በዩናይትድ ኪንግደም ስደተኞች በሕገ-ወጥ መንገድ መታሰራቸው ተሰማ

የስደተኞች ማቆያ ስፍራ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

በዩናይትድ ኪንግደም በመቶዎች የሚቆጠሩ ስደተኞች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በስደተኞች ማቆያ እንደታሰሩ ቢቢሲ ያገኘው የአገር ውስጥ ጉዳዮች ቢሮ ኢሜይል አመላክቷል።

450 ሰዎችን መያዝ የሚችለው ማቆያ ማዕከል አሁን ከሚገባው በላይ ሰዎችን መያዙን የሚጠቁመው የኢሜይል መልዕክቱ፤ እሰሩ ህጋዊ አይደለም ካለ በኃላ “ወደ ሆቴሎች በፍጥነት ማዘዋወር አለብን” ሲል ገልጿል።

የአገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ስደተኞችን የያዙ ጀልባዎች ወደ ዩኬ እየገቡ መሆናቸው ጥገኝንት በመስጠት ሂደቱ ላይ ከፍተኛ ጫኛ ፈጥሯልም ብሏል።

ጨምሮም ቢሮው “ያለመሰልቸት በተቻለ ፍጥነት ሰዎችን ወደ ሆቴል እና ሌሎች ማረፊያዎች ለማዘዋውር” መሞከሩንም ጠቅሷል።

ይህ የኢሜይል ምልክት የተላከው ከሰማንታት በፊት ሲሆን የሀገር ውስጥ ጉዳይ ኃላፊዋ ሱኢላ ብሬቨርማን በማንስተን የሚገኘውን እና ስደተኞች ያሉበትን የተጨናነነቀ ስፍራ ከተመለከቱ በኃላ የተላከ ነው።

በዩኬ ባለው የመረጃ ነጻነት ህግ መሰረት የአገር ውስጥ ጉዳዮች ቢሮ ቋሚ ጸሃፊዎች በመልዕከት ሰንሰለቱ አማካኝነት በወቅቱ መረጃው ድርሷቸው ነበር።

ትይዩ የአገር ውስጥ ጉዳዮች ኃላፊ የሆኑት ዩቬት ኩፐር ኢሜይሉን “የአገር ውስጥ ጉዳይ እያወቁ ሕግ እንደጣሱ” አመላክቷል ብለዋል።

ጨምረውም “አሁን ስልጣን ላይ ባሉት የሀገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮ ሃላፊ አስተዳደር ስር ቢሮው ስርዓቱን መቆጣጠር አልቻለም" ካሉ በኋላ የአገር ውስጥ ጉዳይ ቢሮው የግብር ከፋዮችን ገንዘብ አባክኗል ብለዋል።

ባለፈው ጥቅምት ወር 4 ሺህ የሚሆኑ ሰዎች በማንስቱን በተጨናነቀ እና በሽታ ሊያስከትል በሚችል ሁኔታ እንደተያዙ ተገልጾ ነበር።

ከሳምንታት በፊት ከ450 እስከ 500 የሚሆኑ ጥገኝነት ጠያቂዎች ማንስተን ውስጥ በተፈጠረ መጨናነቅ ምክንያት ወደ ሌሎች ማቆያዎች መሸጋገራቸውን ተገልጿል።

ኢሜይሉ ተይዘው ሊቆዩ የሚገባቸው የስደተኞቹን ማንነታቸውን ለማውቅ አዳጋች ከሆነ ብቻ ነው ያለ ሲሆን ከፍተኛውም የመታሰሪያ ጊዜ አምሰት ቀን ብቻ ነው ብሏል። በዚህም ምክንያት እስሩ ህገውት እንደሆነ ጠቅሷል።

“አብዛኞቹ ለበርካታ ሳምንታት እና ከዛ በላይ ለሆነ ጊዜ በማንስተን ታሰረውዋል። ወደ ሆስቴል ልናዘዋውራቸው ይገባል” ሲል አክሏል።

ማንስተን የተዘጋጀው ወደ ዩኬ በአንስተኛ ጀልባ የሚመጡ ስድተኞችን በፍጥነት ለማስተናገድ ቢሆንም መርማሪዎች ቦታው በርካታ ሰዎች ለረጅም ጊዜ በስፍራው መጉላላታቸው ስጋት ጭሮባቸዋል።

በስፍራው በማይመች ሁኔታ ያሉ ስደተኞችን ስልጠና ያልወሰዱ ሰራተኞች አልፎ አልፎ ምልከታ እንደሚያደርጉላቸውም አመላክቷል።