ለ10 ሰዓታት ባህር ውስጥ የቆየችው ሴት

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ለ10 ሰዓታት በባህር ላይ ህይወትዋን ማቆየት የቻለችውነ ሴት የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች ህይወቷን ሊታደጓት ችለዋል።
ካይ ሎንግስታፍ የተባለችው እንግሊዛዊት ከክሮሺያ ባህር ዳርቻ ከተነሳው መርከብ ላይ ነበር አድዓቲክ በተሰኘ ባህር ላይ የወደቀችው።
የአካባቢው ባለስልጣናት እንደተናገሩት፤ የ46 ዓመቷ ሴት ባህር ውስጥ ከወደቀች ከ10 ሰዓታት ቆይታ በኋላ ነበር የባህር ዳርቻ ጠባቂዎች የታደጓት።
ወደ ሆስፒታል ከተወሰደች በኋላ ''ከመውደቄ በፊት በመርከቡ ጫፍ ላይ ተቀምጬ ነበር። ህይወቴ በመትረፏ በጣም እድለኛ ነኝ'' ብላለች።
ኤችአርቲ ለተባለ የክሮሺያ መገናኛ ብዙሃን ጨምራ እንደተናገረችው ''የባህር ዳርቻው ጠባቂዎች እኔን ከመታደጋቸው በፊት፤ ለ10 ሰዓታት በቀዝቃዛው ባህር ውስጥ ነበርኩኝ'' ብላለች።
ዘሰን የተባለው ጋዜጣ ካይ ሎንግስታፍ ከታደጓት የባህር ዳርቻ ሰራተኞች አንዱ እንደነገረኝ ብሎ እንደዘገባው ካይ ''ዮጋ መስራቴ ለረዥም ሰዓታት መንሳፈፍ እንድችል ረድቶኛል እንዲሁም ቅዝቃዜውን ለመርሳት ስዘፍን ነበር'' ብላለች ብሏል።
ካይ 291 ሜትር ርዝመት ካለው መርከብ ላይ የወደቀች ሲሆን የባህር ዳርቻው ጠባቂዎች ካይን ከመርከቧ 2 ኪ.ሜ. እርቀት ላይ ነበር ያገኟት።
ባህር ጠላቂዎች እንደሚሉት ከሆነ ካይ 291 ሜትር ርዝመት ካለው መርከብ ላይ ስትወድቅ ቢያንስ እስከ 4 ሜትር ድረስ ልትሰምጥ ትቻላለች።
በባህሩ ላይ የነበረውን ማዕበል ተቋቁማ ህይወቷን ማትረፏ በርካቶችን አስገርሟል።












