በቱርክ 'የጠፋ' ግለሰብን ለመፈለገ በተሰማራ ቡድን ውስጥ ተፈላጊው እራሱን ሲፈልግ ተገኘ

በቱርክ 'የጠፋ' ግለሰብን ለመፈለገ በተሰማራ ቡድን ውስጥ ተፈላጊው ራሱ የቡድኑ አባል ሆኖ ተገኘ።
በቱርክ የገባበት ያልታወቀን አንድ ግለሰብ ለመፈለግ በተሰማራው ቡድን ውስጥ ተፈላጊው እርሱ እንዳልሆነ ያልተገነዘበው ግለሰብ ቡድኑን ተቀላቅሎ ራሱን ሲፈልግ መቆየቱን የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙሃን ዘግበዋል።
የነገሩ መነሻ ቤይሃን ሙትሉ የተባለው ግለሰብ ባለፈው ማክሰኞ በቱርክ ቡርሳ ግዛት ከጓደኞቹ ጋር እየጠጡ በደን ወደ ተሞላ ስፍራ ይሄዳሉ።
ሆኖም ቤይሃን ሙትሉ ወደ ቤቱ መመለስ አልቻለም። ይህን ተከትሎ ባለቤቱ እና ጓደኞቹ የቤሃንን መጥፋት ለአካባቢው ባለስልጣናት አሳወቁ። እናም የፋለጋ ቡድን ተሰማራ።
የ50 ዓመቱ ተፈላጊም የጠፋን ግለሰብ ለመፈለግ የተሰማራውን ቡድን በመንገዱ ላይ ተመለከተና ሊቀላቀላቸው ወሰነ።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ
ፍለጋው ተጀመረ። የፍለጋ ቡድኑ አባላት የጠፋውን ሰው ስም መጥራት ሲጀምሩ ከምንገድ የተቀላቀላቸውና ተፈላጊው ሰው "አቤት እዚህ ነኝ" ሲል መለሰ።
እሱ መሆኑ ሲታወቅ ቃሉን እንዲሰጥ ከአንድ የፍለጋ ቡድኑ አባል ጋር ወደ ሌላ ቦታ ተወሰደ።
በቃሉም " [የፓሊስ]መኮንን ከባድ ቅጣት አይቅጡኝ። አባቴ ይገድለኛል" ማለቱ ተነግሯል።
ከዚያም ፖሊስ ሙትሉን ወደ ቤት ሸኝቶታል። ግን ራሱን ሲፈልግ የነበረው ግለሰብ ቅጣት ይጣልበት አይጣልበት የታወቀ ነገር የለም።












