በኢትዮጵያ የ71 ሰዎችን ሕይወት የቀጠፈው የትራፊክ አደጋ

የተንቀሳቃሹ ምስል መግለጫ, በሲዳማ ክልል ሰርገኞች ላይ በደረሰ የትራፊክ አደጋ ሕይወታቸው ካለፈ 71 ሰዎች ውስጥ ከ50 በላይ የሚሆኑት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ዘመዳሞች ናቸው

አደጋው የደረሰው በዞኑ ቦና ዙሪያ ወረዳ ዕሁድ ታኅሳስ 20/ 2017 ዓ.ም. ከሰዓት 11:00 አካባቢ 'አይሱዚ' በተባለ የጭነት ተሽከርካሪ "ወደ ሙሽራዋ ቤት" እየተጓዙ የነበሩ ሰርገኞች ላይ ነው።

ሰርገኞቹ ሚሪዴ ከተባለ ቀበሌ ቤተ ክርስቲያን ደርሰው ወራንቻ ወደተባለ አካባቢ ሲጓዙ ጋለና ወንዝ ድልድይ ላይ ተሽከርካሪው መስመር በመሳት "ተወርውሮ" ወደ ወንዙ መግባቱን የአካባቢው ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ሰርገኞችን አሳፍሮ የነበረ ተሽከርካሪ ወደ ወንዝ በመግባቱ ነው አደጋው የተከሰተው ሲሉ ትራፊክ ፖሊስ ሳጅን እጅጉ ይልማ ይናገራሉ።