የኢራን አምበል ከመጀመሪያው ጨዋታ በፊት በአገሩ ስላለው ሁኔታ ተናገረ

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
በኳታሩ የዓለም ዋንጨ ዛሬ ከአንግሊዝ ብሔራዊ ብድን ጋር የሚጋጠመው የኢራን ብሔራዊ ቡደን አምበል ኢሳን ሀጅሳፊ አገሩ ስለምትገኝበት ሁኔታ ከጨዋታው በፊት ተናግሯል።
ከቅርብ ወራት ወዲህ በኢራን በኃይል የተሞሉ መንግሥትን የሚቃወሙ ሰልፎች እየታዩ ሲሆን፣ መንግሥትም የኃይል እርምጃዎችን እየወሰደ ይገኛል።
ዛሬ በዓለም ዋንጫ ከሚካሄደው የአንግሊዝ እና የኢራን ብሔራዊ ቡደንኖች ጨዋታ በፊት የ32 ዓመቱ የኢራን ተጨዋች የቡድን አጋሮቹ ከተቃውሞው ጋር በተያያዘ ከሞቱት ጎን እንደሚቆሙ ገልጿል።
“በአገራችን ያለው ሁኔታ ትክክል አይደለም። ሕዝባችንም ደስተኛ አይደልም” ሲልም አክሏል።
የኢራን መንግሥት የፀጥታ ኃይሎች ተቃውሞዎችን ለማርገብ በወሰዷቸው የኃይል እርምጃዎች ከ400 በላይ ተቃዋሚዎች መገደላቸውን እና 16 ሺህ 800 ሰዎች መታሰራችውን የሰብአዊ መብት ተሟጋች ድርጅቶች ይገልጻሉ።
የኢራን መሪዎች ታቀዋሚዎቹ በጠላቶች የተቀነበበረ “ሁከት” ተሳታፊዎች ናቸው ሲሉ ይከሳል።
“ከምንም ነገር በፊት በኢራን ለሚገኙ እና ሐዘን ለገባቸው ቤተሰቦች ያለኝን ሐዘን እገልጻለሁ” ሲል በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የተናገረው በተከላከይ ስፍራ የሚጫወተው ሃጅሳፊ “ከእነሱ ጋር እንደሆንን፣ ከጎናቸው እንደምንቆም እና እንዳዘንን ሊያውቁ ይገባል” ብሏል።
“ሁኔታውን ልንክደው አንችልም። በአገራችን ያለው ሁኔታ ጥሩ አይደልም። ይህንንም ተጫዋቾች ያውቃሉ” ሲልም አክሏል።
“እዚህ ተገኝተናል። ያ ማለት የእነሱ ድምጽ አንሆነም ወይም አናከብራቸውም ማለት አይደለም” ያለው ተጨዋቹ “ከማንም ጋር እንጫወት እንታገላለን ያልንን አቅም አውጥተን ተጨውተን፣ ጎል አግብተን በኢራን ለሚገኙ እና ሐዘን ላይ ለሆነው ሕዝባችን እናበረክታለን። ያ ደግሞ ሕዝባችን የሚጠብቀውን ነገር እንደሚቀይር ተስፋ አደርጋለሁ” ሲል ተናግሯል።
ኢራን በዩክሬን ወረራ ላይ ሩሲያን ትደግፋለች በሚል ወቀሳ እና የሴቶች አያየዝን ጨምሮ በአገሪቱ ያለውን የሰብአዊ መብት አያያዝ በመጥቀስ የዓለም ዋንጫ አዘጋጆች ከውድድሩ እንዲያግዷት የሚጠይቁ ዘመቻዎችም ታይተዋል።












