ኬንያዊቷ የማራቶን ክብረወሰን ባለቤት ቼፕጌቲች ለሦስት ዓመታት እገዳ ተጣለባት

ኬንያዊቷ የማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ሩት ቼፕጌቲች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

የምስሉ መግለጫ, ኬንያዊቷ የማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ሩት ቼፕጌቲች

ኬንያዊቷ የማራቶን የዓለም ክብረወሰን ባለቤት ሩት ቼፕጌቲች አበረታች ቅመሞችን ደንብ መጣሷን አምና መቀበሏን ከትሎ ለሦስት ዓመታት ታገደች።

ቼፕጌቲች በመጋቢት ላይ ሃይድሮክሎሮቲያዛይድ (ኤችሲቲዜድ) መጠቀሟ በምርመራ በመረጋገጡ በጊዘያዊነት ታግዳ ነበር። በተለምዶ ኤችሲቲዜድ አበረታች ቅመሞችን ለመሸፈን ጥቅም ላይ ይውላል።

የቼፕጌቲች 2፡9፡56 በሆነ ሰዓት ክብረወሰን ያስመዘገበችበትን የቺካጎ ማራቶንን ጨምሮ ናሙናውን ከመወሰዱ በፊት የተመዘገቡ ስኬቶቿ አይሰረዙም።

ዘ አትሌቲክስ ኢንተግሪቲ ዩኒት (ኤአይዩ) የአራት ዓመት እገዳ እንዲጣልበት ቢጠይቅም የ31 ዓመቷ አትሌት ጥሰቶቹን አምና ስለተቀበለች ቅጣቱ ወደ ሦስት ዓመት ተቀንሷል።

ኤአይዩ ከቼንጌቲች ስልክ የተገኘውን ማስረጃ መመርመሩን ይቀጥላል ተብሏል። ይህም ከ2022 ጀምሮ የተጻፉ መልዕክቶችን እና "አውቃ ነው በደሟ ውስጥ አበረታች ቅመም መኖሩ እንዲረጋገጥ ያደረገችው" የሚለውን ይጨምራል።

የተቋሙ ኃላፊ ብሬት ክሎቲየር "የኤችሲቲዜድ ምርመራ ጉዳይ ተፈትቷል። ነገር ግን ኤአይዩ ሌሎች ጥሰቶች ተከስተው እንደሆነ ለማወቅ ከቼፕጌቲች ስልክ የተገኘውን አጠራጣሪ መረጃ መመርመር ይቀጥላል" ብለዋል።

'ማንም ከሕግ በላይ አይደለም'

ከሁለት ሰዓት ከአስር ደቂቃ በታች 10 ማራቶንን ለመሮጥ የመጀመሪያዋ ሴት ለመሆን የበቃችው ቼፕጌቲች በሚያዝያ ወር በኤአይዩ ቃለ መጠይቅ ሲደረግላት ስለምርመራው ውጤት ማብራሪያ መስጠት አልቻለችም።

Skip podcast promotion and continue reading
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናል

ዜና፣ ትንታኔ እና ታሪኮችን በምሥል እና በድምጽ ለማግኘት

ይህንን በመጫን ሰብስክራይብ ያድርጉ

End of podcast promotion

ኤችሲቲዜድ በአንድ ሚሊ ሊትር ሽንት ውስጥ ቢያንስ 20 ናኖግራም መኖር ሲገባው የቼፕንጌቲች ናሙና ግን 3,800 እንደሆነ ተገምቷል።

ከሁለት ሳምንት በፊት በተደረገ ምርመራም የኤችሲቲዜድ ምጣኔዋ አሳማኝ እንዳልነበር ተደርሶበታል።

በሐምሌ በተደረገላት ቃለ ምልልስ ወቅት ቼፕንጌቲች ከስልኳ የተገኙትን አጠራጣሪ ማስረጃዎች አቅርባለች። ብክለትን የተመለከተውን ጉዳይ ግን ኤአይዩ ውድቅ አድርጎታል።

ቼፕጌቲች በቀጣዩ ቃለመጠይቋ ሃሳቧን ቀይራ ከምርመራው ሁለት ቀን በፊት በመታመሟ ምክንያት ኤችሲቲዜድ የሚል የቤት ሠራተኛዋን መድሃኒት መውሰዷን ተናግራለች።

ኤአይዩ "በአዲሱ ጉዳይ ተዓማኒነት ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ ስለነበረው" እና ከስፖርቱ ፀረ-አበረታች ቅመሞች ሕጎች አንጻር እንዲህ ዓይነቱ "ግድየለሽነት ተዘዋዋሪ ዓላማ ስለሚኖረው የአራት ዓመት ማዕቀብ ይጨምራል" ተብሎ ይታሰባል።

ቼፕጌቲች የፀረ-አበረታች ቅመም ደንብ ጥሰቶችን በተመለከተ በተቀመጠው 20 ቀናት ውስጥ ካመነች በኋላ የአንድ ዓመት እገዳው ቅነሳ ተግባራዊ ተደርጎላታል።

የሶስት ዓመት እገዳው የሚጀመረው ሚያዝያ 19 ቼፕጌቲች ጊዜያዊነት እገዳን ከተጣለባት ጀምሮ ሲሆን ከመጋቢት 14 ጀምሮ የተመዘገቡ የአትሌቷ ውጤቶች፣ ሽልማቶች፣ ማዕረጎች በሙሉ ተሽረዋል።

የኤአይዩ ሊቀመንበር ዴቪድ ሃውማን ጉዳዩ "ማንም ከሕግ በላይ አይደለም" የሚል መሆኑን አጽንኦት ሰጥተውታል።

"በእነዚህ ስፖርተኞች ላይ እምነት ለሚጥሉ ሰዎች አሳዛኝ ቢሆንም ግን ይህ ስርዓቱ እንዴት መሥራት ይጠበቅበታል" ሲሉ ሃውማን ተናግረዋል።

"ኢንዱስትሪው በዝግጅቶቻቸው ላይ የሚፈጸሙ የአበረታች ቅመም ጥሰቶችን ለማጋለጥ የሚያስችሉ የፀረ-አበረታች ቅመም ጥረቶችን በጋራ በመደገፉ ሊመሰገን ይገባል።"