ተመራጩ የኬንያ ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ማን ናቸው?

ዊሊያም ሩቶ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ዊሊያም ሩቶ

የኬንያ ምርጫ ኮሚሽን በ2022 ብሔራዊ ምርጫ ለአስር ዓመታት አገሪቱን በምክትል ፕሬዝዳንትንት የመሩት ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ ቀጣይ ፕሬዝዳንት ሆነው መመረጣቸውን አሳውቋል።

ዊሊያም ሩቶ ከባድ ፉክክር በተካሄደበት ምርጫ ከቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ ጋር ተወዳድረው ነው በጠባብ የድምጽ ልዩነት ፕሬዝዳንታዊውን ምርጫ ማሸነፋቸው ይፋ የተደረገው።

**

የዊልያም ሩቶ የልጅነት ሕይወት የብዙ ደሃ ኬንያውያንን ታሪክ ነው ማለት እንችላለን።

በባዶ እግራቸው ነው ትምህርት ቤት የገቡት።

ጫማ ጋር የተዋወቁት 15 ዓመት ሲሞላቸው ነው። በስምጥ ሸለቆ ገጠራማ አካባቢዎች ዶሮና ለውዝ በመንገድ ዳር ቁጭ ብሎ ሸጠዋል።

ሩቶ ኬንያ ኩዋንዛ የሚል መርህ ይዘው ነበር የተነሱት። በሃገርኛው ስዋሂሊ ኬንያ ትቅደም ወይም መጀመሪያ ለኬንያ እንደማለት ነው። ምጣኔ ሃብቱንም ለማሳደግ ቃል ገብተዋል።

በኬንያ ዕድሜያቸው ከ18 እስከ 34 ዓመት በሆኑት ዘንድ የሥራ አጥነት መጠኑ 40 በመቶ ይጠጋል። በየዓመቱ ወደ ሥራ የሚገቡትን 800,000 ወጣቶች ለመያዝ የሚችል ምጣኔ ሃብት አልተፈጠረም።

ስለዚህም ኑሮአቸውን ለማሸነፍ የሚታገሉትን ወጣቶችን በማሰብ “ትጉ ሃገር” የሚል ሐረግ ይዘው መጥተዋል።

ለምጣኔ ሃብቱ ከታች ወደ ላይ የሚዘልቅ ሃሳብ ማምጣታቸውንም እየገለጹ ይገኛሉ። የኮሮናቫይረስ እና የዩክሬን ጦርነትን ያናረው የኑሮ ውድነት ለተጫናቸው ዜጎች እንደሚጠቅም ቃል ገብተዋል።

ይህ ለ55 ዓመቱ ፕሬዚዳንት የመጀመሪያ ሥራቸው ይሆናል። ዕድል ከእሳቸው ጎን ሆና እንዲመረጡም ምኞታቸው ነው። እአአ በ1997 ዕድል ከእሳቸው ጋር ነበረች። በወቅቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ተወዳድረው የሰሜን ኤልዶሬት ምርጫ ክልል የህዝብ እንደራሴ ለመሆን በቅተዋል። አሁንም ተመሳሳይ እድል ይጠብቃሉ። 

ሩቶ ደጋፊዎቻቸውን መሰብሰብ ተክነውበታል

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ሩቶደጋፊዎችንመሰብሰብተክኖበታል

ሩቶ እና ፖለቲካ የተዋወቁት እአአ በ1992 ነው። በወቅቱ ፕሬዚዳንት ከነበሩት ዳንኤል አራፕ ሞይ ምክርና ትምህርት መቅሰማቸው ይነገራል።

በአንድ ወቅት በወጣቶች የተሞላው የአራፕ ሞዩ የካኑ ፓርቲ አካል ነበሩ። በተመሳሳይ ዓመት በሃገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ለተካሄደው የመድብለ ፓርቲ ምርጫ መራጮችን እንዲሳተፉ ከሰሩ የህብረተሰብ አንቂዎች አንዱ ነበሩ።

ጥሩ ተናጋሪ በመሆናቸው ይታወቃሉ። በዚህ ምክንያት በድጋፍ ሰልፎች ላይ ብዙ ህዝብ ይሰበሰብላቸዋል። ለመገናኛ ብዙኃን ጥያቄዎች በሚሰጠው ምላሽም ጥሩ ተናጋሪ መሆናቸውን አስመስክረዋል።

ብዙ ጊዜ "ጓደኛዬ" ብለው መናገር ይቀናቸዋል። ይህም ከመራጮች ጋር ጥሩ ግንኙነት ለመፍጠር እና የተቺዎችን ልብ ለመብላት ረድቷቸዋል።

ሩቶ እና ኬንያታ ጠንካራ ግንኙነት ነበራቸው

የፎቶው ባለመብት, AFP

የምስሉ መግለጫ, ሩቶእናኬንያታጠንካራግንኙነትነበራቸው

አሰላለፍን መቀየር

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

የተለያዩ የሚንስትርነት ወንበሮችን ይዘዋል። ከ2013 ወዲህ ደግሞ ምክትል ፕሬዝዳንት ናቸው።

በወቅቱ ምርጫ ብዙዎች ተደናግጠው ነበር። ምክንያት ከተባለ የስልጣን ዘመናቸው ሊጠናቀቅ ጥቂት ወራት የቀራቸው የፕሬዝዳንት ኬንያታ ምክትል ሆነው በመከሰታቸው ነው። ከዚያ በፊት ሁለቱ ኬንያውያን በተቃራኒ ጎራ ተሰልፈው ነበር።

