የሱቶን ግምት፡ ማንቸስተር ዩናይትድ ይሸነፋል፤ አርሰናል ከሜዳው ውጭ ያሸንፋል

ኢስቱፒና እና ራሽፈርድ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images

ሾን ዳይሽ ባለፈው የካቲት የኤቨርተን አሠልጣኝ ሆነው እንደተሾሙ በመጀመሪያ ጨዋታቸው አርሰናልን መርታታቸው ይታወሳል።

እሑድ ሁለቱ ቡድኖች ድጋሚ ሲገናኙ ኤቨርተን ይህን ድል ይደግመው ይሆን? ወይስ ከ2017 ወዲህ አርሰናል ለመጀመሪያ ግዜ በጉዲሰን ፓርክ ለመጀመሪያ ግዴ ድል ያደርግ ይሆን?

የቢቢሲ ስፖርት ተንታኙ ክሪስ ሱቶን አርሰናል ይህን ጨዋታ ሊያሸንፍ ይችላል ቢልም ፍልሚያው ቀላል እንደማይሆን ይገምታል።

ሱቶን፤ ኤቨርተን ከአርሰናል ብቻ ሳይሆን ሌሎች የፕሪሚዬር ሊግ ጨዋታዎችንም ገምቷል።

ቀይ መስመር

ቅዳሜ

ዎልቭስ ከሊቨርፑል

ዎልቭስ ከሊቨርፑል

ሱቶን በያዝነው የውድድር ዘመን ሊቨርፑል የማንቸስተር ሲቲ ተፎካካሪ ይሆናሉ የሚል ግምት አለው።

ምንም እንኳ በርካታ የሳዑዲ ክለቦች ሞሐመድ ሳላህን ለመግዛት ቢቋምጡም ሊቨርፑል ተጫዋቹን አለመሸጡ ተገቢ ነው ይላል።

የሊቨርፑል አጥቂ መስመርና አማካዩ ጥሩ አቋም ላይ ነው ያለው የሚለው ሱቶን ሊቨርፑል ወደ ዎልቭስ ሜዳ ተጉዞ ያሸንፋል ባይ ነው።

ግምት፡ 0 - 2

ቀይ መስመር

አስተን ቪላ ከክሪስታል ፓላስ

ማርክ ጉዬ በዓለም አቀፍ እረፍት ወቅት ለአገሩ እንግሊዝ ሲጫወት በመጎዳቱ ለክሪስታል ፓላስ ጉዳት ሊሆን ይችላል ይላል ሱቶን።

ምንም እንኳ ፓላስ መልካም አቋም ላይ ቢሆኑም በዚህ ጨዋታ ግን አስተን ቪላ ይረታል የሚል ግምቱን ያስቀምጣል።

ቪላ በያዝነው የውድድር ዘመን ወጣ ገባ ያለ አቋም ቢያሳዩም በሜዳቸው አይነኬ ናቸው።

ግምት፡ 2 - 0

ፉልሀም ከሉቶን

ፉልሀም ከሉቶን

ሱቶን እንደሚለው ከታችኛው ሊግ ያደገው ሉቶን ታውን ያለፉት ሶስት ጨዋታዎች መረታታቸው በራስ መተማመናቸውን የሚጎዳው ነው።

ወደ ክራቨን ኮቴጅ ተጉዘው ፉልሀምን የሚገጥሙት ሉቶኖች ይህ ፍልሚያ እንደሚከብዳቸው ይናገራል።

ምንም እንኳ ሉቶን ከጨዋታው አንድ ነገር ለማግኘት እንደሚጥሩ ቢያምን ድሉ ግን የፉልሀም ይሆናል ይላል።

ግምት፡ 2 - 0

ማንቸስተር ዩናይትድ ከብራይተን

ማንቸስተር ዩናይትድ ከብራይተን

ማንቸስተር ዩናይትድ ገና የውድድር ዘመኑን አልጀመሩም የሚለው ሱቶን ይህ ጨዋታ ሌላ ፈተና ይሆንባቸዋል የሚል እምነት አለው።

ባለፈው የውድድር ዘመን ብራይተን የመጀመሪያ ጨዋታቸውን ዩናይትድን ኦልድ ትራፈርድ ላይ በማሸነፈ ነው የጀመሩት።

ዘንድሮም ሊደግሙት ይሞክራሉ።

ምናልባት ይህ ጨዋታ ዩናይትድ ቅርፁን የሚያገኝበት ይሆናል። መልሶ ማጥቃት ላይ ምን ያህል ጠንካራ እንደሆኑ እናውቃለን የሚለው ሱቶን የብራይተን ጨዋታ ለዚህ የተመቸ ሊሆን እንደሚችል ይገምታል።

