የኬንያ ምርጫ ከሌሎች አገራት በተለየ ለምን ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ሆነ?
የኬንያ ምርጫ ከሌሎች አገራት በተለየ ለምን ከፍተኛ ወጪ የሚያስወጣ ሆነ?
ዛሬ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. እየተካሄደ ያለው ምርጫ አራት ዕጩዎች ለፕሬዝዳንትነት የሚፎካከሩበት ሲሆን፣ በተለይ በምክትል ፕሬዝዳንቱ ዊሊያም ሩቶና በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ራይላ ኦዲንጋ መካከል ጠንካራ ፉክክር የሚደረግበት ነው።
በዚህ ምርጫ ከአገሪቱ ሕዝብ ግማሽ የሚሆነው በመራጭነት ይሳተፋል። ከ22 ሚሊዮን በላይ መራጮች ለተመዘገቡበት ለዚህ ምርጫ ማካሄጃ ደግሞአገሪቱ 400 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ በጀት መድባለች።
በዚህም መሠረት ለእያንዳንዱ መራጭ 17 ዶላር ይወጣል ማለት ነው። ይህ ደግሞ ከሌሎች አገራትምርጫዎች ጋር ሲነጻጸር ከፍተኛ ወጪ ነው ተብሏል።
ከወጪ አንጻር ለምን የኬንያ ምርጫ ይህን ያህል ውድ ሆነ? ይህ ቪዲዮ ምላሽ አለው።



