የኬንያ ምርጫ 2022: በኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ምርጫ ላይ የሚፎካከሩት እነማን ናቸው?

ኬንያ ነሐሴ 03/2014 ዓ.ም. ለምታካሄደው ፕሬዝደንታዊ ምርጫ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪው ራይላ ኦዲንጋ እና ሥልጣን ላይ ያሉት ምክትል ፕሬዝደንት ዊሊያም ሩቶ መካከል ጠንካራ ፉክክር ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

ለኬንያ መሪነት የሚፎካከሩት እነማን ናቸው?

የኬንያ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩዎች

የሕይወት ታሪካቸውን ለማወቅ ዕጩ ይምረጡ

ራይላ አሞሎ ኦዲንጋ

አዚሚዮ ላ ኡሞጃ ኮአሊዥን

  • የ77 ዓመቱ ፕሬዝዳንታዊ ዕጩ ጀርመን ውስጥ በሚገኘው የማግደበርግ የቴክኖክ ዩኒቨርስቲ ምህንድስና ተምረዋል።
  • አዚሚዮ ላ ኡሞጃ ፓርቲን በመወከል ለፕሬዝዳንትነት ዕጩ ሆነው ቀርበዋል።
  • ባለፉት አራት ምርጫዎች ለፕሬዝዳንትነት የተወዳደሩ ሲሆን፣ የአሁኑ ለአምስተኛ ጊዜ ነው።
  • ኦዲንጋ በኬንያ ውስጥ ለብዝሃ ፓርቲ ዲሞክራሲ ከታገሉ ፖለቲከኞች አንዱ ናቸው። በዚህም ሳቢያ ተይዘው የታሰሩ ሲሆን፣ ለስደትም ተዳርገው ነበር።
  • ከ10 ዓመት በፊትም ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው አገልግለዋል።
  • ኦዲንጋ ሥልጣን ላይ በነበሩበት ጊዜ በገጠር ኤሌክትሪክ የማስፋፋት እና የመንገድ ግንባታዎች በስኬት መጠናቀቃቸው ይነገራል።
  • በአነስተኛ ንግድና በምርት ዘርፍ ኢንቨስትመንት አማካይነት ባለሁለት አሃዝ የኢኮኖሚ እድገት ለማስመዝገብ ችለዋል።
  • ጥራት ያለው ለሁሉም ተደራሽ የሆነ የጤና አገለግሎት።
  • ለሕዝቡ አካላዊ፣ አእምሯዊና ማኅበራዊ እድገት የስፖርት እና የመዝናኛ ተቋማትን ማስፋፋት።
  • በ1982 የተካሄደውን የመፈንቅለ መንግሥት ሙከራ ተከትሎ፣ ራይላ ኦዲንጋ ታይዘው፣ የአገር ክደት ወንጀልን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ክሶች ተመስርተውባቸው ነበር። ኦዲንጋ ከመፈንቅለ መንግሥቱ ዋነኛ መሪ ጋር ግንኙነት አላቸው ቢባልም፣ እሳቸው ግን ሁሌም ያስተባብላሉ። - የኬንያ ብሔራዊ ቤተመዛግብት

