የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ግምት

ሳውዛምፕተን ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

የእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ አራተኛ ሳምንት ጨዋታዎች ቅዳሜ ይካሄዳሉ።

የቢቢሲው እግር ኳስ ተንታኝ ክሪስ ሱቶን ለዚህ ሳምንት ጨዋታዎች ግምቱን አካፍሏል።

እንደ ሱቶን ከሆነ ባለፈው ሳምንት ማንቸስተር ዩናይትድ በሊቨርፑል እንደሚሸነፍ ገምቶ ነበር። ይህ የብዙዎች ግምት ቢሆንም ጨዋታውን ማንቸስተር አሸንፏል።

“ቀለል አድርጌ ነበር ያሰብኳቸው። ዩናይትድ በጨዋታው ላይ ድንቅ ነበሩ። አሁን ዋናው ጥያቄ በዚሁ ይቀጥላሉ ወይ የሚለው ነው” ይላል።

“አስገራሚ ሳምንታት ያለፉ ሲሆን ቡድኖችም ወጥ አቋም ማሳየት አልተቻላቸውም።”

ለዚህ ሳምንትም ሱቶን የሊጉን ጨዋታዎች ግምት አዘጋጅቷል።

ቅዳሜ

ሳውዛምፕተን ከ ማንቸስተር ዩናይትድ

ሳውዛምፕተን ባለፈው ሳምንት ከሌስተር ጋር በነበረው ጨዋታ መጀመሪያ ላይ ቢበለጥም የኋላ ኋላ ወደ ጨዋታው ለመመለስ ችሏል።

በመጨረሻም በማሸነፍ ሦስት ነጥቡን ማግኘት ችሏል። ለማንቸስተር ዩናይትድም ቀላል ተጋጣሚ አይሆኑም።

ማንቸስተር ዩናይትድ ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ ራሱን አሻሽሎ ይቀርባል ብዬ አላሰብኩም ነበር። የብዙዎችም አስተሳሰብ ተመሳሳይ ነበር።

በዚህ ጨዋታ ዩናይትድ ሦስት ነጥቡን ያሳካል።

ግምት፡ 1-2

ብሬንትፎርድ ከ ኤቨርተን

ኤቨርተን በተወሰነ ደረጃ ዕድለኛ አይደለም። ባለፈው ሳምንት ከኖቲንገሃም ፎረስ ጋር ብዙ ዕድል ቢፈጥሩም ማሸነፍ አልቻሉም።

ዴማራይ ግራይ በጨዋታው ጥሩ በመንቀሳቀስ ጎል ቢያስቆጥርም ቡድኑ የአጥቂ ችግር አለበት።

ብሬንትፎርድ ባለፈው ሳምንት በፉልሃም ተሸንፏል።

በዚህ ሳምንት በሜዳው እንደመጫወቱ በጠባብ ውጤት ያሸንፋል።

ግምት፡ 1-0

**

ብራይተን ከ ሊድስ

ሊድስ ጥሩ ውጤት በማስመዝገብ ከወዲሁ አስደንቆኛል።

አዳዲስ ፈራሚዎቻቸው ጥሩ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛሉ።

ሁለቱ ቡድኖች ባለፈው ዓመት ሁለቱንም የሊግ ጨዋታቸውን አቻ አጠናቀዋል። ሁለቱም ጎል አስቆጥረው አቻ ይለያያሉ።

ግምት፡1-1

**

ቼልሲ ከ ሌስተር

ቼልሲ ከተቀናቃኛቸው ሌስተር ተከላካዩን ዌስሊ ፎፋናን ለማስፈርም የሚያደርጉት ጥረት እስከ ቅዳሜ የሚሳካ አይመስልም።

ቼልሲ በኤላን ሮድ ከደረሰበት አስደንጋጭ ሽንፈት እንደሚያንሰራራ እገምታለሁ።

በጨዋታው ሊድስ የበላይ ሆኖ ሲያጠናቅቅ ቼልሲ ግን ተቀዛቅዞ ነበር ያመሸው።

የቶማስ ቱሄል ቡድን ጎል አስቆጣሪ ችግር ቢኖርበትም ይህንን ጨዋታ እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ግምት፡ 2-1

**

ሊቨርፑል እና በርንማውዝ

ሊቨርፑል ከ ብርንማውዝ

ሊጉ ገና ረዥም ርቀት ቢቀረውም ሊቨርፑል በዚህ ጨዋታ ሦስት ነጥብ ማሳካት ይኖርበታል።

አማካይ ስፍራ ላይ የፈጣሪ ተጫዋች ችግር ያለባቸው ሲሆን አጥቂው ዳርዊን ኑኔዝ በቅጣት አለመሰለፉም እንደጎዳቸው በዩናይትድ ጨዋታ ታይቷል።

ወደ ድል ለመመለስ ደግሞ በሜዳቸው ከበርንማውዝ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ትልቅ ዕድል ይዞላቸው መጥቷል።

