ዛሬ ስምንት ቢሊዮን የደረሰው የዓለማችን ሕዝብ በየትኞቹ አካባቢዎች ይኖራል?
ላለፉት አስር ዓመታት ሰባት ቢሊዮን እንደነበረ ሲነገር የቆየው የዓለምችን ሕዝብ ብዛት፣ ዛሬ ስምንት ቢሊዮን ደርሷል። ከፍተኛው የዓለም ሕዝብ የሚኖርባቸው አገራት ሕንድ እና ቻይና ናቸው።
ዛሬ ስምንት ቢሊዮን የደረሰው የዓለም ሕዝብ በአውሮፓውያኑ 2030 ወደ 8.5 ቢሊዮን ከፍ ይላል ተብሎ ይጠበቃል።
በቀጣይ ዓመታት በዓለም ላይ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝብ ይኖራቸዋል ተብለው አስር አገራት ይጠበቃሉ። ከእነዚህ መካከል ግማሹ አፍሪካ ውስጥ የሚገኙ ሲሆን፣ በዋናነት ኢትዮጵያ እና ናይጄሪያ ይጠቀሳሉ።
ይህ ቪዲዮ የዓለማችን ስምንት ቢሊዮን ሕዝብ በየትኞቹ አካባቢዎች እንደሚገኙ ያመላክታል።