ዊሊያም ሳሞይ ሩቶ

ኬንያ ኩዋንዛ አሊያንስ

  • የ55 ዓመቱ ዊሊያም ሩቶ ከእጸዋት እና ከእንስሳት ሳይንስ ጋር በተያያዘ የዶክትሬት እና የቢኤስሲ ዲግሪ ከናይሮቢ ዩኒቨርስቲ አላቸው።
  • ሩቶ የኬንያ ክዋንዛ ፓርቲ አባል የሆነው ዩናይትድ አሊያንስ ፓርቲን ወክለው ለፕሬዝዳንትነት ይወዳደራሉ።
  • ስሙ በመጥፎ የሚነሳው 'ዩዝ ፎር ኬንያ' የተባለው ቡድን መሪ ነበሩ።
  • የግብርና ሚኒስትር እያሉ መሥሪያ ቤታቸው ከሁሉም በላቀ የሚጠበቅበትን በብቃት በማከናወን እውቅናን አግኝተዋል።
  • በ2010 (እአአ) በወጣው አዲሱ ሕገ መንግሥት የኬንያ ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት ሆነው አገልግለዋል።
  • ለ10 ዓመታት የኤልዶሬት አካባቢ እንደራሴ በመሆን የፓርላማ አባል ነበሩ።
  • ለትናንሽና ለመካከለኛ ተቋማት በዓመት 424 ሚሊዮን ዶላር ይመድባሉ።
  • የተለያዩ ወጪዎችን ለመሸፈን ብሔራዊ የትምህርት ድጋፍ ይመሰርታሉ።
  • በፖለቲካ ሹመት ሁለት ሦስተኛውን፣ በካቢኔያቸው ግማሹን ቦታ ሴቶች እንዲይዙ ያደርጋሉ።
  • ከአራት ዓመት በፊት የኬንያ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ የያዙትን 40 ሄክታር መሬት እንዲለቁ እና መሬቴ ተወስዶብኛል ብሎ ለከሰሳቸው ገበሬ 62,500 ዶላር እንዲከፍሉ ወስኗል። - የኬንያ ሕግ
  • ዊሊያም ሩቶ በ2011 (እአአ) በሰብአዊነት ላይ በተፈጸሙ ሦስት ወንጀሎች ተከሰው ዓለም አቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት (አይሲሲ) ቀርበው ነበር። ከአምስት ዓመት በኋላ ደግሞ ፍርድ ቤቱ የቀረቡባቸው ማስረጃዎች ደካማ ናቸው በማለት ክሱን አቋርጦታል። - አይሲሲ

ጆርጅ ዋጃኮያህ

ሩትስ ፓርቲ

  • የ61 ዓመቱ ፕሮፌሰር ጆርጅ ዋጃኮያህ ከዩናይትድ ኪንግደም ዋርዊክ እንዲሁም ከአሜሪካው ቦልቲሞር ዩኒቨርስቲዎች በተለያዩ የሕግ ትምህርቶች ሁለተኛ ዲግሪ አላቸው።
  • ዋጃኮያህ በዚህ ዓመቱ የኬንያ ምርጫ ላይ ሩትስ የተባለውን ፓርቲ ወክለው ለፕሬዝዳንትነት ይወዳደራሉ።
  • በቀድሞው ፕሬዝዳንት ዳንኤል አራፕ ሞይ የአስተዳደር ዘመን በመንግሥት ኃላፊነት ላይ የሰሩ ሲሆን፣ ኋላ ላይ ግን ከመንግሥት ጥቃት በመሸሽ ለስደት ተዳርገዋል።
  • ከአራት ዓመት በፊት ከሌሎች አጋሮቻቸው ጋር በመሆን የሕግ ተቋም መስርተዋል።
  • በአሜሪካ፣ በዩናይትድ ኪንግደም እና በኬንያ በሚገኙ ዩኒቨርስቲዎች ሕግና ኢኮኖሚክስ አስተምረዋል።
  • በኢንዱስትሪ የሚመረትን ማሪዋና ሕጋዊ ያደርጋሉ።
  • የሥራ ቀናት ከሰኞ አስከ ሐሙስ እንዲሆን ይደረጋል።
  • ለአዛውንቶች፣ አቅም ለሌላቸውና ለነፍሰጡር ሴቶች ነጻ የጤና ክብካቤ እና ድጋፍ ይሰጣል።

ዴቪድ ምዉሬ ዋይሂጋ

አጋኖ ፓርቲ

  • ዴቪድ ምዉሬ በምርጫው አጋኖ የተባለውን ፓርቲ ወክለው ለፕሬዝዳንትነት ውድድር ቀርበዋል።
  • የአጋኖ ፓርቲ መሪ ናቸው።
  • ከናይሮቢ ዩኒቨርስቲ በሕግ ዲግሪ ሲኖራቸው በአመራር ደግሞ ሁለተኛ ዲግሪ አግኝተዋል።
  • ልምድ ያላቸው የሕግ ባለሙያ ሲሆኑ፣ በዘርፉ ከ30 ዓመታት በላይ ሰርተዋል።
  • የሕግ ተቋም ያላቸው ሲሆን ከዚህ ቀደም ለተለያዩ የፖለቲካ የሥልጣን ቦታዎች ተወዳድረዋል።
  • አጋኖ ፓርቲን ከስምነት ዓመት በፊት ነበር የመሠረቱት።
  • በአገር ውስጥ ያለውን ሙስና መዋጋት።
  • ሥራ መፍጠር።
  • በውጭ አገራት ተከማችቷል የሚባለውን የአገሪቱን ሀብት ማስመለስ።