ኬንያውያን የ2007ቱን ምርጫ አይረሱትም። አወዛጋቢ የነበረውን ምርጫ ተከትከሎ 1,200 የሚጠጉ ሰዎች ተገድለዋል። ሩቶ እና ኬንያታም በዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት በሰብዓዊነት ላይ በተፈጸሙ ወንጀሎች ምከንያት ክስ ተከፍቶባቸው ነበር። ሩቶ በወቅቱ ተቃዋሚ ከነበሩት ከራይላ ኦዲንጋ ጎን ተሰለፉ። አሁን ኦዲንጋ እና ሩቶ በተቃራኒ መንገድ መጥተው ለፕሬዝዳንትነት ተፋጠዋል። ኬንያታ ደግሞ በድጋሚ ለመመረጥ የተወዳደሩትን ፕሬዝዳንት ምዋዪ ኪባኪን ደግፈው ቆመው ነበር። 

ሁለቱ ሰዎች በስልጣን ላይ ሲወጡ የነበራቸው ጥምረት ፍሬያማ ነበር። ወንድማዊ ፍቅር የተባለለት ጠንካራ ግንኙነት ፈጠሩ። የአይሲሲን ክስ ጭምር ለመከላከል ቻሉ። ዓቃቤ ህግ እአአ በ 2014 በፕሬዚዳንት ኬንያታ ላይ የመሰረተውን ክስ አቋረጠ። ዳኞች ​​ሩቶ ላይ የተመሰረተውን ክስ ደግሞ በ2016 ውድቅ አድርገውታል።

ግንኙነቱ ግን አልዘለቀም። ኬንያታ እአአ በ 2018 በሌላ አስደናቂ የአሰላለፍ ለውጥ ፈጠሩ። ከኦዲንጋ ጋር ታረቁ። ሩቶ ላይ ደግሞ ፊታቸውን አዞሩ። ተሰናባቹ ፕሬዝዳንት በነሐሴው ምርጫ ተተኪያቸው እንዲሆኑ ኦዲንጋን እንደሚደግፉ ይፋ አደረጉ። ኦዲንጋን አለሁልህ ሲሉ የሩቶን ተስፋ አጨለሙ።

የፕሬዚዳንቱ ደጋፊዎች ሩቶን ለአለቃቸው ታዛዥ አይደሉም ሲሉ ይከስሳሉ።

ምክትል ፕሬዝዳንቱ ውንጀላውን ያስተባብላሉ።

በሁለቱ መካከል ፍጥጫ መኖሩን አምነዋል። እሳቸውና ፕሬዝዳንቱ "ፖለቲካን የሚያዩበት መንገድ ነው" የተለያየ መሆኑን ጠቅሰዋል።

ሩቶ በምክትል ፕሬዝዳንትነታቸው ቀጥለዋል። ምስጋና ዋስትና ለሚሰጠው ህገመንግስት።

ሩቶ ወጣቶችን ለማበረታታት ጋሪዎችን ሰጥተዋል

የፎቶው ባለመብት, KENYA DEPUTY PRESIDENT OFFICE

የምስሉ መግለጫ, ሩቶወጣቶችንለማበረታታትጋሪዎችንሰጥቷል

የሰፋፊ መሬት ባለቤቱ እና ጥንቁቁ ገበሬ

በኬንያ ፖለቲካ ብሔር ትልቅ ሚና አለው። ሩቶ በህዝብ ቁጥር ሦስተኛው ከሆነው ካላንጂን ብሔር የመጣ ነው። ከካሌንጂን አንድ ፕሬዝዳንት ብቻ ሃገሪቱን መርቷል። ኬንያ ለረዥም ጊዜ የመሩት አራፕ ሞይ ናቸው።

ሩቶ ከራቼል ጋር ትዳር መስርተዋል። ለመጀመሪያ ጊዜ የተገናኙት በቤተ ክርስቲያን የወጣቶች ህብረት ላይ ነው።

ስድስት ልጆች አፍርተዋል። ኒክ የበኩር ልጃቸው ነው። በአንድ ወቅት በካሌንጂን ሽማግሌዎች መባረኩ ለፖለቲካ ኃላፊነት እየታጨ ነው የሚል ግምት እንዲናፈስ አድርጓል። ሴት ልጃቸው ጁን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ተቀጣሪ ናት።

ሩቶ ለግብርና ከፍተኛ ፍቅር አላቸው። በበቆሎ፣ በወተት እና በዶሮ እርባታ ተሰማርተዋል።

በምዕራብ እና ጠረፋማ አካባቢዎች ሰፋፊ መሬቶች በስማቸው ይገኛሉ። በመስተንግዶ ዘርፍም መዋዕለ ንዋያቸውን አፍስሰዋል።

ሩቶ ከመንግስታዊ የሙስና ቅሌቶች ጋር ስማቸው ተደጋግሞ ይነሳል። በዚህ ምክንያት የሃብት ምንጩ ብዙ ጥያቄ ያስነሳባቸዋል።

እአአ በ2013 የሃገሪቱ ከፍተኛው ፍርድ ቤት በሰጠው ውሳኔ 40 ሄክታር የእርሻ መሬት እንዲያስረክብ ተወስኖባቸዋል። በ 2007 ድህረ-ምርጫ ብጥብጥ ወቅት መሬቱን ለነጠቀው ገበሬ ካሳ እንዲከፍሉም ተፈርዶባቸዋል።