የ110 ዓመቷ የዕድሜ ባለጸጋ የዘፈኑት ሙዚቃ በቲክቶክ ገነነ

ከቲክ ቶክ የተወሰደ ምስል

የፎቶው ባለመብት, Family photo

የ110 ዓመቷ የዕድሜ ባለጸጋ በአንድ ምሽት የቲክቶክ የዓለም ኮከብ ሆኑ፡፡

እማማ አሚ ሐውኪንስ በቲክቶክ ዝነኛ ያደረጋቸው በአንደኛው የዓለም ጦርነት ወቅት ይዘመር የነበረን መዝሙር ለልደታቸው በመዝፈናቸው ነው፡፡

"It's A Long Way to Tipperary" የተሰኘውን መዝሙር እማማ አሚ ሲዘምሩት በቪዲዮ የቀረጻቸው የልጅ ልጅ ልጃቸው ነበር፡፡

በወቅቱ እማማ አሚ 110ኛ ዓመታቸውን እያከበሩ ነበር፡፡

የልጅ ልጅ ልጃቸው ሳቻ የ14 ዓመት ታዳጊ ሲሆን ይህን የእማማ አሚን ቪዲዮ ባጋራ በሰዓታት ውስጥ 100 ሺህ ተመልካች አግኝቷል፡፡

እማማ አማ የሞንማውዝ አካባቢ ተወላጅ ሲሆኑ በእርሳቸው እድሜ ሳሉ በመላው ብሪታኒያ እየዞሩ ይዘምሩ ነበር፡፡ ነገር ግን እናታቸው መዝፈን እንዲያቁሙ አድርገዋቸዋል፡፡

ምክንያቱም በዚያ ወቅት ሴት ልጅ መዝፈን የሚያስከብራት ተግባር አልነበረም፡፡

የሳቻ እናት ሐና ፍሪማን የልጃቸው ሳቻ ቪዲዮ በመላው ዓለም መወደድ በሰው ልጆች መልካምነት ላይ እምነት እንዲኖረን የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

እማማ አማ በመጀመሪያው የዓለም ጦርነት ወቅት ዕድሜያቸው 7 የነበረ ሲሆን በዚያ ዘመን ዝነኛ የነበረውን ሙዚቃ ነበር በልደታቸው ያዜሙት፡፡

እማማ አማ አሁን የሚኖሩት ከሦስት ባለቤታቸው ጋር ሲሆን በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ትልቋ ሴት አያታቸው ጋር አብሮ መኖር ምንኛ ደስ የሚል እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አሚ ሃውኪንስ

የፎቶው ባለመብት, Hannah Freeman

እሷ መስህባችን ናት፤ ክብ ሰርተን ከሷ ጋር ነው ጊዜያችንን የምናሳልፈው ይላሉ፡፡

የቲክቶክ መተግበሪያ የተጀመረው በ2016 ሲሆን አሁን በዓለም ላይ አንድ ቢሊዮን ተጠቃሚዎች አሉት፡፡ ቲክቶክ እጥር ምጥን ያሉ አጫጭር ቪዲዮዎችን የሚያጋሩበት መተግበርያ ነው፡፡

የሳቻ እናት ወ/ሮ ፍሪማን ነገሩን ለቀልድ ብለው ልጃቸውን እስኪ ቅድመ አያትህን ቅረጻቸው እንዳሉትና ይህ ይሆናል ብለው እንዳልጠበቁ ተናግረዋል፡፡