ዕውቁ አሜሪካዊው ተዋናይ ዘ ሮክ በሚስጢር ተሞሸረ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
እውቁ አሜሪካዊ ተዋናይና ፕሮድዩሰር ድዋይን ዳግላስ ጆንሰን፤ በቅፅል ስሙ 'ዘ ሮክ' በህዋይ በተካሄደ ሚስጢራዊ የሠርግ ሥነ-ሥርዓት ለረዥም ዓመታት ፍቅረኛው ከነበረችው ሎረን ሃሺያን ጋር በጋብቻ መተሳሰሩ ተነገረ።
የ47 ዓመቱ ጎልማሳ ዘ ሮክ ይህንን ዜና ይፋ ያደረገው 154 ሚሊየን ተከታዮች ባሉት የኢንስታግራም ገፁ ላይ ነው።
ጥንዶቹ ላለፉት 13 ዓመታት የዘለቀ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን ግንኙነቱን የጀመሩት 'ዘ ጌም ፕላን' የተሰኘውን ፊልሙን በመቅረፅ ላይ ሳለ ነበር፤ ከዚያም የሁለት ልጆች ወላጆች ለመሆን በቅተዋል።
ታዲያ ይህንን ሚስጥራዊ የሠርግ ሥነ ሥርዓታቸውን የሚያሳየው ፎቶግራፍ በኢንስታግራም ከተለቀቀ በኋላ በሦስት ሰዓታት ውስጥ ከሰባት ሚሊየን በላይ ሰዎች ወደውታል።
ይህ ጽሑፍ በInstagram. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የInstagram ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ Instagram ይዘት መጨረሻ

የዓለማችን ዝነኛ የፊልም ኮከብ ዘ ሮክ [በመዝገብ ስሙ ድዋይን ጆንሰን] ከሆሊውድ እውቅ ተዋናዮች የእንኳን ደስ አለህ መልዕክቶችም ጎርፈውለታል።
በፎቶግራፉ ላይ አስተያየታቸውን ከሰጡት የሆሊውድ ኮከቦች መካከል ራያን ሬይኖልድስ፣ ካረን ጊላን፣ ፒ ዲዲ፣ ጀሲካ ቸስቴይን፣ እና ናኦሚ ካምፕቤል ይገኙበታል።
ባለቤቱ ሎረን በ1980ዎቹ በነበሩት ሙዚቃዎች በቦስተን ባንድ በተሰራው 'ሞር ዛን ኤ ፊሊንግ' ሙዚቃ አባቷ ድራም ተጨዋች ነበሩ። እሷም ሙዚቀኛ ስትሆን በኦንላይን በምትለቃቸው የሙዚቃ ሥራዎች ትታወቃለች።
ይህ ለ ዘ ሮክ ሁለተኛ ጋብቻው ነው ። ከመጀመሪያው ሚስቱ ዳኒይ ጋርሺያ ጋር በአውሮፓዊያኑ 1997 ትዳር መስርተው 18 ዓመት ወጣት ልጅ አድርሰዋል።















