ዩናትድ ማርቲኔዝን ለማስፈረም ተስማማ የሚሉ እና ሌሎች የዝውውር ዜናዎች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
የአውሮፓ ታላላቅ ክለቦች ከፍተኛ ገንዘብ በማውጣት ተጫዋቾችን ለማዘዋወር ድርድርና ስምምነት እያደረጉ ነው። እነ ማን ወዴት ሊያቀኑ ይችላሉ? ከስምምነት የደረሱስ እነማን ናቸው?
ማንችስተር ዩናይትድ የግራ መስመር ተጫዋች የሆነውን ሊሳንድሮ ማርቲኔዝን ለማስፈረም ከአያክስ ጋር መስማማቱ ተዘግቧል።
ዩናትድ ለአርጀንቲናውው ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ 45 ሚሊዮን ፓዎንድ ይከፍላል ተብሏል።
የዩናትድ አሰልጣኝ ኤሪክ ቴን ሃግ፣ ማርቲኔዝ ወደ ዩናይትድ እንዲመጣ ያግባቡት፤ አርሰናል ተጫዋቹን ለማስፈረም ከጫፍ ከተቃረበ በኋላ ነው የሚሉ ዘገባዎች በስፋት ወጥተዋል።
ሊሳንድሮ ማርቲኔዝ በዩናትድ ቤት ለመቆየት ሲስማም በዚህ የዝውውር መስኮት ለቀያዮቹ ሴጣኖች ፊርማቸውን ያኖሩ ተጫዋቾችን ቁጥር ወደ ሦስት ከፍ ያደርገዋል።
ቴይለር ማላሲያ ከቀናት በፊት እንዲሁም ክርስቲያን ኤሪክሰን ትናንት አርብ ሐምሌ 08/2014 ዓ.ም. ዩናይትድን በይፋ ተቀላቅሏል።
ዴንማርካዊው የቀድሞ የአያክስ፣ ቶተነሃም፣ ኢንተር ሚላን እና ብሬንትፎርድ አማካይ ኤሪክሰን በኦልድትራፎርድ ሦስት ዓመት ለመቆየት በነጻ ተዘዋውሯል።
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 1
ኩሊባሊ ወደ ቼልሲ
ቼልሲ ሴኔጋላዊውን የመሃል መስmር ተከላካይ ኩሊባሊን ከናፖሊ አስፈርሟል።
የ31 ዓመቱ ኩሊባሊ በቼልሲ 4 ዓመት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል። ቼልሲ በርካታ ልምድ ያለውን አንጋፋ ተከላካይ ያስፈረመው፤ አንቶኒ ሩዲገርን ለሪያል ማድሪድ እንዲሁም አንድሪያስ ክርስተንሰን ለባርሴሎና በነጻ ዝውውር አሳልፎ ከሰጠ በኋላ ነው።
ኩሊባሊ የሴኔጋል ብሔራዊ ቡድን አጋሩን እና የቼልሲ ግብ ጠባቂ ኤዱዋርድ ሜንዲን ካነጋገረ በኋላ ቼልሲን የመቀላቀል “ውሳንዬ ቀላል ሆኗል” ብሏል።
ራፊኒያ ወደ ባርሴሎና
ይህ ጽሑፍ በX. የቀረበ ይዘት ይዟል። ገጹ ቴክኖሎጂዎች ወይም ኩኪዎች ሊኖረው ስለሚችል ገጹ ከመከፈቱ በፊት የእርስዎን ፍቃድ እንጠይቃለን። ፍቃድዎን ከመስጠትዎ በፊት የX ኩኪ ፖሊሲ እና የ ማንበብ ይፈልጉ ይሆናል። ይዘቱን ለማንበብ ‘እቀበላለሁ ቀጥል’ የሚለውን ይምረጡ።
የ X ይዘት መጨረሻ, 2
በመጨረሻም ብራዚሊያዊው ራፊኒያ ወደ ባርሴሎና ማቅናቱ ይፋ ሆኗል።