በርንማውዝ ባለፈው ሳምንት በማንቸስተር ሲቲ ቢሸነፍም ተከላካይ ክፍሉ ጠንካራ ነው። በዚህ ጨዋታ ሊቨርፑል ቀድሞ ጎል ማስቆጠር ይገባዋል።

ግምት፡ 3-0

**

ማንቸስተር ሲቲ ከ ክሪስታል ፓላስ

ክሪስታል ፓላስ ባለፉት ጥቂት ዓመታት ሲቲን በሜዳው ማሸነፍ ችሏል።

ፓላስ በመልሶ ማጥቃት ጠንካራ ከሆኑ የሊጉ ክለቦች አንደኛው ቢሆንም ሲቲ ላይ አይሳካለትም።

ኒውካስል ነጥብ ለማግኘት ከሲቲ ጋር ኣደረገው ፉክክር ጠንካራ ሲሆን ፓላስ ግን ይህንን ያደርጋል ብዬ አለሳብም። ጎል ግን ያስቆጥራል።

ግምት፡ 3-1

**

አርሴናል ከ ፉልሃም

አርሴናል ደጋፊዎች በቡድናቸው ተስፋ መሰነቅ ጀምረዋል። ጋብርኤል ጂሰስ ድንቅ አጀማመር ያደረገ ሲሆን አርሴናል እንደሚያሸንፍ እገምታለሁ።

ፉልሃም ባለፈው ሳምንት ከብሬንትፎርድ ጋር በነበረው ጨዋታ ተገቢ የሆነ ድል አስመዝግቧል። ውድድር ዓመቱ ሲጀመር ማንም ባይገምትም ፉልሃም ጠንካራ መሆኑን እያሳየ ነው።

የባለፈው ሳምንቱ ውጤታቸው ጥሩ ቢሆንም በዚህ ሳምንት በአርሴናል ይፈተናሉ።

ግምት፡ 2-0

አርሴናል ከ ፉልሃም

እሁድ

አስቶን ቪላ ከ ዌስት ሃም

ሁለቱ ቡድኖች ውድድር ዓመቱን ተመሳሳይ መልክ ይዘው ነው የጀመሩት።

አስቶን ቪላ ባለፈው ሳምንት ከክሪስታል ፓላስ ጋር በነበረው ጨዋታ ሽንፈት ገጥሞታል።

ኤቨርተንን ቢያሸንፉም ከበርንማውዝ ጋር በነበራቸው ጨዋታም በመሸነፋቸው የዚህን ሳምንት ጨዋታ ይጠብቃሉ።

ዌስት ሃምም ውጤታማ መሆን አልቻለም። የመጀመሪያዎቹን ሦስት ጨዋታወች የተሸነፉ ሲሆን አሰልጣኝ ዴቪድ ሞዬስም ጫና እየመጣባቸው ነው።

ቡድናቸው ከፎረስት ጋር ጥሩ ቢጫወትም ውጤታማ አልሆኑም። ከብራይተን ጋር ጥሩ አልተጫወቱም። የተከላካይ መስመር ችግርም አለባቸው።

ግምት፡ 1-1

**

ዎልቭስ ከ ኒውካስል

ዎልቭስ ጎል ማስቆጠር እየከበደው ነው። ጥሩ ዕድል በመፍጠር እና ጥሩ ተጫዋቾችን በመያዝ በኩል ባይታሙም አፈጻጸም ላይ ችግር አለባቸው። ይህ በተደጋጋሚ የተባለ ነው።

በዚህ ምክንያት ተንከር ብለው የሚጫወቱ ቢሆንም ባለፈው ሳምንት ከማንቸስተር ሲቲ ጋር አቻ ከተለያየው ኒውካስል ጠንካራ ፉክክር ይጠብቃቸዋል።

አጨዋወታቸው፣ ወደ ፊት በከሚሄዱበት መንገድ እና ከማጥቃት ሂደታቸው አንጻር ኒውካስል ያሸንፋል ብዬ እገምታለሁ።

ግምት፡ 1-2

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቶተንሃም

ኖቲንግሃም ፎረስት ከ ቶተንሃም

በፎረስት አጀማመር ተደንቄያለሁ። ቡድኑ ከፍተኛ ገንዘብ ለተጫዋቾች ዝውውር ያወጣ መሆኑ መረሳት የለበትም።

ስቲቭ ኩፐርን የመሰለ ጥሩ አሰልጣኝ ቢኖራቸውም አጨዋወታቸው ለስፐርስ የተመቸ ነው።

በቶተንሃም ባልከፋም ከቼልሲ ነጥብ ተጋርተው ዎልቭስን በጠባብ ውጤት በማሸነፍ ጥሩ ውጤት አስመዝግበዋል።

የፎረስት አጨዋወት ለኮንቴ ቡድን የሚመች ይመስለኛል።

ግምት፡ 0-5