት፣ የደህንነት እና የስለላ ተቋማት፣ የሁቲዎች "ወታደራዊ የሕዝብ ግንኙነት ዋና መስሪያ ቤት" እና የጦር መሳሪያዎችን ለማከማቸት የሚያገለግሉ ወታደራዊ ማዕከላት ይገኙበታል።

"የመከላከያ ኃይሉ የሁቲ አሸባሪ መንግስት በእስራኤል መንግሥት ላይ እያደረሰ ያለውን ተደጋጋሚ ጥቃቶችን በመቃወም በሁቲ አገዛዝ ላይ በቅርቡ ተጨማሪ የማጥቃት ዘመቻዎችን ያደርጋል" ሲል አክሏል።

የእስራኤሉ ጦር በሰጠው ሌላ መግለጫ እንዳስታወቀው ረቡዕ ዕለት የሁቲዎች በኢላት ላይ ያደረሱትን ጥቃት በተመለከተ በተደረገው ምርመራ ከየመን የተወነጨፈው ሰው አልባ አውሮፕላንን በአንጻራዊነት ዘግይቶ እንዳወቀው እና በፕሮቶኮሉ መሠረት የማስጠንቀቂያ ደውል እንዲሰማ ተደርጓል ብሏል።

"አይረን ዶም (የአየር መከላከያ ዘዴ) በመጠቀም የመጥለፍ ሙከራዎች ተደርገዋል፤ ነገር ግን አልተሳካም። መንስኤው ተለይቷል፤ የማስተካከያ እርምጃዎችም ተተግብረዋል" ሲል አክሏል።

በጋዛ ጦርነት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ የእስራኤል ጦር በሁቲዎች ወደ እስራኤል ከተነሱት ሰው አልባ አውሮፕላኖች ውስጥ ከ98 በመቶ በላይ የሚሆኑትን መጥለፋቸውን አይዲኤፍ አስታውቋል።

የሁቲ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ጥቃቱ "ጠላት የሆነችው እስራኤል በጋዛ ሰርጥ፤ በሕዝባችን ላይ ለፈጸመችው የዘር ማጥፋት ወንጀል እና አደገኛ መባባስ ምላሽ ለመስጠት ነው" ብሏል።

መስከረም 10 የሁቲ ሰው አልባ አውሮፕላኖች በኢላት ራሞን አውሮፕላን ማረፊያ ላይ ባደረሱት ጥቃት አንድ ሰው ከቆሰለ ከአራት ቀናት በኋላ የእስራኤል ጦር በሰነአ እና በአል-ጃውፍ ግዛት 35 ሰዎችን የገደለ ተከታታይ ጥቃት ፈጽሟል ሲል በሁቲ የሚመራው የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር አስታውቋል።

የጋዜጠኞች መብት ተሟጋቹ (ሲፒጄ) ባለፈው ሳምንት እንዳስታወቀው በሰነአ ከተገደሉት መካከል 31 ጋዜጠኞች እና የሚዲያ ሠራተኞች እንደሚገኙበት እና ክስተቱ በዓለም አቀፍ ደረጃ በፕሬስ ላይ በ16 ዓመታት ውስጥ ታይቶ የማይታወቅ አሰቃቂ ጥቃት ነው ብሏል።

የየመን ሴፕቴምበር 26 ጋዜጣ ከአንዱ በስተቀር ሁሉም በቢሮው ወይም በመንግስት የሞራል መመሪያ ዳይሬክቶሬት ዋና መሥሪያ ቤት ውስጥ ይሠሩ እንደነበር ገልጿል።

የእስራኤል ጦር በወቅቱ "የሁቲ የሕዝብ ግንኙነት መምሪያን" ዒላማ አድርጌያለሁ ብሏል።