በዩኬ የተፈጠረውን የነዳጅ እጥረት ቀውስ ለማቃለል የሀገሪቱ ሰራዊት ዝግጁ ነው ተባለ

በለንደን የተሰለፉ መኪኖች

የፎቶው ባለመብት, EPA

በዩኬ የተፈጠረውና አራተኛ ቀን ባስቆጠረው የነዳጅ አቅርቦት መስተጓጎል ምክንያት የተፈጠሩ ረጃጅም ሰልፎችንና መሰል ችግሮችን ለማቃለል ሰራዊቱ ዝግጁ መሆኑ ተገለጸ።

በሀገሪቱ በተከሰተው የነዳጅ አቅርቦት ችግር የነዳጅ ማመላለሻ አሽከርካሪዎች እጥረትም ገጥሟል።

አስፈላጊ ሆኖ ከተገኘ እስከ 150 የሚደርሱ የወታደር ነዳጅ ጫኝ አሽከርካሪዎች ሥልጠና በመሰጠት ማሰማራት እንደሚቻልም ተጠቅሷል።

በርካታ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች የነዳጅ አቅርቦት ሊከሰት ይችላል በሚል ስጋት በርካታዎች በነዳጅ ማደያዎች በማጣሪያዎች በቁጥር በዝተው ይታያሉ።

ዩናይትድ ኪንግደም ከ100 ሺህ በላይ የጭነት መኪና አሽከርካሪዎች ያስፈልጋታል ተብሎ የሚገመት ሲሆን ባለፉት ወራት የምግብ አቅራቢዎችን እና ሱፐርማርኬቶችን ጨምሮ የተለያዩ ኢንዱስትሪዎች ችግር አጋጥሟቸዋል።

የሀገሪቱ ባለስልጣን በነዳጅ ማደያዎች ለሚታዩት ረጃጅም ሰልፎች ነዳጅ ሳያስፈልጋቸው ወደ ማደያዎች የሚሄዱ ሰዎችን ተጠያቂ አድርገዋል።

ኤኤሲሲ የተባለ ኩባንያ እንዳስታወቀው ከዓርብ ጀምሮ የአንድ ሊትር ነዳጅ ዋጋ በአንድ ሳንቲም ጨምሯል ይህም ከስምንት ዓመት በኋላ የታየ ነው።

ከፍተኛ ሰዎች በሚታዩባቸው ማደያዎች አነስተኛ ቁጥር ያላቸው ቸርቻሪዎች ዋጋውን ከዚህም በላይ እየጨመሩ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ ብሏል።

በሌላ በኩል እንደ ጤና እና ማህበራዊ እንክብካቤ ላሉ ወሳኝ ሠራተኞች ቅድሚያ የነዳጅ ተደራሽነት እንዲያገኙ ጥሪዎችን እያደረጉ ነው።