በርካታ የናይጄሪያ ታጣቂዎች ጥቃት ሲሸሹ ሰጥመው ሞቱ

ከቦኮሃራም የተማረኩ የጦር መሳሪያዎች

የፎቶው ባለመብት, AFP

በሰሜን ምስራቅ ናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት በርካታ ታጣቂዎች በመሬት እና በአየር ላይ የነበረውን ጥቃት ለመሸሽ ሲሞክሩ በወንዝ ውስጥ ገብተው ሰጥመው እንደሞቱ የደህንነት ምንጮች ገለጹ።

የቦኮሃራም ተዋጊዎች መደበቂያ በሆነው የሳምቢሳ ጫካ አካባቢ በሚገኙ መንደሮች ላይ ወታደሮች ጥቃት ሰንዝረዋል።

ታጣቂዎቹ የጦር ሰፈራቸውን ትተው ሲሸሹም ወንዝም ውስጥ የገቡ ሲሆን በወቅቱም ከፍተኛ ዝናብ ነበር ተብሏል።

ከመንግሥት ወታደሮች ጋር ወግነው የሚዋጉ የአካባቢው ሚሊሻዎች ከ100 በላይ የታጣቂ አስከሬኖችን ከወንዙ አውጥተው በአቅራቢያው እንደቀበሩ ተናግረዋል።

በአውሮፓውያኑ 2009 በጀመረው አመፅ በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ተገድለዋል እናም ወደ ሁለት ሚሊዮን የሚጠጉ ተፈናቅለዋል።