246 የኮኬይን ከረጢቶችን የዋጠው ግለሰብ አውሮፕላን ላይ ሞተ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ከሜክሲኮ ከተማ በተነሳው አውሮፕላን ተሳፋሪ የነበረው ጃፓናዊ 246 ከረጢት ኮኬይን በመዋጡ ሕይወቱ ሊያልፍ ችሏል።
በዚህም ምክንያት በረራው በጃፓኑ ናሪታ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፍ የሚጠበቅበት ቢሆንም በሜክሲኮዋ ሶኖራ ግዛት ለማረፍ ተገዷል።
ባለስልጣናት እንዳሉት ዩዶ ኤን የተባለው ግለሰብ ሆዱ ውስጥ በደበቀው ዕፅ ምክንያት ጭንቅላቱ ውስጥ ባጋጠመው የፈሳሽ መጠራቀም ሳቢያ ሊሞት ችሏል።
ይህ ግለሰብ ከኮሎምቢያ ዋና ከተማ ቦጎታ የጀመረውን ጉዞ ቀይሮ ወደዚህ በረራ እንደገባም ታውቋል።
የሶኖራ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በሰጠው መግለጫ መሠረት የእፅ ከረጢቶቹ 2.5 ሴንቲ ሜትር ርዝመትና 1 ሴንቲ ሜትር ስፋት አላቸው። በግለሰቡ ላይ በተደረገው የውስጥ አካል ምርመራም እነዚህ ከረጢቶች በግለሰቡ ሆድና አንጀት ውስጥ እንደታዩ ተነግሯል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ

አውሮፕላኑ በህረሞሲሎ ከተማ በድንገት ካረፈ በኋላ ቀሪዎቹ 198 ተሳፋሪዎች ጉዟቸውን እንደገና መቀጠላቸውም ተገልጿል።
የሜክሲኮ ባለስልጣናት ጉዳዩን በመመርመር ላይ ይገኛሉ።