ነገር ግን ዩናይትድ የዘንድሮ አቋማቸውን ካልቀየሩ ለብራይተን የተመቸ ጨዋታ እንደሚሆን ይናገራል።

ግምት፡ 2 - 3

ቀይ መስመር

ቶተንሃም ከሼፊልድ ዩናይትድ

አዲሱ የቶተንሃም አሠልጣን አንጅ ፖስቴኮግሉ ቡድኑን እየቀየሩት እንደሆነ ሱቶን እምነት አለው።

በያዝነው የውድድር ዘመን ቶተንሃም ደስ የሚያሰኝ ኳስ እያሳዩ እንደሆነና ይህም ውጤት እያመጣላቸው እንደሆነ ሱቶን ያስረዳል።

ቢሆንም ሼፊልድ ዩናይትድ ከሲቲ ጋር ሲጫወቱ ያሳዩትን ዓይነት ጠንካራ መከላከል ከተገበሩ ለቶተንሃም ፈተና ይሆናል ባይ ነው።

እንደ ሱቶን ከሆነ ቶተንሃም አንድ ጎል ካስቆጠሩ ከመደጋገም የሚመልሳቸው የለም።

ግምት፡ 3 - 0

ዌስት ሃም ከ ሲቲ

ዌስት ሃም ከማንቸስተር ሲቲ

በዚህ ፍልሚያ ማንቸስተር ሲቲ ሙሉ በሙሉ ጨዋታውን ለመቆጣጠር ይሞክራሉ። ነገር ግን ይህ ለዴቪድ ሞየስ ጉዳያቸው አይደለም።

ዌስት ሃም አድፍጠው ጠብቀው መልሶ ማጥቃት ማድረግ ነው ዓላማቸው።

ምንም እንኳ ዌስት ሃም በመሰል ጨዋታዎች ተከላክሎ መልሶ በማጥቃት ቢታወቅም ሲቲን መርታት ግን ይሳነዋል የሚል ግምቱን ያስቀምጣሉ።

ግምት፡ 1 - 2

ቀይ መስመር

ኒውካስል ከብሬንትፈርድ

ኒውካስል ያለፉትን ሶስት ጨዋታዎች በተከታታይ ሽንፈት ቀምሷል። ብሬንትፈርድ ደግሞ በጣም የተደራጁና መች ማጥቃት እንዳለባቸው የሚያውቁ ናቸው።

ነገር ግን ኒውካስል ይህ ጨዋታ ከውጤት ቀውስ የሚወጣበት እንደሆነ ሱቶን ያምናል።

ባለፈው ዓመት ንቦቹ ወደ ኒውካስል ሜዳ መጥተው 5-0 ተረትተዋል። ዘንድሮም በሰፊ ልዩነት ይረታሉ ይላል።

ግምት፡ 4 - 0

እሑድ

ቦርንመዝ ከቼልሲ

ቦርንመዝ ከቼልሲ

ቼልሲ አሁን ባላቸው አቋም ምን እንደሚያደርጉ መገመት ከባድ ነው ይላል ሱቶን።

ቼልሲ ምንም እንኳ ጥሩ ጨዋታ ቢያሳዩም የፈጠሩትን ዕድል እየተጠቀሙበት አይደለም።

ቦርንመዝ ወደ ብሬንትፈርድ ተጉዘው ነጥብ ይዘው መምጣታቸው አስገርሞኛል የሚለው ሱቶን ጨዋታው አቻ እንደሚሆን ይገምታል።

ግምት፡ 1 - 1

ኤቨርተን ከአርሰናል

ኤቨርተን ከአርሰናል

ሾን ዳይሽ፤ ማይክል አርቴታን ድጋሚ በሜዳቸው ያሸንፉ ይሆን?

እርግጥ ነው ኤቨርተን ይህን ጨዋታ ቢረታ ትልቅ ዜና ነው። ምንም እንኳ ጉዲሰን ፓርክ ላይ ጥሩ ጨዋታ እያሳዩን ቢሆንም ኤቨርተን እንዲያሸንፍ መጠበቅ ተገቢ አይደለም ይላል ሱቶን።

ኤቨርተን በጨዋታው ጎል እንደሚያገቡ የሚገምተው ሱቶን የመጨረሻው ድል ግን የአርሰናል ይሆናል ይላል።

ግምት፡ 1 - 2

ሰኞ

ኖቲንግሃም ፎሬስት ከበርንሊ

ኖቲንግሃም ፎሬስት ከበርንሊ

በርንሊ ዘንድሮ ሶስት ጊዜ ሽንፈት ቀምሰዋል። ወደ ፕሪሚዬር ሊጉ ሲያድግ ብዙዎች በቪንሴንት ኮምፓኒ አሠልጣኝነት የሚያሳዩትን ኳስ ለማየት ጓጉተው ነበር።

ነገር ግን ይህ ፕሪሚዬር ሊግ ነው። ነጥብ ለማግኘት መከላከልም ይጠበቅባቸዋል።

የስቲቭ ኩፐር ኖቲንግሃም ፎሬስት ይህ ጨዋታ እንደሚያሸንፍ ሱቶን ግምቱን ያስፍራል።

ግምት፡ 2 - 1