በሊድስ ዩናይትድ ቆይታው አስደናቂ ብቃት ያሳየው ራፊኒያ በቅደሚያ ከአርሰናል ቀጥሎ ከቼልሲ ጋር ስሙ በስፋት ተያይዞ ነበር። እንዲያውም ክለቡ ሊድስ በራፊኒያ ሽያጭ ዙሪያ ከቼልሲ ጋር ከስምምነት ደርሶም ነበር ተብሏል።
ተጫዋቹ ግን መዳረሻው ባርሴሎና እንዲሆን በመፈለጉ ምክንያት የቼልሲ እና የአርሰናል ዝውውር ጥረት ሳይሳካ ቀርቷል።
የ25 ዓመቱ ራፊኒያ 55 ሚሊዮን ፓዎንድ በሚጠጋ ገንዘብ ባርሳን ከተቀላቀለ በኋላ፤ “ከልጅነቴ ጀምሮ የነበረን ሕልሜ ነው የተሳካው” ብሏል።

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ሌሎች የዝውውር ጭምጭምታዎች
አርሰናል ዩክሬናዊውን የማንችስተር ሲቲ ተጫዋች ኦሌክሳንደር ዚንቼንኮን ለማስፈረም ተቃርቧል ሲል ኢኤስፒኤን ዘግቧል።
የ25 ዓመቱ ዚንቼንኮ ስሙ ከአርሰናል ጋር መያያዝ ከጀመረ ሰነባብቷል። ሲቲ ከብራይተን ኩኮሪያልን የሚያስመጣ ከሆነ፤ የማሃል እና ግራ መስመር ተከላካይ እንዲሁም አማካይ ሆኖ መጫወት ይችላል የሚባልለት ዚንቼንኮ ወደ አርሰናል ማቅናቱ አይቀርም እየተባለ ነው።
መድፈኞቹ ሪኮርድ በሆነ ገንዘብ ያስፈረሙትን ውዱ ተጫዋቻቸውን በዚህ የውድድር ዘመን ለመሸጥ ፍላጎት አላቸው።
አይቮሪ ኮስታዊው ኒኮላስ ፔፔ ገዢ ካገኘ አርሰናል ለመሸጥ ዝግጁ የሆነ ይመስላል። የ27 ዓመቱ ፔፔ በ72 ሚሊዮን ፓዎንድ ወደ አርሰናል ከመጣ በኋላ የሚጠበቅበትን መወጣት አልቻለም።
በቀጣይ የውድድር ዘመን የአሠልጣኝ ሚኬል አርቴታ ዕቅድ ውስጥም የለም ተብሏል።
ሊንጋርድ ወደ ሳዑዲ?
ዴይሊ ስታር በማንችስተር ዩናይትድ የነበረው ውል የተጠናቀቀው ጄሲ ሊንጋር ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያቀና ይችላል ብሏል።
የ29 ዓመቱ ሊንጋርድ በዚህ የዝውውር መስኮት ስሙ ከኤቨርተን እና ዌስት ሃም ዩናይትድ ጋር በተደጋጋሚ ሲነሳ የቆየ ቢሆንም ባልተጠበቀ ሁኔታ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሊያቀና ይችላል ተብሏል።
ሊንጋር ስሙ ያልተጠቀሰውን የሳዑዲ ክለብ የሚቀላቀል ከሆነ በዓመት 10 ሚሊዮን ፓዎንድ ሊከፈለው ይችላል ተብሏል።
ኤቨርተን እና ኮርኔት
ኤቨርተን በ2021/22 ከፕሪሚየር ሊጉ ከወረደው በርንሌይ አይቮሪ ኮስታዊውን የክንፍ መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ፍላጎት አለው ሲል ዘ አትሌቲክ ዘግቧል።
ማክስዌል ኮርኔት ባለፈው የውድድር ዓመት ድንቅ ብቃት ቢያሳይም ክለቡን ከመውረድ መታደግ አልቻለም።
የ25 ዓመቱ የክንፍ ተጫዋች የፍራንክ ላምፓርድ ቡድንን እንዲቀላቀል ኤቨርተን እና በርንሌይ ንግግር ላይ ናቸው ብሏል ዘ አትሌቲክ።












