ኮካ ኮላ ፌስቡክና ሌሎች ገፆች ላይ ማስታወቂያ ማስነገር አቆመ

የፎቶው ባለመብት, EPA
ኮካ ኮላ ለሚቀጥሉት 30 ቀናት በማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ላይ የሚያሰራውን ማስታወቂያ እንደሚያቋርጥ አስታወቀ።
ድርጅቱ ይህን የሚያደርገው ማኅበራዊ ሚድያዎች የጥላቻ ንግግርን እንዲቆጣጠሩ ጫና ለማሳደር ነው።
የኩባንያው ዋና ሥራ አስኪያጅ ጄምስ ክዊንሲ "ዓለም ለዘረኝነት ቦታ ሊኖራት አይገባም፤ ማኅበራዊ ድር-አምባዎችም ለዘረኝነት ቦታ ሊኖራቸው አይገባም" ሲሉ ተደምጠዋል።
ማኅበራዊ የትስስር መድረኮች ትልቅ ኃላፊነት አለባቸው፤ ግልፅ ሊሆኑም ይገባል ብለው ሥራ አስኪያጁ።
ግዙፉ የማኅበራዊ ትስስር መድረክ ፌስቡክ ጉዳት ሊያደርሱ የሚችሉ መረጃዎችንና ሐሰተኛ ወሬዎችን አጋልጣለሁ ብሏል።
የፌስቡክ ፈጣሪ ማርክ ዛከርበርግ የእሱ ድረ-ገፅ ላይ የሚለጠፉ ማስታወቂያዎች "ለተወሰነ የሰው ልጅ ጎሳ፣ ዜጋ፣ እምነት፣ ፆታ፣ ወይንም የስደት ሁኔታ" የሚያዳሉ ከሆነ አግዳለሁ ብሏል።
በመገናኛ መድረኮች ላይ የሚወጡ የጥላቻ ንግግሮችን ለመቃወም እየተካሄደ ያለው (#StopHateforProfit) ዘመቻ አስተባባሪዎች ፌስቡክ የጥላቻ ንግግርና ሐሰተኛ መረጃዎች እንዳይሰራጩ የድርሻውን አልተወጣም ሲሉ ይወቅሳሉ።
ከ90 በላይ ድርጅቶች የዚህን እንቅስቃሴ ሐሳብ በመደገፍ ምርታቸውን ማስተዋወቅ አቁመዋል።
ነገር ግን ኮካ ኮላ ማስታወቂያዎቹን ፌስቡክ ላይ ማስነገር ማቆሙ ዘመቻውን ተቀላቅሏል ማለት አይደለም ሲል ሲኤንቢሲ ለተሰኘው የቴሌቪዥን ጣብያ አሳውቋል።
ሥራ አስኪያጁ በዓለም ደረጃ ማኅበራዊ ትስስር መድረኮች ላይ የሚያደርጉትን የማስታወቂያ ሥራ አቁመው ስለ ማስታወቂያ ፖሊሲያቸው የወደፊት ዕጣ ፈንታ ሊያጤኑ እንደሆነ ተናግረዋል።
ልብስ አምራቹ ሊቫይ ስትራውስ ፌስቡክ ላይ ማስታወቂያ ማስነገር አቁሚያለሁ ብሏል። ድርጅቱ የዛከርበርግ ፌስቡክ ጠንካራ አቋም የለውም ሲል ወቅሷል።
"ፌስቡክ ዘላቂ ለውጥ ለማምጣት ቆራጥ እንዲሆን እንጠይቃለን" ብለዋል የድርጅቱ የማስታወቂያ ክፍል ኃላፊ ጄን ሰይ።
ታላላቅ ተቋማት በጸረ ጥላቻ ንግግር እንቅስቃሴ ውስጥ እኣካሄደ ያለው ጥምረት ዛከርበርግ ከዚህ የበለጠ እርምጃ እንዲወስድ አሳ












