ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር እንደምታስገባ ገለጸች

የፎቶው ባለመብት, Getty Images
ኢትዮጵያ የኮሮናቫይረስ ክትባትን በመጪው ሚያዚያ ወር ወደ አገር ውስት እንደምታስገባ ገለጸች።
የሚገባው የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባት ቢያንስ 20 ከመቶ ለሚሆኑ ተጋላጭ የህብረተሰብ ክፍሎች እንደሚዳረስ የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ ይህንን የክትባት ሥራ የሚያስተባብር ግብረሃይል በብሄራዊ ደረጃ መቋቋሙም ተገልጿል።
በጤና ሚኒስቴር የክትባትና ተያያዥ ጉዳዮች የሚኒስትሯ ከፍተኛ አማካሪ ዶክተር ሙሉቀን ዮሃንስ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት በሰጡት መረጃ መሰረት፣ ከጤና ሚኒስቴር፣ ከጠቅላይ ሚኒስቴር እና ከፕሬዚዳንት ፅ/ት ቤቶች ጋር በመቀናጀት የኮሮናቫይረስ መከላከያ ክትባትን ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት ዝግጅቶች እየተደረጉ ነው፡፡
ክትባቱን ለመውሰድ ቅድሚያ የሚያገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች የዓለም ጤና ድርጅት ባወጣው መስፈርት መሰረት የጤና ባለሙያዎች፣ እድሜያቸው የገፉ፣ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ሰዎችና መጪውን ምርጫ ተከትሎ ተደራራቢ ስራና ሃላፊነት ያለባቸው የጥበቃ ኃይሎች መሆናቸውን ተገልጿል።
የክትባቱ ብዛት እየታየም ለአውቶብስና የባቡር አሽከርካሪዎች እንዲሁም በመንግስት ትምህርት ቤቶች ለሚሰሩ መምህራን እንዲዳርስ የሚደረግ መሆኑን ተመልክቷል።
ኢትዮጵያ ክትባቱን ወደ ሃገር ውስጥ የምታስገባው ‹‹ኮቫክስ›› በተሰኘው ዓለም አቀፍ የክትባት ሸማች ማህበር መሆኑንም ዶክተር ሙሉቀን ተናግረዋል።
የመጀመሪያው ዙር ክትባት እስከ መጪው ሚያዝያ ወር ወደ ሀገር ውስጥ እንደሚገባና በፈረንጆቹ አቆጣጠር እስከ 2021 መጨረሻ ድረስ ደግሞ ክትባቱ ሙሉ በሙሉ ወደ ሃገር ውስጥ እንደሚገባም አማካሪው ጠቁመዋል።
ኮቫክስ (COVAX) ምጣኔ ኀብታቸው ደካማና መካከለኛ ለሆኑ አገራት ክትባቱን ለማቅረብ ያለመ፣ በዓለም ጤና ድርጅት እና በሌሎች ዓለም አቀፍ የጤና ተቋማት የተመሰረተ ኢኒሼቲቭ ነው።
ሁሉም የአፍሪካ አገራት ይህንን ኢኒሼቲቭ ተቀብለውታል።
ይህም ማለት አፍሪካ በዚህ ኢኒሼቲቭ በኩል ክትባቱ ፍቃድ ካገኘና ከፀደቀ በኋላ፣ 220 ሚሊዮን ክትባቶችን ታገኛለች።
እኤአ በ2021 መጨረሻ ላይ ኮቫክስ 2 ቢሊዮን የኮቪድ-19 ክትባቶችን ለመግዛት እቅድ ይዟል።አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ ተገለፀ።
አጠቃላይ የተገኘው ክትባት በዚህ ዓመት ጥቅም ላይ እንደሚውል የሕብረቱ መሪ የደቡብ አፍሪካው ፕሬዚደንት ሲሪል ራማፎሳ ቃል ገብተዋል።
ይህ ክትባት ከዚህ ቀደም ቃል ከተገባው 600 ሚሊየን 'ዶዝ 'ተጨማሪ ቢሆንም አሁንም ግን ሙሉ አህጉሩን ለመከተብ በቂ አይደለም።
በዚህም የዓለማችን ድሃ አገራት ከሃብታም አገራት ይልቅ ክትባቱን ለመከተብ ረዥም ጊዜ ሊጠብቁ ይችላሉ የሚል ስጋት አለ።
ምንም እንኳን በአፍሪካ በቫይረሱ የተያዙ እና የሚሞቱ ሰዎች ቁጥር በንፅፅር ዝቅተኛ ቢሆንም በአንዳንድ አገራት በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በድጋሜ እየጨመረ ነው።
አፍሪካ ለአህጉሩ የሚሰራጭ ለጊዜው 270 ሚሊዮን 'ዶዝ' (መጠን) የኮቪድ-19 ክትባት በአፍሪካ ሕብረት በኩል ማግኘቷ መገለፁ ይታወሳል።